Get Mystery Box with random crypto!

Ayu zehabesha

የቴሌግራም ቻናል አርማ ayuzehabesha — Ayu zehabesha A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ayuzehabesha — Ayu zehabesha
የሰርጥ አድራሻ: @ayuzehabesha
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 139
የሰርጥ መግለጫ

@abretp

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-09-04 16:51:13 አላማጣ ላይ አየር ሀይል ከሰዓታት በፊት እርምጃ ወስዷል።
11.9K viewsAyu, edited  13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 14:24:43
አድዐርቃይ ወረዳ
ለአሥራ ሦስት ወራት በህወሓት ታጣቂዎች ግፍና መከራ ሲፈፀምባቸው የነበሩት እና ላቅ ያለ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸው የሰሜን ጎንደር የአዳርቃይ ወረዳ ቀበሌዎች ነፃ እየወጡ ነው። ሐዋዛ ህወሓት በርካታ ታጣቂዎች አስፍሮበት የነበረ ዛሬ ነፃ ከወጡት ቀበሌዎች አንዱ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎች ይኖራሉ፣ የቻናሌ ቤተሰብ በመሆን ተከታተሉ
http://t.me/ayuzehabesha http://t.me/ayuzehabesha
26.4K viewsAyu, edited  11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 14:10:04 አሁናዊ መረጃ
ሰቆጣ ግንባር
ሰቆጣ ከተማ ሰላም ነው።
በሰቆጣ በወለህ ውቅር እሚባል ቦታ ላይ ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ይገኛል።
በዚህ ግንባር የተሰለፉ የህወሓት ታጣቂዎች ብዛት በጣም ብዙ እንደሆነ ታውቋል።
የህዝቡ ደጀንነት በቃላት የሚገለፅ አይደለም፣ቡና ሳይቀር ለሰራዊቱ ግንባር ድረስ በመውሰድ እያበረታቱ ይገኛሉ።
ራያ ግንባር
በግዳን በኩል በተኩለሽ፣በቀይአፈር እና በድኖ አሁን ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ነው።
በአላውሃ ማዶ በባቡር መንገዱ እና በአስፋልቱ መካከል ካለው ሜዳ ላይ እና ተራራ ላይ ከፍተኛ ውጊያ አለ።
በወርቄ በኩል አሁንም ድረስ የሞት የሽረት ትግል እያደረገ ይገኛል።
በራያ ግንባር የህወሓት ታጣቂዎች ማጥቃት ላይ ሳይሆን መከላከል ላይ ያተኮረ ስራ ነው በአብዛኛው እየሰሩ ያሉት። ሙሉ ማጥቃት ደግሞ በሰቆጣ በኩል አድርገው እየተንቀሳቀሱ ነው።
ሁኔታው በየሰዓቱ ስለሚለዋወጥ ያለውን ነገር ለማድረስ በቻልኩት እጥራለሁ።
አዩ ዘሀበሻ
ነሃሴ 29/2014 ዓ.ም
ሰዓት ከቀኑ:- 8:10
የውስጥ መስመር @ayulaw
ተጨማሪ መረጃዎች ይኖራሉ፣ የቻናሌ ቤተሰብ በመሆን ተከታተሉ
http://t.me/ayuzehabesha http://t.me/ayuzehabesha
27.1K viewsAyu, edited  11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 12:52:47 የህወሃት ታጣቂ ቁስለኛ በከፍተኛ ሁኔታ ከመብዛቱ የተነሳ በመሆኒ፣ በአዲጉደም፣ በኩሃ አካባቢ በገጠር ት/ቤቶች እና ጤና ኬላዎች ላይ ህዝቡ በጨው እና በባህላዊ ህክምና ቁስለኛውን እያከመ እንደሚገኝ የወጣው መረጃ ይጠቁማል።
ተጨማሪ መረጃዎች ይኖራሉ፣ የቻናሌ ቤተሰብ በመሆን ተከታተሉ
http://t.me/ayuzehabesha http://t.me/ayuzehabesha
30.2K viewsAyu, edited  09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 11:47:56
በምዕራብ ግንባር (ወልቃይት) ሸረሪና፣ ነጭ ድንጋይ፣ በረከት በተደረገ ጦርነት የሀገር መከላከያ የህወሃትን ተጨማሪ አምስት ምሽጎች ሰብሮ መቆጣጠሩን ሰማሁ!
በተከዜ ወንዝ ዳርቻ በተካሄደው በዚሁ ጦርነት ከመከላከያ ሰራዊቱ ጥይት የተረፈው ታጣቂ ወደ ኋላ ሲሸሽ ድልድዩን ሰብሮታልና ተከዜን ለማቋረጥ ሲሞክሩ በውሃው መወሰዳቸውም ታውቋል። በሱዳን የሚገኙ የጁንታው ታጣቂዎችና አመራሮች ተከዜ የተፋቸውን አስከሬን እየሰበሰቡ እንደሆነ ታውቋል።
በዚህም ቀደም ሲል እንዳደረጉት ወራሪዎቹን "ተገለው ወንዝ ውስጥ የተጣሉ ንፁሃን" በማለት ሊጠቀምባቸው መሆኑ ተገምቷል።
ይህን ቀድመን ልናከስመው የተገባ የጁንታው ሴራ ነው ማለት ነው።
ህወሃት ሲሸሽ ያንጠባጠባቸው መገናኛዎችም ተይዘዋል። በምስሉ የሚታየው የጁንታው ባለሁለት አቅጣጫ Two way communique መገናኛ ከሀገረ እንግልጣር/እንግሊዝ የተደረገ ድጋፍ እንደሚሆን ይገመታል።
#የዓባይልጅ
ተጨማሪ መረጃዎች ይኖራሉ፣ የቻናሌ ቤተሰብ በመሆን ተከታተሉ
http://t.me/ayuzehabesha http://t.me/ayuzehabesha
32.5K viewsAyu, edited  08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 10:41:03
የዋግኽምራ ዞን የጋዝጊብላ ወረዳ ህዝብ ገደል፣ አቀበት፣ ቁልቁለት፣ ድካም ሳይበግራቸው ከደጀንነታችን ምንም ነገር የሚያግደን የለም በማለት የህወሃትን ታጣቂ በየሸለቆውና ተራራው ለሚቀጠቅጠው ጀብደኛው የመከላከያ ሰራዊት: ሚሊሻና ፋኖ ስንቅ ምሽግ ድረስ በማቀበል ደጀንነቱን እያረጋገጠ ይገኛል።
ወጣቶቹ ታሪካዊ ጠላታችን የሆነው ትህነግ እስኪደመሰስ ከእኛ የሚጠበቀውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ለጥምር ጦራችን በየትኛውም ቦታ ገብተን ስንቅና ትጥቅ እያቀረብን እንገኛለን ከዚህም ባሻገር ግንባር ገብተን እንዋጋለን በማለት ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል።
ወጣቶቹ ደጅንነታችን ወሰን የለውም አቀበት: ቁልቁለት ገደል: ውጣ ውረዱ ሁሉም አይበግረንም ተግባራችን ከዚህ በላይ አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት በድጋሜ ደጀንነታቸውን አረጋግጠዋል።
                      አስከተማ
ፎቶ ከወረዳው ኮሙኒኬሽን
ተጨማሪ መረጃዎች ይኖራሉ፣ የቻናሌ ቤተሰብ በመሆን ተከታተሉ
http://t.me/ayuzehabesha http://t.me/ayuzehabesha
33.2K viewsAyu, 07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 10:24:55
የምስራቅ አምሓራ ፋኖ እና የቤተ አምሓራ ፋኖ አንድ ላይ ለመታገል በግንባር ላይ ውይይት አደረጉ።
የትህነግ ወራሪ ቡድን በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን የህልውና ጦርነት ለመመከት ብሎም ለመቀልበስ የምስራቅ አምሓራ ፋኖ ዋና አዛዥ ሻለቃ ምሬ ወዳጆና የቤተ አምሓራ ፋኖ ዋና አዛዥ ሻለቃ ሰለሞን አራጋው በተገኙበት ግንባር ካለው ሰራዊት ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ላይ ከተነሱት ሀሳቦች በዋናነት እንደ አምሓራ የገጠመንን የህልውና አደጋ እንደከዚህ ቀደሙ ጠላት በህዝባችን ላይ የከፋ አደጋና ጉዳት ሳያስከትል ሁላችንም የጋራ ግንባር ፈጥረን ትግላችንን እንቀጥላለን ብለዋል።
ስለሆነም እንደ አምሓራ ሁሉም ሰው በሚችለውና በአቅሙ ልክ ከጎናችን በመሆን በህዝባችንና በሀገራችን ላይ የተከፈተውን የህልውና ጦርነት ከህዝባችን ጋር በመሆን እናሸንፋለን ሲሉም አክለዋል።
በተጨማሪም የምስራቅ አምሓራ ፋኖና ከቤተ አምሓራ ፋኖ ጋር ማንኛውንም የግንባር ላይ ትግል የጠላትን ሴራና ፕሮፓጋንዳ በማክሸፍ በኩል ስራዎችን የጋራ በማድረግና በመናበብ መስራት እንደሚጠበቅባቸው በውይይቱ ላይ ለተገኘው የፋኖ ሰራዊት አባል መልእክት አስተላልፈዋል።
ተጨማሪ መረጃዎች ይኖራሉ፣ የቻናሌ ቤተሰብ በመሆን ተከታተሉ
http://t.me/ayuzehabesha http://t.me/ayuzehabesha
32.8K viewsAyu, edited  07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 09:29:32 በግንባር ከሚገኙ የፀጥታ አካላት በስልክ ያገኘሁት መረጃ
ሰቆጣ በአስተማማኝ ሁኔታ እየተጠበቀች ሲሆን፣
መከላከያ ህዝቡን በማረጋጋት እረገድ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል።
ጥሩ ወታደራዊ ጥምረት እንዳለ እና መልካም ነገሮች አሉ(ወታደራዊ መረጃዎች በዝርዝር ስለማይነገሩ ነው)።
ማታ ወለህ ወረዳ ውስጥ ከተፈናቃዮች ጋር ተደባልቀው የነበሩ የህወሓት ታጣቂዎች ሸሽተዋል።
በእርግጥ ወራሪው ሀይል አሁንም ከሰቆጣ ከተማ በቅርብ እርቀት በሚገኙ ሀሙሲት:ትያ እና ወለህ ማሪያም በሚባሉ ቦታዎች ሰለሚገኝ ሙሉ በሙሉ ከሰጋት ነፃ ሁናለች ለማለት ባያሰደፍርም ለጊዜው ግን ከተማዋ በወገን ጦር እጅ ነች:ስለዚህ ጠላት ሰቆጣን ተቆጣጥሪያለሁ በማለት የሚያሰራጨው መረጃ ነጭ ውሸት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል::
ጎብዬ፣ሮቢት፣ተኩለሽ የህወሓት ታጣቂዎች ለሊቱን የት እንደሄዱ አይታወቅም፣ ምንም አይነት የተኩስ ድምፅ አይሰማም(ነፃ ወጥተዋል አልወጡም ለማለት አያስደፍርም)
በግዳን ትናንት በጥቁር ውሃ ሰዱቅ ተራራ ላይ የነበረው ከፍተኛ ውጊያ አሁን ጋብ ብሎ ጥምር ጦሩ ጥሩ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለቸው ቦታዎችን እንደተቆጣጠረ ለማወቅ ችያለሁ።
በወርቄ በኩል ጥሩ ዜና አብስረውኛል።
ለአሁኑ ያለኝ መረጃ ይሄ ነው ቀጣይ...... ይጠብቁኝ
አዩ ዘሀበሻ
ነሃሴ 29/2014 ዓ.ም
ሰዓት ከጠዋቱ 3:29
35.0K viewsAyu, edited  06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 07:18:17 ከሰቆጣ በስልክ
"መንገድ ጀምሮ የነበረው ህዝብ አሁን እየተመለሰ ነው ወደ ሰቆጣ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም። መከላከያ የማረጋጋት ስራ እየሰራ ነው አዩ እኔ አልወጣሁም ምክንያቱም የመከላከያ ሀይል ወታደራዊ ብቃት በቅርብ እያየን ስለሆነ እኔ አልወጣሁም"።
ከሰቆጣ አንዱ ወዳጄ ጋር አሁን ደውዬ ያገኘሁት መረጃ ነው።
አዩ ዘሀበሻ
ተጨማሪ መረጃዎች ይኖራሉ፣ የቻናሌ ቤተሰብ በመሆን ተከታተሉ
http://t.me/ayuzehabesha
37.9K viewsAyu, edited  04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 22:14:16 የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ እየተዘዋወሩ በሞንታርቮ ህዝቡ ተረጋግቶ እምዲቀመጥ መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ። በአካባቢው የነበረው የተኩስ ድምጽ ጋብ ያለ ሲሆን የህወሓት ታጣቂዎች ወደ ኋላ (ቲያ የሚባል ቦታ) ሲያፈገፍጉ አይቀርም ብለዋል።
====================
ስለጦርነቱ ፈጣን መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ
http://t.me/ayuzehabesha    http://t.me/ayuzehabesha
http://t.me/ayuzehabesha   http://t.me/ayuzehabesha
በውሸት አካውንት እንዳትሸወዱ
9.9K viewsAyu, edited  19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ