Get Mystery Box with random crypto!

B B C News አማርኛ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amharic1 — B B C News አማርኛ™ B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amharic1 — B B C News አማርኛ™
የሰርጥ አድራሻ: @bbc_amharic1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 62.41K
የሰርጥ መግለጫ

Broadcast & media production company
Addis Ababa, Ethiopia 🇪🇹

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-31 00:17:48
ታዳጊዋ የ10,000.00 ዶላር ሽልማቷን ለብፁዕነታቸው አበረከተች!
**
ይችን ድንቅ ብላቴና ሎዛ ትባላለች። በትምህርቷ እጅግ ድንቅ ብቃት በማስመዝገቧ የ10ሺ ዶላር ሽልማት ትምህርት ቤቷ ይሸልማታል።

ልበ በርሀኗ ሎዛ በአሜሪካ በተለያዩ ከተሞች እየዞሩ ለፈረሰችው ወልድያ እና ላሊበላ ገንዘብ እየሰበሰቡ ለሚገኙት ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ቃል ገብታ ሰነበተች።

ታዲያ ዛሬ በቅዱስ ገብርኤል ዲሲ የተገኙት ብፁእነታቸው እዚህም በመሰብሰብ ላይ እያሉ ይች ትንሽዬ ብላቴና "ካለኝ ላይ ቀንሼ ሳይሆን የተሸለምኩትን ሙሉ ብር ይሄው እውቀቱን የሰጠኝ አምላክ ነው እሱ የሰጠኝን ለሱ" ብላ ሙሉውን ሰጠች።

የዘመኑ ሰው እንኳን ያለውን ካለው ላይ ማካፈል በማይፈልግበት በዚህ ዘመን ልበ ብርሀኑዋ ሎዛ ሙሉ የሽልማት ገንዘቧን ለግሳለች።

Via:- orthodox tewohido network
@bbc_amharic1
5.6K views21:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 23:25:39
የሰዓት እላፊ ገደብ መረጃ !!

ወልድያ ከተማ
ለሰው- ከምሽቱ 12፡00 እስከ ንጋቱ 1፡00

ለተሽከርካሪ- እስከ ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ

ሰቆጣ ከተማ
ለሰው- ከምሽቱ 1፡00 እስከ ንጋቱ 12፡00
ለተሽከርካሪ - ከምሽቱ 12፡00 እስከ ንጋቱ 12፡00
ለተፈናቃይ - ከካምፕ ውጭ መንቀሳቀስ ሙሉ በሙሉ ክልክል ነው።

ሐይቅ ከተማ
ሰው- ከምሽቱ 2፡00 በኋላ
ለተሽከርካሪ- ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ
መጠጥ ቤቶች - ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ
ኩታበር
ተሽከርካሪ- ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ
መጠጥ ቤቶች- ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ
ሰው- ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ

ደሴ ከተማ

ለከተማው ነዋሪ- ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ
ለምግብና መጠጥ ቤቶች ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ
ለማንኛውም እንግዳ- ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ
ለታክሲ- ከምሽቱ 2፡ዐዐ ጀምሮ
ለባጃጅ- ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ

ኮምቦልቻ ከተማ
ሰውም፣ታክሲዎችም- ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ

መቅደላ ከተማ
ሰው- ከምሽቱ 2፡00 እስከ ጧቱ 12፡00 ድረስ
ተሽከርካሪ- ከምሽቱ 12፡ዐዐ እስከ ጧቱ 12፡ዐዐ
ለምግብና መጠጥ ቤቶች -ከምሽቱ 2፡00 በኋላ

ደብረ ብርሃን ከተማ
ለተሽከርካሪ - ከምሽቱ 2፡00 በኋላ
ለምግብና መጠጥ ቤቶች- ከምሽቱ 2፡00 በኋላ
ለተፈናቃይ- ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ ወደ ከተማዋም ወደ ጣቢያም መግባት ክልክል ነው።

ደባርቅ ከተማ
ለባጃጅ- ከምሽቱ 1፡00 በኋላ
ለተፈናቃይ- ከምሽቱ 12፡00 በኋላ ወደ ከተማውም ወደ ጣቢያም መግባት ክልክል ነው።

የሰዓት እላፊ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።

#SHARE #ሼር
@bbc_amharic1
5.9K views20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:44:14
ለአሸባሪው ህወሓት ሊተላለፍ የነበረ ከ1 ሚሊዮን በላይ ብር ተያዘ

ከስሃላ ወረዳ ወደ በየዳ ወረዳ በቅብብሎሽ ለሽብርተኛው ህወሓት ሊደርስ የነበረ 1 ሚሊዮን 253 ሺህ ብር መያዙን የተከዜ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ጀጃው ፈረደ ገልጸዋል።

አሸባሪው ቡድን ሰርጎ ገቦችን በማዘጋጀት ገንዘብ እና ቁሳቁስ እንዲሻገርለት ቢፈልግም በአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና በኅብረተሰቡ ጥብቅ ክትትል ዕቅዱ ከሽፏል ብለዋል።

ቡድኑ ሊጠቀምበት የነበረ 600 ሊትር አረቂ፣ 10 ጣቃ አቡጀዲ፣ 15 ሺህ 9 የሶላር መብራት እና ከአምስት ኩንታል በላይ ጨው እና መሰል ቁሳቁስ ከእነተጠርጣሪዎቹ መያዙን የአማራ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

@bbc_amharic1
10.0K views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:31:45 በኮምቦልቻ ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የከተማችን ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ሰፊው  ከመከረ በኋላ በቀጣዮቹ ነጥቦች ላይ ጥብቅ ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም በኮምቦልቻ ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብን ጨምሮ የተለያዩ ዉሳኔዎች ተላልፈዋል።

1ኛ የጠላትን ሀሳብና እንቅስቃሴ በመደገፍ አሉባልታ በማናፈስ በህብ ረተሰብ መካከል ሽብርና ውዥንብር በሚነዙ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ላይ በህግ እንዲጠየቁ ተወስኗል ።

2ኛ  በከተማ ደረጃ  አገልግሎት የምትሰጡ  ታክሲዎች እስከ  11 ሰዓት  ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ  ውሳኔ ተላልፏል ።

3ኛ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተንተርሶ የከተማችን ነዋሪ ላይ ያለ አግባብ ዋጋ ጭማሪ በማድረግ እና ሸቀጦችን በመከዘን በገበያ ላይ እጥረትን  በመፍጠር ነዋሪውን ለተጨማሪ ወጭና የኑሮ ጫና የሚጥሉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ  ይወሰዳል።

4ኛ ከወቅታዊ የጸጥታ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በምግብ ቤቶች በመጠጥ ቤቶች በካፌዎችና በግረሶሪዎች ላይ እስከ 11 ስዓት ጀምሮ ማንኛውም አገልግሎት መሰጠት የተከለከለ ነው።

5ኛ  የአልጋ አከራይ ሆቴሎዎች የመኖሪያ ቤትና የመደብ አከራዮች የተከራዩን ማንነት የሚገልጽ  መረጃ  በመያዝ  እንድታስገለግሉና በአቅራቢያችሁ ለሚገኝ የጸጥታ ተቋማት ጋር በቅርበት በመስራት የተከራዩን መታወቂያ ኮፒ በማድረግ  ጭምር የመሰጠት ግዴታ አለባችሁ።

6ኛ በከተማው አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ወይም  ድርጊቶች ጸጉረ ልውጥ ሰዎች አጠራጣሪ ተሽከርካሪዎች ወዘተ ሲታዩ  ለጸጥታ ተቋማት መጠቆም እንደሚገባ ተገልጿል።

7ኛ በከተማው ውስጥ የሚገኙ DSTV ማሳያ ቤቶች ፣የቡና መሸጫ ቤቶች ፣የሺሻና የጫት ማስቃሚያ ቤቶች ውስጥ ተሰብስቦ  ጫት መቃም በህግ ያስጠይቃል።

8ኛ  በማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም አላስፈላጊ ህዝብን ወደ አለመረጋጋት የሚወስዱ የተዛቡ መረጃዎችን መልቀቅ በህግ ያስጠይቃል።

9ኛ  የከተማችን የጸጥታ ኃይሎች ከመንግዜውም በላይ በመናበብ በመቀናጀት የተሰጣችሁን ኋላፊነት በብቃት በመወጣት  ህግ የማስከበር ሚናችሁን እንድትወጡ በጥብቅ እናሳስባለን። የከተማችን ነዋሪም በማህበራዊ ሚዲያዎች እና በበሬ ወለደ በሀሰተኛ በሚለቀቁ  መረጃዎች  ሳይደናገር እና አላስፈላጊ ውዦብር ውሰጥ ሳይገባ በተረጋጋና በሰከነ መልኩ መደበኛ ሰራችሁን እንድታከናውኑ ተገልጿል።

10ኛ ከተፈቀደላቸው የከተማችን የፀጥታ ኃይሎች ወጭ የጦር መሳሪያ ይዞ በቡድንም ሆነ በግል  ይዞ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።

11ኛ  መንግስት  ከሚሰራቸው የተቀናጀ ድጋፍ አሰባሰብ ስርዓት ውጭ ለመከላከያ ፣ ለልዩ ኃይል ድጋፍ በሚል ሰበብ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ግብዓቶችን ማሰባሰብ ፈጽሞ የተከለከለ ነዉ። ያለ ከተማ አስተዳደሩ ዕውቅና  በግልም ሆነ በቡድን ወደ ግንባር መንቀሳቀስ  የተከለከለ ነው።

13ኛ ማንኛውም ተቋማት ተሽርካሪዎችን  ለጸጥታ ሰራ በተፈለጉ ጊዜ የጸጥታ ተቋሙ ሲጠይቅ  ቀና ትብብር እንድታደርጉ ከተማ አስተዳዳሩ አሳስቧል።

14ኛ .ከዛሬ ነሀሴ 24/2014ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም የከተማችን ነዋሪ ከ11 ጀምሮ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። በቀጣይም የጸጥታ ምክር ቤቱ በየጊዜው የሚያወጣቸውን ውሳኔዎች እናሳውቃለን ሲል የከተማ መስተዳድሩ ማስታወቁን ብስራት ራዲዮ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

@bbc_amharic1
11.0K views13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 12:02:16
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለአንድ ደቂቃ 50 ሳንቲም የአገልግሎት በማስከፈል ላይ ይገኛል

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ውስጥ በ25 ከተሞች አገልግሎት እጀምራለሁ አለ።

ከሁለት ዓመት በፊት በወጣ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ጨረታ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በው ዕለት የመጀመሪያውን የደንበኞች የቴሌኮም አገልግሎቱን በድሬዳዋ አስጀምሯል።

ኩባንያው በመነሻ ኮዱ 07 በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች አካሂዷል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮች ለድሬዳዋ ደንበኞቹ በመሸጫ ሱቆች ይፋ ያደረገ ሲሆን ኔትወርኩን ለአንድ ወር የሚቆይ የሙከራ አገልግሎት ተጀምሯል።

ድርጅቱ የድምጽ አገልግሎቱን በደቂቃ ከሳፋሪ ኮም ስልክ ቁጥሮች ወደ ሳፋሪኮም እና ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርዶች በደቂቃ 50 ሳንቲም የሚያስከፍል ሲሆን ለኢንተርኔት ደግሞ በ10 ብር 120 ሜጋ ባይት፣ 900 ሜጋ ባይቱን በ50 ብር እንዲሁም ሁለት ጌጋ ባይት መጠን ያለውን ኢንተርኔት ደግሞ በ100 ብር ለ30 ቀናት በመደበኛነት በመሸጥ ላይ ነው።

ኩባንያው አክሎም እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ 2015 ድረስ ባሉት ስምንት ወራት ውስጥ በ25 የኢትዮጵያ ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደሚጀምር ለአልዓይን አስታውቋል።

አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ ኮምቦልቻ፣ ሀረር፣ አዳማ፣ ሀዋሳ፣ጅማ፣ ጅግጅጋ እና ሌሎች ከተሞች በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ውስጥ አገልግሎቶቹ ከሚጀመርባቸው አካባቢዎች ዋነኞቹ ናቸውም ተብሏል።

@bbc_amharic1
12.1K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:26:17
#ATTENTION

ሐይቅ !

የሐይቅ ከተማ አስተዳደርና የተሁለደሬ ወረዳ የጸጥታ ም/ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ፦

-  የባለ 3 እግር ተሽከርካሪና አነስተኛና መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።

- የመጠጥ ግሮሰሪዎች ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ተከልክሏል።

- ህግ ከሚያስከብሩ የጸጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- በየጫት ቤቱና መቃሚያ ቤቶች በማንኛውም ሰዓት መሰባሰብ፤ በነዚህ አካባቢዎች መቃምና መገኘት ተከልክሏል።

- ከጸጥታ ኃይሉ ውጭ በዘመቻ ሰበብ ከመንግስት እውቅና ውጭ ማንኛውንም ወታደራዊ አገልግሎት የሚሰጥ አልባሳት፣ ትጥቅ፣ የጦር መሳሪያና የመሳሰሉትን በማንኛውም ሰዓት በከተማው ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።

- ተፈናቅይም ሆነ ሌሎች ወደከተማው የሚገቡ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት በሚያገኙበት ተቋም ራሳቸውን የመግለፅ እንዲሁም ተቋማቱም መጠየቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

- በከተማው አሉባልታ መንዛት፣ ህዝቡን በማሸበር አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ፣ የግል ንብረት እና እቃ እንዲሰብሰብ ማነሳሳት በጥብቅ ተከልክሏል።

ነዋሪዎች ማንኛውም ጥቆማ ካላቸው በ 033 222 0481 ፣ 033 222 0955 ፣ 0333 222 0006 በመደወል መጠቆም ይችላሉ ተብሏል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)
@bbc_amharic1
12.2K views06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:24:21
ጠ/ሚ ዐቢይ በአልጄሪያ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው በአልጄሪያ ያደረጉትን የስራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

@bbc_amharic1
11.1K views06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:24:10
በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ በአዲስ አበባ መስተዳድር ስለተፈረሙ በከተማ መስተዳድሩ በጀት እና በአለም ባንክ ብድር የሚከናወኑ 3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ ስለሚደረግባቸው 3 የመንገድና የድልድይ ግንባታ የተመለከተ መረጃ ነው እነዚህም

1. የመጀመርያው ከአፍሪካ ጎዳና - ኤድናሞል አደባባይ - 22 ማዞሪያ - እንግሊዝ ኢምባሲ

2. ሁለተኛው የአየር ጤና - ወለቴ ሱቅ - አለም ገና አደባባይ

3. የአቃቂ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት ናቸው ።
ስለሚሰሩት መንገዶች ያለው እውነታ

• በአጠቃላይ ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው መንገድ ነው፡፡
• ከ15 - 30 ሜትር የጎን ስፋት ያላቸውን 3 የመንገድና የድልድይ ግንባታ ያካተተ ነው፡፡
• ለከተማዋ የመጀመሪያ የሆነውን Intelligent Transport System (ITS) ያካተተ ዲዛይን የተሰራለት ነው፡፡

• የትራፊክ ፍሰትና ቁጥጥር ስርዓቱን ለማዘመን በመከናወን ላይ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች አንዱ ነው፡፡
• ከ2.4 – 4 ሜትር ስፋት ያለው የእግረኛ መንገድ አለው፡፡
• 2 ሜትር ስፋት ያለው የብስክሌት ብቻ መሄጃ መንገድ አለው፡፡
• 9 የሳይክል ማቆሚያና 3 የሳይክል መከራያ ቦታዎች አሉት፡፡

• ዘመናዊ የመንገድ መሰረተ ልማትን ታሳቢ ያደረጉ የብልህ የትራንስፖርት ስርዓት አለው።
•10 የመንገድ መጋጠሚያዎች ላይ ሲሲቲቪ ካሜራዎች አሉት።
• 2 ቦታዎች ላይ ዲጂታል የትራፊክ መቁጠሪያዎች አሉት።
• ቅፅበታዊ የአውቶቡስ መረጃ ማግኛ ስርዓቶች አሉት።

• ኦፕቲክ ፋይበርና ዲጂታል ዋይፋይ ባክአፕ አለው።
• መዝናኛ ቦታ ተካቷል።
የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ ማሻሻያ
• የፈጣን አውቶብስ መስመር (BRT B-7) አካቷል፡፡
......................
@bbc_amharic1
12.1K views06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:03:47
#Haile_Hotels_and_Resorts

ሃይሌ ሪዞርት በአዲስ አበባ ያስገነባውን ባለ 5 ኮከብ ሆቴል በቅርቡ ያስመርቃል።

ሃይሌ ሪዞርት እና ሆቴሎች በአዲስ አበባ ላምበረት አካባቢ ያስገነባውን ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል በቅርቡ እንደሚያስመርቅ ተገልጿል።

ባለ ዘጠኝ ወለል ዘመናዊ ሕንጻ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል እንደሆነ የተነገረለት የሃይሌ ሪዞርት እና ሆቴል 8ኛ ሆቴል "ሃይሌ ግራንድ ሆቴል" ተብሎ እንደተሰየመ ተሰምቷል፡፡

ሆቴሉ 160 ምቹ የመኝታ ክፍሎች ፤ ስታንዳርድ እና ፕሬዝደንሺያል ተብለው የተለዩ ልዩ የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች ፤ የመዋኛ ገንዳ ፤ ጂምናዝየም ፤ ቅርጫት ኳስ ፤ የቤት ውስጥ እግር ኳስ ፤የጠረጴዛ ቴኒስ መጫወቻዎች እና የምሽት ክበብ አካቶ የያዘ ነው ፡፡

በተጨማሪም 300 መኪኖች የሚይዝ ፓርኪንግ በሕንጻው ምድር ክፍል ተገንብቶለታል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሰራተኞች ቅጥር እና ስልጠና በመካሔድ ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 በሃዋሳ አንድ ብሎ የመጀመሪያውን ሆቴል የከፈተው ሃይሌ ሪዞርት እና ሆቴሎች በቅርቡ በወላይታ ሶዶ ፤ ደ/ብርሃን እና ኮንሶ ተጨማሪ ሶስት ሆቴሎች እንደሚከፍት ታውቋል፡፡

በቀጣይ በጎርጎራ ከአንድ ቢሊየን ብር  በላይ ወጪ ልዩ የመዝናኛ ሆቴል እንደሚገነባ እና ሃይሌ ሪዞርት ዓለም አቀፍ ብራንድ በማድረግ በምስራቅ አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ አገሮች ሆቴሎች እና ሪዞርቶች የመገንባት እቅድ እንዳለው ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ

@bbc_amharic1
14.2K views14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:42:00
የህወሓት ታጣቂዎች በቆቦ ከተማ ንጹሃንን መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ!

ቆቦ ከተማን የተቆጣጠሩት የህወሓት ታጣቂዎች ንጹሃንን መግደላቸውን የራያ ቆቦ ወረዳ ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ ገለጹ።መንግስት የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ ሲባል የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን መልቀቁን መግለጹን ተከትሎ የህወሃት ታጣቂዎች በራያ ቆቦ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮችንና ወጣቶችን መገደላቸውን ነዋሪዎቹ ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል።

ለደህንነታቸውን ሲባል ድምጻቸውን ቀንሰው በስልክ ያነጋገሩን ግለሰብ፤ በከተማዋ ወጣቶች መገደላቸውን ተናግረዋል።በቆቦ ከተማ ስልክ ይዞ መገኘት እንደሚስገድል የተናገሩት አስተያየት ሰጭዋ፤ የተገደሉ ወጣቶች አስክሬን አሁንም አለመነሳቱን ተናግረዋል።አሁን ላይ በቆቦ ከተማ በተለያዩ መንገዶች ላይ የተገደሉ ወጣቶች አስክሬን እንዳለ የተናገሩት ደግሞ ሌላ አስተያየት ሰጭ ናቸው። አሁን ባለው ሁኔታ አስክሬን ማንሳት እንዳልተቻለ የተገለጸ ሲሆን አሁንም ውጊያ እንዳለ ተናግረዋል።

ወጣቶቹ እና አርሶ አደሮቹ “ፋኖ ናችሁ፤ የብልጽግና አባል ናችሁ፤ ሚሊሻ ናችሁ” በሚል ግድያ እየተፈጸመ እንደሆነ ገልጸዋል።በሮቢት ከተማ ብቻ ሁለት ወጣቶች መገደላቸውን ከስፍራው ወደ ወልዲያ የመጣ አንድ አስተያየት ሰጭ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግሯል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://am.al-ain.com/article/eye-witnesses-say-tplf-fighters-kills-civilian-in-kobo-town

@bbc_amharic1
14.0K views11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ