Get Mystery Box with random crypto!

B B C News አማርኛ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amharic1 — B B C News አማርኛ™ B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amharic1 — B B C News አማርኛ™
የሰርጥ አድራሻ: @bbc_amharic1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 62.41K
የሰርጥ መግለጫ

Broadcast & media production company
Addis Ababa, Ethiopia 🇪🇹

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-29 14:10:37 ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት ሙከራ ጀመረ!

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ተከታታይ የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት ሙከራ በድሬዳዋ ከተማ መጀመሩን አስታወቀ፡፡የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ፥ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ሂደት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች የሚካሔድ ሲሆን÷ ደንበኞች በ07 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት እንደሚችሉ ተገልጿል፡ደንበኞች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርዶች የድርጅቱ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት እንደሚችሉ እና ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሑፍ መልዕክቶች ጥቅል ያገኛሉም ተብሏል፡፡

የደንበኝነት ማስጀመሪያ ጥቅሉ በሚያልቅበት ጊዜ ደንበኞች የአየር ሰዓት ከሽያጭ ማዕከላት ወይም መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች በመግዛት መሙላት እና አገልግሎቱን በቀጣይነት መጠቀም እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡በድሬዳዋ ከተማ አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች፥ ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሑፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉ መገለጹን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

[Reporter]
@bbc_amharic1
13.8K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 09:59:51
መከላከያ ሰራዊት አሸባሪውን ቡድን እንደ አመጣጡ አፀፋዊ ምላሽ እየሠጠውና እየደመሰሰው እንደሚገኝ አስታወቀ!!

የአገር መከላከያ ሠራዊት ካለፈው የኅልውና ዘመቻዎች የጠላትን አሠላለፍ በውል በመገንዘብ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን እንደ አመጣጡ አፀፋዊ ምላሽ እየሠጠው እና እየደመሰሰው እንደሚገኝ አስታወቀ።

ሠራዊታችን የድል ሠራዊት ነው በሚል ባወጣው መግለጫ በየትኛውም ቦታና ጊዜ፣ አስቸጋሪ መልክአ ምድርንም ሆነ የአየር ፀባይ ተቋቁሞ ግዳጁን በድል አድራጊነት የሚወጣው ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ጠላትን በአስተማማኝ መመከት የሚችል ኃይል መሆኑን አረጋግጧል።

ሠራዊቱ ከራሱ ይልቅ ሕዝብን ያስቀደመ፣ ለሀገር እና ለሕዝብ ራሱን አሳልፎ የሠጠ ብሔራዊ ኩራታችን ነው ብሏል።

ጠላቶቻችን ሕዝባዊ ባህሪውን በውል ስለሚገነዘቡ ህፃናትንና ሴቶችን ከፊት አሰልፈው ክፍለ ዘመን ባለፈበት ጦርነት በሕዝብ መአበል መዋጋታቸው የሠራዊታችንን አይበገሬነትና ጀግንነት ጠንቅቀው ስለሚያውቁት እንደሆነ ገልጿል።ጠላት ለዜጎቹ ደንታ እንደሌለው ባሳየው በዚህ የኋላ ቀር ጦርነት ሠራዊታችን በከፍተኛ ጥንቃቄ እና የኃላፊነት መንፈስ ግዳጁን እየተወጣ እንደሆነ በማመልከት አሸባሪው ህወሓት በለኮሠው እሳት መልሶ እየለበለበው እንደሚገኝ መከላከያ ሰራዊት አስታዉቋል።

@bbc_amharic1
14.4K views06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:48:35
አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በጎረቤት አገራት መደበቁን መንግሥት ገለጸ

የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እየወሰዱ ባለው እርምጃ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከመዳከም አልፎ ወደ ጎረቤት አገራት በመሸሽ መደበቁን መንግሥት አስታወቀ፡፡

በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሸበሪ ቡድኑን ማዳከም መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

ቡድኑ እየተወሰደበት ባለው እርምጃ እየተዳከመ ቢሆንም የውሸት መረጃዎችን በማሰራጨት ለጥፋት ሀይሉ ሽፋን የሚሰጡ ግለሰቦች መኖራቸውን የጠቆሙ ሲሆን ሁኔታው በሕዝብ ዘንድ መጠራጠርን ለመፍጠር ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በወለጋ አሸባሪው ቡድን ጥቃት ላደረሰባቸው ዜጎች መንግሥት አስፈላጊውን ደጋፍ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የአሸባሪዎቹ አላማ ከውጭ ባንዳዎች ጋር በመተባበር ሕዝቡ በመንግሥት ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ህብረተሰቡ ከመንግስት ጋር በመቆም የህግ ማስከበር ዘመቻውን እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

@bbc_amharic1
8.4K views09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 20:13:38
#የጋራመኖሪያ

እርምጃ እየተወሰደባቸው ነው!!

ከ14ኛ ዙር የ20/80 እንዲሁም ከ40/60 3ኛ ዙር እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮና የቤቶች ቢሮ የተለያየ እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ሰራተኞች ስም ዝርዝር!!

1ኛ. ዶ/ር ሙሉቀን ሃብቱ ቢሮ ሃላፊ ከሃላፊነቱ የተነሳ

በቁጥጥር ስር የዋሉ፡-

1ኛ. አብርሀም ሰርሞሎ የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ
2 ኛ . መብራቱ ወልደኪዳን :_ዳይሬክተር
3ኛ. ሀብታሙ ከበደ :_ሶፍትዌር ባለሙያ
4ኛ. ዬሴፍ ሙላት :_ሶፍትዌር ባለሙያ
5ኛ. ጌታቸው በሪሁን :_ሶፍትዌር ባለሙያ
6ኛ. ቃሲም ከድር :_ሶፍትዌር ባለሙያ
7ኛ. ስጦታው ግዛቸው :_ሶፍትዌሩን ያለማ
8.ኛ. ባየልኝ ረታ ፡_ሶፍትዌር ተቆጣጣሪ
9ኛ. ሚኪያስ ቶሌራ ፡_የቤቶች ኢንፎሜሽንና ቴክኖሎጂ ባለሙያ
10ኛ .ኩምሳ ቶላ ፡_ የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳሬክተር

በቀጣይም ሂደቱን እየተከታተልን ለህዝባችን ማድረሳችንን የምንቀጥል ይሆናል፡፡

@bbc_amharic1
11.1K views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 14:26:38
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 6 ብር ጭማሪ ማድረጉን ገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከነገ ጀመሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን አስታውቋል።የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ለውጥን ብቻ መሰረት በማድረግ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ የሚዲ-ባሶች እና የሚኒ-ባስ ታክሲዎች የአገልግሎት ታሪፍ ማስተካከያ ከነገ ሐምሌ 7/2014 ዓ.ም ጀምሮ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 6 ብር ጭማሪ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮው አስታውቋል።በዚህም በሚዲ-ባስ 0.50 ሳንቲም እስከ 2.00 ብር የተጨመረ ሲሆን በሚኒ-ባስ 0.50 እስከ 6 ብር ተጨምሯል ተብሏል።

@bbc_amharic1
11.5K viewsedited  11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 14:16:02
ዩሮ እና የአሜሪካ ዶላር ለመጀመሪያ ጊዜ እኩል ሆኑ

ዩሮ እና የአሜሪካ ዶላር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እኩል እንደሆነና ከዚህ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ ዩሮ 12 በመቶ መቀነሱ ተገለጸ።

በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በተፈጠረው የኃይል አቅርቦት አለመመጣጠን የተነሳ አውሮፓ የኢኮኖሚ ውድቀት እንዳጋጠማት ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።

ከጦርነቱ በፊት 40 በመቶ የሚሆነውን ጋዝ በሩሲያ የቧንቧ መስመር ያገኝ የነበረው የአውሮፓ ኅብረት ከጦርነቱ በኋላ በሩሲያ ዘይት እና ጋዝ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ሲሞክር ሩሲያ በበኩሏ ለአንዳንድ የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት የጋዝ አቅርቦትን አቋርጣለች።

የኢነርጂ ቀውሱ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ያስከተለ ሲሆን የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክ የዋጋ ግሽበትን ለማውረድ ፖሊሲውን በበቂ ሁኔታ ማጥበቅ ስለመቻሉ ጥርጣሬን ፈጥሯል ነው የተባለው።

በዚህም የዩሮ ዋጋ ከዶላር እኩል በመሆኑ የወርቅ ግብይት ላይ አሉታዊ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

የዩሮ ዞን የዋጋ ግሽበት በ8 ነጥብ 6 መቶ ላይ በመቀመጡ ከአውሮፓዊያኑ 2011 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ወር የወለድ ምጣኔን እንደሚያሳድግ የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክ አስታውቋል።

@bbc_amharic1
11.1K views11:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 21:30:41
መንግሥት ለትግራይ ክልል የመልሶ ግንባታ ትግበራ ከተመድ ጋር ስምምንት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ለሚከናወነው የመልሶ ግንባታ ፕሮጀክት ትግበራ ከተመድ የፕሮጀክት አገልግሎት ቢሮ (UNOPS) ጋር የሦስተኛ ወገን የትግበራ ስምምንት በዛሬው ዕለት መፈራረሙን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ፕሮጀክቱ መንግሥት በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ በጦርነት የተጎዱ ማኅበረሰቦችን መልሶ የማቋቋም ፕሮጀክት በሚል ውጥን በመላው ሀገሪቱ ለማከናወን ያቀደው ፕሮጀክት አካል መሆኑ ተገልጿል።

የፕሮጀክቱ ዓላማዎችም፣ የመሠረታዊ አገልግሎቶችን እና ለአየር ፀባይ ለውጥ የማይበገር የማኅበረሰብ መሠረተ ልማትን መልሶ መገንባት እና ማሻሻል እንዲሁም በኢትዮጵያ በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች ውስጥ የሚገኙ እና የፆታ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የባለብዙ ዘርፍ ምላሽ አገልግሎቶችን ተደራሽነት ማሻሻል ናቸው።

በስምምነቱ መሠረት UNOPS በትግራይ ክልል የመልሶ መገንባት፣ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ማሻሻል እና የአየር ንብረት መቋቋም የሚችል ማኅበረሰባዊ መሠረተ ልማት መገንባት ተግባራትን ያከናውናል ተብሏል።

የተመድ የፕሮጀክት አገልግሎት ቢሮ ከመንግሥት ጋር በገባው ስምምነት መሠረት ማኅበራዊ ተቋማትን ይደግፋል፣ ከማኅበረሰቡ ጋር በመምከርም ማኅበረሰቡ ለሚፈልጋቸው አገልግሎቶች ፈጣን ምላሽ የሚያገኝበትን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ተብሏል።

@bbc_amharic1
12.3K views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 21:26:55
በጎንደር ከተማ ኤርትራውያንን የጫነ የመከላከያ መኪና ከፍተሻ አካላት ሲያመልጥ በቁጥጥር ስር ዋለ!

ከጎንደር ከተማ በቅርብ ርቀት ከምትገኘው አምባ ጊዎርጊስ ከተማ ከ 31ኛ ክፍለ ጦር እንደመጣ በመግለፅ ሶስት ኤርትራውያንን የጫነ ኮድ 06580 መ.ከ ሰሌዳ የመከላከያ ሰራዊት መኪና ለመፈተሽ ፈቃደኛ ባለመሆንና ኬላ በመጣስ ለማምለጥ ሲሞክር በቁጥጥር ስር ውሏል።

ወደ ጎንደር ከተማ እየገባ የነበረው ይህ መኪና የአካባቢው የኬላ ተቆጣጣሪዎች ሊያስቆሙት በሚሞክሩበት ጊዜ በቦታው የነበሩ እንስሳትን በመግጨት ሊያመልጥ ሙከራ አድርጓል።በማምለጥ ላይ ያለው ተሽከርካሪ ከጎንደር ከተማ በ 3 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ወለቃ ቀበሌ ላይ 3 ኤርትራዊያን የጫነው ሹፌር ከነመኪናው በመከላከያ ሰራዊት ኃይል ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ሶስት ኤርትራውያንና የመኪናው አሽከርካሪ በጎንደር ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።

[Addis Zeybe]
@bbc_amharic1
11.2K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 15:07:25
የአሜሪካ የህዋ ተመራማሪዎች በእጅጉ ውጤታማ ነው የሚባለውን የጥንታዊ ህዋን ፎቶግራፍ ማንሳታቸው ይፋ ሆኗል፡፡

10 ቢሊዮን ዶላር ወጭ በተደረገበት ኢንፍራሬድ የጄምስ ዌብ ቴሌስኮፕ የተነሳው ግልፅ ያለ ፎቶግራፉ ወደ ምድር ለመድረስ ቢሊዮን እና ቢሊዮን አመታት የሚፈጅባቸውን ሩቅ ያሉ የህዋ አካላት ጭምር ያካተተ ሲሆን ይህም የጥንታዊው አለም ወይም ህዋ አፈጣጠርን በውል ለመረዳት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በሳይንስ እንደሚታመነው የሰው ልጅ በህዋ በአንዳች መንገድ ብዙ ቢሊዮን የብርሃን አመታት ርቀት (ላይት ይር) ቢጓዝ ምድር እንዴት እንደተፈጠረች መመልከት ይቻላል፡፡ይህ የህዋን ዝርዝር መረጃ በግልጽ የሚያሳዩት ምስሎች ይፋ የሆኑትም የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ከተመለከቷቸው በኋላ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ በዚሁ የጄምስ ዌብ የህዋ መመልከቻ መነፅር ወይም ቴሌስኮፕ የተነሱ ተጨማሪ ፎቶግራፎች በተከታታይ ለህዝቡ ይፋ ይደረጋሉ ተብሏል፡፡

ጆ ባይደን ፎቶግራፎቹን ከተመለከቱ በኋላ ከነዚህ ፎቶዎች አለም የሚረዳው አሜሪካ ትላልቅ ነገሮችን መስራት እንደምትችል ነው ማለታቸው በዘገባው ተጠቁሟል፡፡

@bbc_amharic1
12.6K views12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 14:40:36
በደሴ ከተማ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

በደሴ ከተማ በተለምዶ ሳላይሽ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በደሴ ከተማ የ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር አለባቸው መለሰ ለኤፍቢሲ እንደገለጹት ዛሬ 5 ሰዓት ከ30 ላይ ሳላይሽ በግ ተራ አካባቢ የቆራሌ ዕቃ በሚራገፍበት ሰዓት ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ነገር ፈንድቶ በሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡
በፍንዳታው በግ ሲገዙ የነበሩ ሰዎችና የቀን ሠራተኞች ላይ ጉዳት መድረሱ የተገለጸ ሲሆን ተጎጂዎችም ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
የፖሊስ መረጃ እንደሚያመላክተው እስካሁን ድረስ ከ31 በላይ ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ15 በላይ በቦታው ለሽያጭ የቀረቡ በጎች ሞተዋል።

@bbc_amharic1
11.7K views11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ