Get Mystery Box with random crypto!

B B C News አማርኛ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amharic1 — B B C News አማርኛ™ B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amharic1 — B B C News አማርኛ™
የሰርጥ አድራሻ: @bbc_amharic1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 62.41K
የሰርጥ መግለጫ

Broadcast & media production company
Addis Ababa, Ethiopia 🇪🇹

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 12:42:45
የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ኃይሎች ጥቃት ከፍተዋል ብለዋል። በጉዳዩ ላይ የኤርትራም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስታት ዛሬ ያሉት ነገር የለም።

@bbc_amharic1
5.1K views09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:40:26
"ሕወሐት ወረራውን እያስፋፋ መጮኹን ቀጥሎበታል"

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ሕወሐት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በየአቅጣጫው በለኮሰው እና ዛሬም እያስፋፋ ባለው እሳት ንጹሐን እየተገደሉ ነው፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ፣ ንብረትም እየወደመ ነው።

አሁን እንደሚታየው አሸባሪውን ሕወሓት ከሀገር አጥፊነት ተግባሩ የማስቆም ግዴታ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ላይ ወድቋል። ምክንያቱም:-

1. የሽብር ቡድኑ ሰላማችንን እንዳያደፈርስና ሀገራችንን እንዳያፈርስ መከላከል ስለሚገባ፤

2. ሕወሐት ወደ ትግራይ የሚላከውን ርዳታ ለተቸገረው ሕዝብ እንዳይደርስ፣ በተቃራኒው እርዳታው ለጦርነት እንዲውል እያደረገ በመሆኑ መንግሥት እርዳታው ለተረጂው ሕዝብ እንዲደርስና ትግራይ ውስጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሕዝቡን ከችግር የመከላከል ግዴታ ስላለበት፤

3. ሕወሐት በእኩይ ተግባሩ ሕዝብን በረሃብ ለመቅጣት አቅዶ ተደጋጋሚ ጦርነት የሚከፍተው በክረምት የግብርና ወቅት በመሆኑ መንግሥት ወረራውን እየተከላከለ ያለው ሕዝብን ከረሃብ የማዳን ግዴታ ስላለበት ጭምር ነው።

ይሁንና በሕወሓት የሽብር ቡድን እየደረሱ የሚገኙ ጥፋቶችን ለማስቆም መንግሥት ለሰላማዊ አማራጭ ያደረጋቸው ጥረቶች ሁሉ እየመከኑ ባሉበት ሁኔታ፣ አሸባሪውን ሕወሓት መጫን ሲገባቸው "ሁለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም።

በመሆኑም ሕወሓት ተደጋጋሚ የሰላም አማራጮችን በመግፋት የከፈተው ጥቃት ሃገራችንን እንዳይበትን፣ የመከላከያ ኃይላችን በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተበትን ወረራ ከሰላም ወዳዱ ደጀን ሕዝብ ጋር በመሆን በጽኑ ጀግንነት በመከላከል ላይ ይገኛል።

@bbc_amharic1
5.1K views09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 23:44:29
ቪዲዮ - በጦርነቱ የተማረኩት ህፃናት ልጆች ምን ይላሉ?

"... ለአንድ ባለስልጣን ተብሎ፣ ለአንድ ሰው ብሎ የሞተውን ሰው እናንተ አላያችሁም የሞተው እንደኔ ቢማረክ ጥሩ ነበር"

"... የትግራይ ህዝብ ይሄን ጁንታ አትመኑት ፣ አትውጡ"

"...አንድ የሀብታም ልጅ እኮ አታገኙም፣ የደሀው ልጅ ነው ፣ የደብረፂዮን ልጅ የለም፣ የጌታቸው ረዳ ልጅ የለም... የትግሬ የደሀ ልጅ ግን አለ፣ የሞተም አለ። የአለም ህዝብ ቢያየን ጥሩ ነው። ዝም ብሎ እየሞትን እያየን ነው"

@bbc_amharic1
3.7K views20:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 23:08:17
#Breaking
የአውሮፓ ህብረት ከሩሲያ ጋር የነበረውን “የቪዛ ማመቻቸት ስምምነት” ሙሉ በሙሉ ለማቆም ወሰነ!!

ውሳኔው የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ በህብረቱና እና በሩሲያ መካከል የነበረው “የቪዛ ማመቻቸት ስምምነት” ለማቆም ሚያስችላቸውን እርምጃ ለመውሰድ ላለፉት ሁለት ቀናት በቼክ ሪፐብሊክ ከመከሩ በኋላ የተደረሰ ስምምነት ነው ተብሏል፡፡

ሚኒስተሮቹ በውይይታቸው ከሩሲያ ወደ አጎራባች ግዛቶች የሚደረጉ የድንበር ማቋረጦች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ትኩረት ሰጥተው የተመለከቱት አንኳር ነጥብ እንደነበር የአውሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል አስታውቋል፡፡ሚኒስትሮቹ የድንበር ማቋረቱ ሁኔታ በአውሮፓ ከፍተኛ የሆነ ደህንነት ስጋት መደቀኑን በተመለከተ መወያየታቸውም ተገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት የአውሮፓ ህብረት ከሩሲያ ጋር የነበረውን “የቪዛ ማመቻቸት ስምምነት” ሙሉ በሙሉ ለማቆም መወሰኑ ጆሴፕ ቦሬል ከደቂቃዎች በፊት በትዊተር ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ ይፋ አድርገዋል፡፡

@bbc_amharic1
4.7K views20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 22:36:35
ወለጋ

በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ አገምሳ ከተማ ትናንት ከማለዳ ጀምሮ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ 55 ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ!!

የአከባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ለአንድ ዓመት ያህል የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የአከባቢውን ፀጥታ ሲያስከብሩ ነበር። ይሁንና ባለፈው ዕሁድ ነሐሴ 22 ቀን፣ 2014 የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከከተማዋ መነሳታቸውን ተከትሎ የተለያዩ ስያሜ ያላቸው ታጣቂዎች በከተማዋ መፈራረቃቸውን ነው የዐይን እማኞች የገለጹት።

የአይን እማኞቹ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት «መንግስት ‘ሸኔ’ ያላቸው “የኦሮሞ ነጻነት ጦር” ሰኞ ጠዋቱን ገብተው ከተማዋን ተቆጣጠሩዋት» ብለዋል።ታጣቂዎቹ ከተማዋ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መንቀሳቀስ ከጀመሩ በኋላ ወደ 59 መሳሪያ ከማህበረሰቡ አስፈትተው በዚያው ሰኞ ቀን ከተማዋን ለቀው ወጥተዋል፡፡

“ትናንት ማክሰኞ ጠዋት ደግሞ ፋኖ ነን ያሉ የታጠቁ አካላት ወደ ከተማዋ ገብተው ከኦነግ ጋር አብራችኋል በሚል በመደዳው ከተማዋ ላይ ተኩስ በመክፈታቸው ከ15 ሺህ የማያንሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል” ነው ያሉት፡፡

ከትናንት ማታ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የ55 ሲቪል ዜጎች አስከሬን መቅበራቸውንና የ32 ሰዎች አስከሬን በየጫካውና በየገደሉ እየፈለግን ነው” ሲሉም የችግሩን ስፋት አስረድተዋል፡

(ምንጭ፣ የጀርመን ድምፅ/Dw)
@bbc_amharic1
5.6K views19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:20:51 ህወሓት ወልዲያን ተቆጣጥሯል የሚባለዉ ሀሰተኛ ነዉ

የወልዲያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ

የህወሓት ሃይል ወልዲያ ከተማን ተቆጣጥሯል እየተባለ በተለያዩ ሚዲያዎች የሚነዛው ወሬ ሀሰት ነው ሲል የወልዲያ ከተማ መስተዳድር አስታውቋል።

የወልዳያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ዶ/ር ዳዊት መለሰ ከተማዋ በጠላት ቁጥጥር ስር አለመውደቋን እና ሰላም መሆኗን ለሁሉም ማህበረሰብ መግለፅ እወዳለሁ ሲሉ በመግለጫቸው ተናግረዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ጥምሩ ሃይሉ ከቆቦ ከተማ ለቆ መውጣቱን መነሻ በማድረግ ወደ ከተማችን ብዙ ማህበረሰብ በመፍለሱና ሲዋጋ የነበረው የመከላከያ ሰራዊት ወደ ወልዲያ ከተማ መምጣቱ ተከትሎ ማህበረሰባችን በትላንትናው ዕለት ትንሽ የተረበሸ ቢሆንም ከትላንትና ጀምሮ ሁላችንም በጋራ በመረባረብ ማህበረሰባችን እንዲረጋጋና ሰላሙ ወደነበረበት እንዲመለስ እየሰራን ነው ብለዋል።

ከተማዋ ሰላም መሆኗንና በአሁኑ ስአት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ የአማራ ልዩ ሃይል ፍኖና ሚሊሻ በጥምረት በግንባር እየተዋደቁ በመሆኑ ከከተማዋ ማህበረሰብ በተጨማሪም መላው የሰሜን ወሎ ህዝብ የክልሉና አጠቃላይ የኢትዮጽያ ህዝብ ለጥምር ጦሩ ደጀን እንዲሆን ጥሪ ማቅረባቸውን ብስራት ከከተማ መስተዳድሩ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

@bbc_amharic1
11.1K views14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 16:11:47
በቂ መሳሪያ ሳይሆን በቂ ሰው ስላለን ሕዝባዊ ማዕበል ችግር የለውም - የአሸባሪው ሕወሓት አፈቀላጤ ጌታቸው ረዳ የጭካኔ ጥግ

@bbc_amharic1
11.9K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:41:45
በመቀሌ ከተማ የአየር ድብደባ መፈፀሙ ተገለፀ!!

የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ትናንት እኩለ ሌሊት በሰው አልቫ አውሮፕላን ድብደባ ተፈፅሟል።ድብደባው ያደረሰዉ ጉዳት ስለመኖር-አለመኖሩ ግን ቃል አቀባዩ አልገለፁም።

በፌደራል መንግሥት እና በሕወሃት መካከል በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ግጭት ካገረሸ ወዲህ፣ በመቀሌ የአየር ድብደባ እንደተፈጸመ ሕወሃት ሲገልጽ የአሁኑ ሁለተኛው ነው።

@bbc_amharic1
11.8K views12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:22:37
ሕወሓት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አካባቢ ወረራ ከፍቷል” የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት

የሕወሐት ዕብሪት ለሰላም የተዘረጉ እጆች እንዲታጠፉ እያስገደደ ነው!

መንግሥት ለሰላም አማራጭ ዕድል ለመስጠት ሲል የሕዝብ ማዕበል አስነሥቶ ሕጻናትን፣ ወጣቶችንና አረጋውያንን ለመማገድ የመጣውን የሕወሐት ታጣቂ፣ በምሥራቅ አማራ በኩል በጀግንነት ሲከላከል ቆይቷል። ሕወሐት በምሥራቅ አማራ በኩል በቆቦና አካባቢው የከፈተው ወረራ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና በደጀኑ ሕዝብ ጠንካራ የመከላከል ብቃት የተነሣ ባሰበው ልክ አልሄደለትም።

በዚህም ምክንያት ለሰላም የተሰጠውን ሁለንተናዊ አማራጭ አሽቀንጥሮ ጥሎ ወረራውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች እያስፋፋ ይገኛል። ያለ ጦርነት መኖር የማይችለው ሕወሐት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አካባቢ ወረራ ከፍቷል።

ይሄንን የሕወሐት ወረራ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት በተሟላ ዝግጅትና በጽኑ ቁመና እየተከላከለ ይገኛል። የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ አቅጣጫዎች የተከፈቱበትን ጥቃቶች በጽናት እየተከላከለ፣ አሁንም ለሰላም አማራጮች የዘረጋቸውን እጆች ዛሬም ድረስ አላጠፈም።

ለሰላም የተዘረጋው እጅ በሕወሐት ዕብሪታዊ ወረራ ምክንያት እንዳይታጠፍ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚቻለውን እንዲያደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት አሁንም ያሳስባል። ወገናችን የሆነው የትግራይ ሕዝብም ይሄንን የዕብሪት ወረራ በማውገዝ ሕወሐት ከሚያስከትልበት መከራ ራሱን ነጻ እንዲያወጣ ጥሪ እናቀርባለን።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
@bbc_amharic1
12.5K views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 00:17:48
ወደ ወልድያ ከተማ ለማቅናት ያሰበው የትሕነግ ወራሪ ቡድን እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ እግሩ ከሼህ ሁሴን ጅብሪል የትንቢት ሜዳ መሐልና ጠርዝ አልዘለለም።

ቡድኑ የተመኘውን የባሩድ ጸበል ከምድር በሚፈልቅ ብቻ ሳይሆን ከሰማይም በሚዘንብ እየተቸረው ይገኛል።

የትግራይ ወራሪ ሃይል ወልዲያ ከተማን ተቆጣጥሯልም እየተባለ በተለያዩ ሚዲያዎች የሚነዛው ወሬ ሀሰት ነው ሲሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶክተር ዳዊት መለሰ አስታውቀዋል።

ወልዲያ ከተማ በጥላት ቁጥጥር ስር አለመውደቋን እና ሰላም መሆኗን ለሁሉም ማህበረሰብ መግለፅ እወዳለሁ ነው ያሉት ከንቲባው በመግለጫቸው።

ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን።
@bbc_amharic1
5.9K views21:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ