Get Mystery Box with random crypto!

ፋሲል ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ቅጣት ተላለፈባቸው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርና ሥነ-ሥርዓት | B B C News አማርኛ™

ፋሲል ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ቅጣት ተላለፈባቸው

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርና ሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ ሲያያቸው በነበሩ ሁለት ጉዳዮች ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ አሳልፏል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ ረቡዕ ሰኔ 29/2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት በመመርመር እንዲሁም በኮሙኒኬ 30 ጥሪ የተደረገላቸው የጨዋታ አመራሮች እና የክለብ አባላት ጥሪ በማድረግ ካነጋገር በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ድሬዳዋ እግር ኳስ ክለብ ክለቡ ከባሕርዳር ጋር በነበረው የ28ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ግጥሚያው ከተጠናቀቀ በኋላ የክለቡ ደጋፊዎችና የቡድን አመራሮች አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦበታል፡፡

የክለቡ ደጋፊዎችና የቡድን አመራሮች በዕለቱ ባጠፉት ጥፋትና ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጥፋት ከተቀጡት ቅጣትም ሊታረሙ ባለመቻላቸው ክለቡ 75 ሺሕ እንዲከፍል መወሰኑን ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በነበረው የ30ኛ ሳምንት ጨዋታ ከ68ኛው ደቂቃ ጀምሮ ስፖርታዊ ጨዋነትን ያልተከተለ ድጋፍ ስለመስጠታቸው እና ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የጥበቃ ኃይሎች ሊቆጣጠሩት ባልቻለ ሁኔታ ወደ መጫወቻ ሜዳ ጥሰው ስለመግባታቸውና ስለማወካቸው እንዲሁም ለሜዳሊያ አስጣጥ ሥነ-ሥርዓት አፈጻጸም እንቅፋት ስለመሆናቸው ሪፖርት ቀርቦበታል። በዚህም ክለቡ 100 ሺሕ እንዲከፍልና በሜዳው የሚጫወተውን ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ያለደጋፊ በዝግ ስታዲየም እንዲያደርግ ተወስኗል።

@bbc_amharic1