Get Mystery Box with random crypto!

ዩሮ እና የአሜሪካ ዶላር ለመጀመሪያ ጊዜ እኩል ሆኑ ዩሮ እና የአሜሪካ ዶላር በታሪክ ለመጀመሪያ | B B C News አማርኛ™

ዩሮ እና የአሜሪካ ዶላር ለመጀመሪያ ጊዜ እኩል ሆኑ

ዩሮ እና የአሜሪካ ዶላር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እኩል እንደሆነና ከዚህ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ ዩሮ 12 በመቶ መቀነሱ ተገለጸ።

በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በተፈጠረው የኃይል አቅርቦት አለመመጣጠን የተነሳ አውሮፓ የኢኮኖሚ ውድቀት እንዳጋጠማት ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።

ከጦርነቱ በፊት 40 በመቶ የሚሆነውን ጋዝ በሩሲያ የቧንቧ መስመር ያገኝ የነበረው የአውሮፓ ኅብረት ከጦርነቱ በኋላ በሩሲያ ዘይት እና ጋዝ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ሲሞክር ሩሲያ በበኩሏ ለአንዳንድ የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት የጋዝ አቅርቦትን አቋርጣለች።

የኢነርጂ ቀውሱ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ያስከተለ ሲሆን የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክ የዋጋ ግሽበትን ለማውረድ ፖሊሲውን በበቂ ሁኔታ ማጥበቅ ስለመቻሉ ጥርጣሬን ፈጥሯል ነው የተባለው።

በዚህም የዩሮ ዋጋ ከዶላር እኩል በመሆኑ የወርቅ ግብይት ላይ አሉታዊ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

የዩሮ ዞን የዋጋ ግሽበት በ8 ነጥብ 6 መቶ ላይ በመቀመጡ ከአውሮፓዊያኑ 2011 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ወር የወለድ ምጣኔን እንደሚያሳድግ የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክ አስታውቋል።

@bbc_amharic1