Get Mystery Box with random crypto!

በደሴ ከተማ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ በደሴ ከተማ በተለምዶ ሳላይሽ ተብሎ በሚጠ | B B C News አማርኛ™

በደሴ ከተማ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

በደሴ ከተማ በተለምዶ ሳላይሽ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በደሴ ከተማ የ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር አለባቸው መለሰ ለኤፍቢሲ እንደገለጹት ዛሬ 5 ሰዓት ከ30 ላይ ሳላይሽ በግ ተራ አካባቢ የቆራሌ ዕቃ በሚራገፍበት ሰዓት ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ነገር ፈንድቶ በሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡
በፍንዳታው በግ ሲገዙ የነበሩ ሰዎችና የቀን ሠራተኞች ላይ ጉዳት መድረሱ የተገለጸ ሲሆን ተጎጂዎችም ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
የፖሊስ መረጃ እንደሚያመላክተው እስካሁን ድረስ ከ31 በላይ ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ15 በላይ በቦታው ለሽያጭ የቀረቡ በጎች ሞተዋል።

@bbc_amharic1