Get Mystery Box with random crypto!

በኮምቦልቻ ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት በወ | B B C News አማርኛ™

በኮምቦልቻ ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የከተማችን ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ሰፊው  ከመከረ በኋላ በቀጣዮቹ ነጥቦች ላይ ጥብቅ ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም በኮምቦልቻ ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብን ጨምሮ የተለያዩ ዉሳኔዎች ተላልፈዋል።

1ኛ የጠላትን ሀሳብና እንቅስቃሴ በመደገፍ አሉባልታ በማናፈስ በህብ ረተሰብ መካከል ሽብርና ውዥንብር በሚነዙ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ላይ በህግ እንዲጠየቁ ተወስኗል ።

2ኛ  በከተማ ደረጃ  አገልግሎት የምትሰጡ  ታክሲዎች እስከ  11 ሰዓት  ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ  ውሳኔ ተላልፏል ።

3ኛ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተንተርሶ የከተማችን ነዋሪ ላይ ያለ አግባብ ዋጋ ጭማሪ በማድረግ እና ሸቀጦችን በመከዘን በገበያ ላይ እጥረትን  በመፍጠር ነዋሪውን ለተጨማሪ ወጭና የኑሮ ጫና የሚጥሉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ  ይወሰዳል።

4ኛ ከወቅታዊ የጸጥታ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በምግብ ቤቶች በመጠጥ ቤቶች በካፌዎችና በግረሶሪዎች ላይ እስከ 11 ስዓት ጀምሮ ማንኛውም አገልግሎት መሰጠት የተከለከለ ነው።

5ኛ  የአልጋ አከራይ ሆቴሎዎች የመኖሪያ ቤትና የመደብ አከራዮች የተከራዩን ማንነት የሚገልጽ  መረጃ  በመያዝ  እንድታስገለግሉና በአቅራቢያችሁ ለሚገኝ የጸጥታ ተቋማት ጋር በቅርበት በመስራት የተከራዩን መታወቂያ ኮፒ በማድረግ  ጭምር የመሰጠት ግዴታ አለባችሁ።

6ኛ በከተማው አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ወይም  ድርጊቶች ጸጉረ ልውጥ ሰዎች አጠራጣሪ ተሽከርካሪዎች ወዘተ ሲታዩ  ለጸጥታ ተቋማት መጠቆም እንደሚገባ ተገልጿል።

7ኛ በከተማው ውስጥ የሚገኙ DSTV ማሳያ ቤቶች ፣የቡና መሸጫ ቤቶች ፣የሺሻና የጫት ማስቃሚያ ቤቶች ውስጥ ተሰብስቦ  ጫት መቃም በህግ ያስጠይቃል።

8ኛ  በማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም አላስፈላጊ ህዝብን ወደ አለመረጋጋት የሚወስዱ የተዛቡ መረጃዎችን መልቀቅ በህግ ያስጠይቃል።

9ኛ  የከተማችን የጸጥታ ኃይሎች ከመንግዜውም በላይ በመናበብ በመቀናጀት የተሰጣችሁን ኋላፊነት በብቃት በመወጣት  ህግ የማስከበር ሚናችሁን እንድትወጡ በጥብቅ እናሳስባለን። የከተማችን ነዋሪም በማህበራዊ ሚዲያዎች እና በበሬ ወለደ በሀሰተኛ በሚለቀቁ  መረጃዎች  ሳይደናገር እና አላስፈላጊ ውዦብር ውሰጥ ሳይገባ በተረጋጋና በሰከነ መልኩ መደበኛ ሰራችሁን እንድታከናውኑ ተገልጿል።

10ኛ ከተፈቀደላቸው የከተማችን የፀጥታ ኃይሎች ወጭ የጦር መሳሪያ ይዞ በቡድንም ሆነ በግል  ይዞ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።

11ኛ  መንግስት  ከሚሰራቸው የተቀናጀ ድጋፍ አሰባሰብ ስርዓት ውጭ ለመከላከያ ፣ ለልዩ ኃይል ድጋፍ በሚል ሰበብ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ግብዓቶችን ማሰባሰብ ፈጽሞ የተከለከለ ነዉ። ያለ ከተማ አስተዳደሩ ዕውቅና  በግልም ሆነ በቡድን ወደ ግንባር መንቀሳቀስ  የተከለከለ ነው።

13ኛ ማንኛውም ተቋማት ተሽርካሪዎችን  ለጸጥታ ሰራ በተፈለጉ ጊዜ የጸጥታ ተቋሙ ሲጠይቅ  ቀና ትብብር እንድታደርጉ ከተማ አስተዳዳሩ አሳስቧል።

14ኛ .ከዛሬ ነሀሴ 24/2014ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም የከተማችን ነዋሪ ከ11 ጀምሮ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። በቀጣይም የጸጥታ ምክር ቤቱ በየጊዜው የሚያወጣቸውን ውሳኔዎች እናሳውቃለን ሲል የከተማ መስተዳድሩ ማስታወቁን ብስራት ራዲዮ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

@bbc_amharic1