Get Mystery Box with random crypto!

ታዳጊዋ የ10,000.00 ዶላር ሽልማቷን ለብፁዕነታቸው አበረከተች! ** ይችን ድንቅ ብላቴና ሎዛ | B B C News አማርኛ™

ታዳጊዋ የ10,000.00 ዶላር ሽልማቷን ለብፁዕነታቸው አበረከተች!
**
ይችን ድንቅ ብላቴና ሎዛ ትባላለች። በትምህርቷ እጅግ ድንቅ ብቃት በማስመዝገቧ የ10ሺ ዶላር ሽልማት ትምህርት ቤቷ ይሸልማታል።

ልበ በርሀኗ ሎዛ በአሜሪካ በተለያዩ ከተሞች እየዞሩ ለፈረሰችው ወልድያ እና ላሊበላ ገንዘብ እየሰበሰቡ ለሚገኙት ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ቃል ገብታ ሰነበተች።

ታዲያ ዛሬ በቅዱስ ገብርኤል ዲሲ የተገኙት ብፁእነታቸው እዚህም በመሰብሰብ ላይ እያሉ ይች ትንሽዬ ብላቴና "ካለኝ ላይ ቀንሼ ሳይሆን የተሸለምኩትን ሙሉ ብር ይሄው እውቀቱን የሰጠኝ አምላክ ነው እሱ የሰጠኝን ለሱ" ብላ ሙሉውን ሰጠች።

የዘመኑ ሰው እንኳን ያለውን ካለው ላይ ማካፈል በማይፈልግበት በዚህ ዘመን ልበ ብርሀኑዋ ሎዛ ሙሉ የሽልማት ገንዘቧን ለግሳለች።

Via:- orthodox tewohido network
@bbc_amharic1