Get Mystery Box with random crypto!

ለአሸባሪው ህወሓት ሊተላለፍ የነበረ ከ1 ሚሊዮን በላይ ብር ተያዘ ከስሃላ ወረዳ ወደ በየዳ ወረ | B B C News አማርኛ™

ለአሸባሪው ህወሓት ሊተላለፍ የነበረ ከ1 ሚሊዮን በላይ ብር ተያዘ

ከስሃላ ወረዳ ወደ በየዳ ወረዳ በቅብብሎሽ ለሽብርተኛው ህወሓት ሊደርስ የነበረ 1 ሚሊዮን 253 ሺህ ብር መያዙን የተከዜ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ጀጃው ፈረደ ገልጸዋል።

አሸባሪው ቡድን ሰርጎ ገቦችን በማዘጋጀት ገንዘብ እና ቁሳቁስ እንዲሻገርለት ቢፈልግም በአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና በኅብረተሰቡ ጥብቅ ክትትል ዕቅዱ ከሽፏል ብለዋል።

ቡድኑ ሊጠቀምበት የነበረ 600 ሊትር አረቂ፣ 10 ጣቃ አቡጀዲ፣ 15 ሺህ 9 የሶላር መብራት እና ከአምስት ኩንታል በላይ ጨው እና መሰል ቁሳቁስ ከእነተጠርጣሪዎቹ መያዙን የአማራ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

@bbc_amharic1