Get Mystery Box with random crypto!

የአሜሪካ የህዋ ተመራማሪዎች በእጅጉ ውጤታማ ነው የሚባለውን የጥንታዊ ህዋን ፎቶግራፍ ማንሳታቸው ይ | B B C News አማርኛ™

የአሜሪካ የህዋ ተመራማሪዎች በእጅጉ ውጤታማ ነው የሚባለውን የጥንታዊ ህዋን ፎቶግራፍ ማንሳታቸው ይፋ ሆኗል፡፡

10 ቢሊዮን ዶላር ወጭ በተደረገበት ኢንፍራሬድ የጄምስ ዌብ ቴሌስኮፕ የተነሳው ግልፅ ያለ ፎቶግራፉ ወደ ምድር ለመድረስ ቢሊዮን እና ቢሊዮን አመታት የሚፈጅባቸውን ሩቅ ያሉ የህዋ አካላት ጭምር ያካተተ ሲሆን ይህም የጥንታዊው አለም ወይም ህዋ አፈጣጠርን በውል ለመረዳት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በሳይንስ እንደሚታመነው የሰው ልጅ በህዋ በአንዳች መንገድ ብዙ ቢሊዮን የብርሃን አመታት ርቀት (ላይት ይር) ቢጓዝ ምድር እንዴት እንደተፈጠረች መመልከት ይቻላል፡፡ይህ የህዋን ዝርዝር መረጃ በግልጽ የሚያሳዩት ምስሎች ይፋ የሆኑትም የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ከተመለከቷቸው በኋላ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ በዚሁ የጄምስ ዌብ የህዋ መመልከቻ መነፅር ወይም ቴሌስኮፕ የተነሱ ተጨማሪ ፎቶግራፎች በተከታታይ ለህዝቡ ይፋ ይደረጋሉ ተብሏል፡፡

ጆ ባይደን ፎቶግራፎቹን ከተመለከቱ በኋላ ከነዚህ ፎቶዎች አለም የሚረዳው አሜሪካ ትላልቅ ነገሮችን መስራት እንደምትችል ነው ማለታቸው በዘገባው ተጠቁሟል፡፡

@bbc_amharic1