Get Mystery Box with random crypto!

የባለ እድሎች ስም ዝርዝር እስካሁን አልተለቀቀም! “የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት እጣ | B B C News አማርኛ™

የባለ እድሎች ስም ዝርዝር እስካሁን አልተለቀቀም!

“የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት እጣ ባለ እድሎች ስም ዝርዝር እስካሁን አልተለቀቀም” የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለኢትዮጵያ ቼክ

በዛሬዉ እለት የ40/60 ባለ ሁለት እና ሶስት መኝታ ቤት ባለ እድለኞች ስም ዝርዝር የሚል ፋይል (PDF) በተለይም በፌስቡክ እንዲሁም በቴሌግራም ግሩፖችና ቻነሎች አማካኝነት ሲሰራጭ ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራትን ያናገረ ሲሆን “እኛ ኦፊሺያሊ አልለቀቅንም” ብለዋል። በተጨማሪም “ዌብሳይት ላይ እንለቃለን፤ ጋዜጣም እናትማለን ብለናል። ነገር ግን ያልተጠናቀቁ ስራዎች ስላሉ እስካሁን አልለቀቅንም። በየቦታዉ እኛም እንደናንተዉ እንሰማለን። ትክክል አይደለም” ብለዋል

ምንጭ ፣ ኢትዮጵያ ቼክ
@bbc_amharic1