Get Mystery Box with random crypto!

ባለፉት 12 ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበው ቡና 1.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ! ኢትዮጵያ | B B C News አማርኛ™

ባለፉት 12 ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበው ቡና 1.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ!

ኢትዮጵያ ባለፉት 12 ወራት ለውጭ ገበያ ካቀረበችው የቡና ምርት 1.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቷን የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን ገለጹ።

ይህ ገቢ የተገኘው ወደ ውጭ ከተላከው 300 ሺህ ቶን የቡና ምርት መሆኑን ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።
በዚህ ዓመት የተገኘው ገቢ በዓመት በአማካይ ይገኝ ከነበረው ገቢ ጋር ሲነጻጸር የ500 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱንም አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ይህ ግብ እንዲሳካ ላደረጉ የቡና አምራቾች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

@bbc_amharic1