Get Mystery Box with random crypto!

' በፀጥታ አጠባበቁ ላይ ችግሮች እንደነበሩ መካድ አይቻልም ' - ፖሊስ የጃፓን ፖሊስ ባለፈው ዓ | B B C News አማርኛ™

" በፀጥታ አጠባበቁ ላይ ችግሮች እንደነበሩ መካድ አይቻልም " - ፖሊስ

የጃፓን ፖሊስ ባለፈው ዓርብ በደቡባዊቷ ናራ ከተማ የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ግድያ በተፈጸመበት ወቅት የፀጥታ ጥበቃ ክፍተቶች እንደነበሩ ገልጿጻ።

የናራ ፖሊስ አዛዥ ቶሞአኪ ኦኒዙካ ፤ " በፀጥታ አጠባበቁ ላይ ችግሮች እንደነበሩ መካድ አይቻልም " ሲሉ ተናግረዋል።

ተፈጥረዋል ያሏቸውን ክፍተቶች የት ላይ እንደሆኑ ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

በሺንዞ አቤ ላይ ግድያውን በመፈጸም የተጠረጠረው የ41 ዓመቱ ቴሱያ ያማጋሚ አንድ በስም ያልተጠቀሰ ተቋም ላይ ቂም ይዞ ነበር ሲል ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

የጃፓን የመገናኛ ብዙኃን ፤ ለምርመራው ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገቡት ከሆነ ተጠርጣሪው ወላጅ እናቱን የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ከከተተ አንድ የሃይማኖት ቡድን ጋር ሺንዞ አቤ ግንኙነት አላቸው ብሎ ያምናል።

ፖሊስ በተጠርጣሪውና በክስተቱ ላይ ጥልቅ ምርመራ እያካሄደ ይገኛል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።
@bbc_amharic1