Get Mystery Box with random crypto!

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በጎረቤት አገራት መደበቁን መንግሥት ገለጸ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እየወሰ | B B C News አማርኛ™

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በጎረቤት አገራት መደበቁን መንግሥት ገለጸ

የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እየወሰዱ ባለው እርምጃ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከመዳከም አልፎ ወደ ጎረቤት አገራት በመሸሽ መደበቁን መንግሥት አስታወቀ፡፡

በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሸበሪ ቡድኑን ማዳከም መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

ቡድኑ እየተወሰደበት ባለው እርምጃ እየተዳከመ ቢሆንም የውሸት መረጃዎችን በማሰራጨት ለጥፋት ሀይሉ ሽፋን የሚሰጡ ግለሰቦች መኖራቸውን የጠቆሙ ሲሆን ሁኔታው በሕዝብ ዘንድ መጠራጠርን ለመፍጠር ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በወለጋ አሸባሪው ቡድን ጥቃት ላደረሰባቸው ዜጎች መንግሥት አስፈላጊውን ደጋፍ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የአሸባሪዎቹ አላማ ከውጭ ባንዳዎች ጋር በመተባበር ሕዝቡ በመንግሥት ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ህብረተሰቡ ከመንግስት ጋር በመቆም የህግ ማስከበር ዘመቻውን እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

@bbc_amharic1