Get Mystery Box with random crypto!

በጎንደር ከተማ ኤርትራውያንን የጫነ የመከላከያ መኪና ከፍተሻ አካላት ሲያመልጥ በቁጥጥር ስር ዋለ! | B B C News አማርኛ™

በጎንደር ከተማ ኤርትራውያንን የጫነ የመከላከያ መኪና ከፍተሻ አካላት ሲያመልጥ በቁጥጥር ስር ዋለ!

ከጎንደር ከተማ በቅርብ ርቀት ከምትገኘው አምባ ጊዎርጊስ ከተማ ከ 31ኛ ክፍለ ጦር እንደመጣ በመግለፅ ሶስት ኤርትራውያንን የጫነ ኮድ 06580 መ.ከ ሰሌዳ የመከላከያ ሰራዊት መኪና ለመፈተሽ ፈቃደኛ ባለመሆንና ኬላ በመጣስ ለማምለጥ ሲሞክር በቁጥጥር ስር ውሏል።

ወደ ጎንደር ከተማ እየገባ የነበረው ይህ መኪና የአካባቢው የኬላ ተቆጣጣሪዎች ሊያስቆሙት በሚሞክሩበት ጊዜ በቦታው የነበሩ እንስሳትን በመግጨት ሊያመልጥ ሙከራ አድርጓል።በማምለጥ ላይ ያለው ተሽከርካሪ ከጎንደር ከተማ በ 3 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ወለቃ ቀበሌ ላይ 3 ኤርትራዊያን የጫነው ሹፌር ከነመኪናው በመከላከያ ሰራዊት ኃይል ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ሶስት ኤርትራውያንና የመኪናው አሽከርካሪ በጎንደር ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።

[Addis Zeybe]
@bbc_amharic1