Get Mystery Box with random crypto!

B B C News አማርኛ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amharic1 — B B C News አማርኛ™ B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bbc_amharic1 — B B C News አማርኛ™
የሰርጥ አድራሻ: @bbc_amharic1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 62.41K
የሰርጥ መግለጫ

Broadcast & media production company
Addis Ababa, Ethiopia 🇪🇹

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-12 13:54:27
" ዕጣው ሙሉ ለሙሉ ተሰርዟል ብሎ መናገር አይቻልም " - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ተሰርዟል ብሎ መናገር አይቻልም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገለፀ።

የኮርፖሬሽኑ የሥራ ሀላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት " ዳታው ገብቶ ዕጣው ከወጣ በኋላ ያሉ ስህተቶች መኖራቸው ይታያል በተባለው መሰረት የተወሰኑ ክፍተቶች አሉ " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት የከተማ አስተዳደሩ ምን ሊወስን እንደሚችል አልታወቀም ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ሽመልስ ጉዳዩና ውሳኔው ዛሬ ሊታወቅ ይችላል ሲሉም ጠቁመዋል።

ባለፈው ሳምንት ዓርብ 25,491 ሰው ዕጣ ወጥቶለታል ያሉት አቶ ሽመልስ ፤ ስህተት የፈጠረው ሰው እንደተለየው ሁሉ በስህተቱ እድሉ የተፈጠረለት ማነው የሚለው ተለይቶ ወደ ሚቀጥለው ደረጃ የሚያሻግረው አማራጭ ይታያል ተብሎ እንደሚታመን አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበረው የተዝረከረከ አሰራር እንዳይኖር ቀድሞ ማጣራት ተደርጓል ያለው የቤቶች ኮርፖሬሽን ዳታው ከገባ እና ዕጣው ከወጣ በኋላ ያሉ ስህተቶች መኖራቸውን ገልጿል፤ ጉዳዩ እልባት ለማግኘት ተቃርቧል ሲልም አሳውቋል።

መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነው።
@bbc_amharic1
11.7K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 10:47:05 "ሸኔ እና ትሕነግ መጠነ ሰፊ ጥፋት እየፈፀሙብን ነው"

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ

አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ትሕነግ በአማራ ሕዝብ ላይ መጠነ ሰፊ ጥፋት እየፈጸሙ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ይህንን ያሉት ከሰሜን ሸዋ ዞን የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር ዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ እየተወያዩ ባሉበት ወቅት ነው።

በውይይቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ በርካታ ጥቃቶች እየተፈፀመበት ነው ያሉ ሲሆን ጥቃቱን ማክሸፍ የሚቻለው በመደማመጥና በመተባበር ብቻ ነው ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ከውስጥም ከውጭም እየደረሱ ያሉ ጫናዎችን ለመቋቋም በሰከነ መንገድ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ያወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ "ሸኔ እና ትሕነግ መጠነ ሰፊ ጥፋት እየፈፀሙብን ነው" ብለዋል፡፡

ይህን መጠነ ሰፊ ጥቃትና ጥፋት የሚያቀናብሩትንና በክልሉ ውስጥም ከክልሉ ውጭም ባሉ አካባቢዎች እያደረሱት ያለውን የጥፋት አጀንዳ ለማክሸፍ ጠንካራ መንግሥታዊ መዋቅር መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት ይህንን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እየሠራን ነው ብለዋል።

በክልሉ ውስጥ ለአብነት ከሰሞኑ በአጣዬና አካባቢው የደረሰው ጥቃት በተደጋጋሚ ረፍት ለመንሳት የሽብር ቡድኖች የጠነሰሱልን ሴራ አካል ነው ተብለዋል።

አሚኮ
@bbc_amharic1
11.5K views07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 08:21:50
የባለ እድሎች ስም ዝርዝር እስካሁን አልተለቀቀም!

“የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት እጣ ባለ እድሎች ስም ዝርዝር እስካሁን አልተለቀቀም” የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለኢትዮጵያ ቼክ

በዛሬዉ እለት የ40/60 ባለ ሁለት እና ሶስት መኝታ ቤት ባለ እድለኞች ስም ዝርዝር የሚል ፋይል (PDF) በተለይም በፌስቡክ እንዲሁም በቴሌግራም ግሩፖችና ቻነሎች አማካኝነት ሲሰራጭ ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራትን ያናገረ ሲሆን “እኛ ኦፊሺያሊ አልለቀቅንም” ብለዋል። በተጨማሪም “ዌብሳይት ላይ እንለቃለን፤ ጋዜጣም እናትማለን ብለናል። ነገር ግን ያልተጠናቀቁ ስራዎች ስላሉ እስካሁን አልለቀቅንም። በየቦታዉ እኛም እንደናንተዉ እንሰማለን። ትክክል አይደለም” ብለዋል

ምንጭ ፣ ኢትዮጵያ ቼክ
@bbc_amharic1
12.3K views05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:47:37 በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ከትናንት ጀምሮ በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች እና ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደተቀሰቀሰ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። በግጭቱ የሰው ሕይወት እንደጠፋና ንብረቶች እንደወደሙ የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል። ግጭቱ የተፈጠረው ከአጣዬ ከተማ ወጣ ብለው በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ነው። ወደ ገጠር ቀበሌዎች ገብቶ ከመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ የገባው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እንደሆኑ የዓይን ምስክሮች ገልጸዋል።

Via:- Wazema
@bbc_amharic1
13.4K views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 16:27:41
ተቋርጦ የነበረው የአውሮፕላን በረራ በአብዛኛው መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ጸባይ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የአውሮፕላን በረራ በአብዛኛው መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታዉቋል፡፡

አየር መንገዱ ለጥቂት ሰአታት በአዲስ አበባ የነበረው ጭጋጋማ የአየር ፀባይ መሻሻል ማሳየቱን ጠቁሟል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉና ከኢትዮጵያ የሚነሱ በረራዎች በአብዛኛው መጀመራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

@bbc_amharic1
13.6K views13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 14:54:36
" በፀጥታ አጠባበቁ ላይ ችግሮች እንደነበሩ መካድ አይቻልም " - ፖሊስ

የጃፓን ፖሊስ ባለፈው ዓርብ በደቡባዊቷ ናራ ከተማ የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ግድያ በተፈጸመበት ወቅት የፀጥታ ጥበቃ ክፍተቶች እንደነበሩ ገልጿጻ።

የናራ ፖሊስ አዛዥ ቶሞአኪ ኦኒዙካ ፤ " በፀጥታ አጠባበቁ ላይ ችግሮች እንደነበሩ መካድ አይቻልም " ሲሉ ተናግረዋል።

ተፈጥረዋል ያሏቸውን ክፍተቶች የት ላይ እንደሆኑ ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

በሺንዞ አቤ ላይ ግድያውን በመፈጸም የተጠረጠረው የ41 ዓመቱ ቴሱያ ያማጋሚ አንድ በስም ያልተጠቀሰ ተቋም ላይ ቂም ይዞ ነበር ሲል ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

የጃፓን የመገናኛ ብዙኃን ፤ ለምርመራው ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገቡት ከሆነ ተጠርጣሪው ወላጅ እናቱን የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ከከተተ አንድ የሃይማኖት ቡድን ጋር ሺንዞ አቤ ግንኙነት አላቸው ብሎ ያምናል።

ፖሊስ በተጠርጣሪውና በክስተቱ ላይ ጥልቅ ምርመራ እያካሄደ ይገኛል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።
@bbc_amharic1
12.4K views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 14:27:35
ባለፉት 12 ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበው ቡና 1.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ!

ኢትዮጵያ ባለፉት 12 ወራት ለውጭ ገበያ ካቀረበችው የቡና ምርት 1.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቷን የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን ገለጹ።

ይህ ገቢ የተገኘው ወደ ውጭ ከተላከው 300 ሺህ ቶን የቡና ምርት መሆኑን ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።
በዚህ ዓመት የተገኘው ገቢ በዓመት በአማካይ ይገኝ ከነበረው ገቢ ጋር ሲነጻጸር የ500 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱንም አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ይህ ግብ እንዲሳካ ላደረጉ የቡና አምራቾች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

@bbc_amharic1
11.1K views11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 13:54:14
ፋሲል ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ቅጣት ተላለፈባቸው

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርና ሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ ሲያያቸው በነበሩ ሁለት ጉዳዮች ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ አሳልፏል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ ረቡዕ ሰኔ 29/2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት በመመርመር እንዲሁም በኮሙኒኬ 30 ጥሪ የተደረገላቸው የጨዋታ አመራሮች እና የክለብ አባላት ጥሪ በማድረግ ካነጋገር በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ድሬዳዋ እግር ኳስ ክለብ ክለቡ ከባሕርዳር ጋር በነበረው የ28ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ግጥሚያው ከተጠናቀቀ በኋላ የክለቡ ደጋፊዎችና የቡድን አመራሮች አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦበታል፡፡

የክለቡ ደጋፊዎችና የቡድን አመራሮች በዕለቱ ባጠፉት ጥፋትና ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጥፋት ከተቀጡት ቅጣትም ሊታረሙ ባለመቻላቸው ክለቡ 75 ሺሕ እንዲከፍል መወሰኑን ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በነበረው የ30ኛ ሳምንት ጨዋታ ከ68ኛው ደቂቃ ጀምሮ ስፖርታዊ ጨዋነትን ያልተከተለ ድጋፍ ስለመስጠታቸው እና ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የጥበቃ ኃይሎች ሊቆጣጠሩት ባልቻለ ሁኔታ ወደ መጫወቻ ሜዳ ጥሰው ስለመግባታቸውና ስለማወካቸው እንዲሁም ለሜዳሊያ አስጣጥ ሥነ-ሥርዓት አፈጻጸም እንቅፋት ስለመሆናቸው ሪፖርት ቀርቦበታል። በዚህም ክለቡ 100 ሺሕ እንዲከፍልና በሜዳው የሚጫወተውን ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ያለደጋፊ በዝግ ስታዲየም እንዲያደርግ ተወስኗል።

@bbc_amharic1
11.4K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ