#ATTENTION
ሐይቅ !
የሐይቅ ከተማ አስተዳደርና የተሁለደሬ ወረዳ የጸጥታ ም/ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህም ፦
- የባለ 3 እግር ተሽከርካሪና አነስተኛና መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።
- የመጠጥ ግሮሰሪዎች ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ተከልክሏል።
- ህግ ከሚያስከብሩ የጸጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
- በየጫት ቤቱና መቃሚያ ቤቶች በማንኛውም ሰዓት መሰባሰብ፤ በነዚህ አካባቢዎች መቃምና መገኘት ተከልክሏል።
- ከጸጥታ ኃይሉ ውጭ በዘመቻ ሰበብ ከመንግስት እውቅና ውጭ ማንኛውንም ወታደራዊ አገልግሎት የሚሰጥ አልባሳት፣ ትጥቅ፣ የጦር መሳሪያና የመሳሰሉትን በማንኛውም ሰዓት በከተማው ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።
- ተፈናቅይም ሆነ ሌሎች ወደከተማው የሚገቡ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት በሚያገኙበት ተቋም ራሳቸውን የመግለፅ እንዲሁም ተቋማቱም መጠየቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
- በከተማው አሉባልታ መንዛት፣ ህዝቡን በማሸበር አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ፣ የግል ንብረት እና እቃ እንዲሰብሰብ ማነሳሳት በጥብቅ ተከልክሏል።
ነዋሪዎች ማንኛውም ጥቆማ ካላቸው በ 033 222 0481 ፣ 033 222 0955 ፣ 0333 222 0006 በመደወል መጠቆም ይችላሉ ተብሏል።
(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)
@
bbc_amharic1