Get Mystery Box with random crypto!

'ሸኔ እና ትሕነግ መጠነ ሰፊ ጥፋት እየፈፀሙብን ነው' ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ | B B C News አማርኛ™

"ሸኔ እና ትሕነግ መጠነ ሰፊ ጥፋት እየፈፀሙብን ነው"

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ

አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ትሕነግ በአማራ ሕዝብ ላይ መጠነ ሰፊ ጥፋት እየፈጸሙ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ይህንን ያሉት ከሰሜን ሸዋ ዞን የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር ዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ እየተወያዩ ባሉበት ወቅት ነው።

በውይይቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ በርካታ ጥቃቶች እየተፈፀመበት ነው ያሉ ሲሆን ጥቃቱን ማክሸፍ የሚቻለው በመደማመጥና በመተባበር ብቻ ነው ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ከውስጥም ከውጭም እየደረሱ ያሉ ጫናዎችን ለመቋቋም በሰከነ መንገድ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ያወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ "ሸኔ እና ትሕነግ መጠነ ሰፊ ጥፋት እየፈፀሙብን ነው" ብለዋል፡፡

ይህን መጠነ ሰፊ ጥቃትና ጥፋት የሚያቀናብሩትንና በክልሉ ውስጥም ከክልሉ ውጭም ባሉ አካባቢዎች እያደረሱት ያለውን የጥፋት አጀንዳ ለማክሸፍ ጠንካራ መንግሥታዊ መዋቅር መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት ይህንን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እየሠራን ነው ብለዋል።

በክልሉ ውስጥ ለአብነት ከሰሞኑ በአጣዬና አካባቢው የደረሰው ጥቃት በተደጋጋሚ ረፍት ለመንሳት የሽብር ቡድኖች የጠነሰሱልን ሴራ አካል ነው ተብለዋል።

አሚኮ
@bbc_amharic1