2022-09-02 12:09:32
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የተላለፈ ውሳኔ
ለመላው የጎንደር ህዝብ ለሶስተኛ ዙር አገራችን ለማፈራረስ ወራሪዉ ሃይል ጦርነት ለኩሷል ፡፡
ስለሆነም አሁን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የጎንደር ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡
ጥምር ጦራችን በሁሉም ግንባር በሙሉ ብቃትና ወኔ ጠላትን እየመከተ እየደመሰሰ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የጎንደር ከተማ አስተዳደርና የፀጥታ ምክር ቤት ማህበረሰባችን ራሱን ማዘጋጀትና የከተማችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል
የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡
1. ከፀጥታ መዋቅሩ ውጭ፣ በከተማችን በብሎክ አደረጃጀት አካባቢን እንዲጠብቅ በተሰጠው ተራው ከተሰማራው ውጭ በየትኛውም ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፡፡
2. ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጭ የተለያዩ የፀጥታ አካላት አልባሳትን መልበስ የተከለከለ ነው፡፡
3. ማህበረሰቡን የሚያውኩ አሉባልታዎች ወይም የሃሰት መረጃዎችን በተለያዩ ሚዲያዎች፣ በመጠጥ ቤቶች ወዘተ ማሰራጨት ህዝቡን ማወዛገብ ማሰጨነቅ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
4. በከተማችን የሚገኙ ተፈናቃዮች ከተሰጣቸው መጠለያ ካምፕ ውጭ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን ለገበያ፣ ለህክምና፣ ለአንገብጋቢ ጉዳዮች፣ ለተለያዩ ስራዎች ከመጠለያው መውጣት ያለበት ተፈናቃይ በሚመለከታቸው የካምፕ አስተባባሪዎችና በክ/ከተማው የፀጥታ መዋቅር እውቅና እና የመውጫና የመግቢያ ፈቃድ መለያ ካርድ ይዞ ተመዝግቦ ተፈቅዶለት የሚንቀሳቀስ ይሆናል፡፡
5. በተለያዩ አሉባልታ ወሬዎችና ስበብ በመፈለግ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ባንክ ቤት፣ ሱቆችና ሆቴሎች፣ የገበያ ማዕከሎች እና የመሳሰሉትን መዝጋት የተከለከለ ነው፡፡
6. ማንኛውም የግል ሆነ የመንግስት ተሸከርካሪ ለፀጥታ ስራ ሆነ ለዘመቻ የሠው ሃይል ለማንቀሳቀስ በሚመለከታቸው የዘመቻ ማምሪያ ኮማንድ ፖስት ትብብር ሲጠየቅ የመተባበር ግዴታ አለበት ላለመተባበር ተሸከርካሪን የሚሸሽግ፣ የሚያሸሽ ሆን ብሎ ተበላሸ በሚል ላለመተባበር ጥረት የሚያደርግ ተጠያቂና የጥፋት ኃይሎች ተባባሪ ተደርጎ ስለሚቆጠር ከዚህ አይነት ጥፋት በመቆጠብ ኃላፊነትን መወጣት ይገባል፡፡
7. ማንኛውም የቤት አከራይ ወይም አልጋ የሚያከራይ፣ ሆቴሎች፣ ፔንሲዮኖች ተከራዮቻቸውን እና ተጠቃሚዎቻቸውን የመለየትና ማንነታቸውን የመለየት፣ የታደሰ ህጋዊ መታወቂያ ስለመኖራቸው የማረጋገጥ ግዴታ እና አስፈላጊውን መረጃ ይዞ ለጸጥታ አካል ሪፖርት የማድረግ ኃላፊነትና ግዴታ አለበት
8. ማንኛውም ሰው ፀጉረ ልውጥ ሰው ሲያጋጥመው በቅርብ ለሚገኝ የፀጥታ አካል የመጠቆም ኃላፊነት አለበት
9. ከነሀሴ 27/2014 ዓ.ም ጀምሮ የቀበሌ መታወቂያ መስጠት የተከለከለ ሲሆን አስቸኳይ የሆነ ጉዳይ የገጠመው ለምሳሌ ለህክምና መታወቂያ ቢያስፈልግ፣ ወደ ዩኒቨርስቲ ለመሄድ ቢያስፈልግ፣ ወደ ውጭ አገር የሚያስፈልግ ጉዞ የመሳሰሉት አስቸኳይ ጉዳዮች ከገጠሙና መታወቂያ መስጠት ካስፈለገ የክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚና የክ/ከተማው ሰላምና ደህንነት በጋራ በማየት መታወቂያ የመስጠት ፈቃድ ሊሰጡ ይችላሉ
10. ማንኛውም የመንግስት የግል ታጣቂ አካባቢውን በብሎክ አደረጃጀት ውስጥ በመካተት በየደረጃው ያለ የፀጥታ አካላት በሚሰጠው ስምሪት አካባቢውን የመጠበቅ ኃላፊነት ግዴታ አለበት
11. አግባብነት የሌለው የዋጋ ንረት የሚፈጥሩ በሸቀጦች በግብርና ምርቶች ላይ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ጨምሮ ህዝቡን ማስቃየት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
12. ከከተማ ውጭ ወደ ከተማው ለጸጥታ ስራ፣ ሆነ የጦር ,መሳሪያ ይዞ ወደ ከተማው መግባት አስፈላጊ ለሆኑ ስራዎች የሚንቀሳቀስ ማንኛውም አካል ለስራ ከተላከበት አካባቢ ከሚመለከተው የፀጥታ አካል የይለፍ ደብዳቤና መታወቂያ መያዝ ግዴታ አለበት
13. ወቅታዊ ሁኔታውን እንደምቹ ሁኔታ ተጠቅሞ በህገ ወጥ ስራዎች፣ በህገ ወጥ ግንባታ መሰማራት ከወራሪው ኃይል ያልተለየ ጥፋት ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን በመገንዘብ ከዚህ አይነት ጥፋት ማንኛውም ሰው መቆጠብ አለበት
14. በጫት ቤቶች ተሰብስቦ በመቃም አሉባልታና ሽብር መንዛት የተከለከለ ነው
15. ተገቢ ያልሆነ ምክኒያት የሌለዉ የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ በህዝቡ ላይ ሌላ ጫና መፍጠር በመሆኑ ክዚሀ ብፊተ የከተማዉ ምክር ቤት የወሰነዉ ዉሳኔ በቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር ክልከላዉ እንደተጠበቀ የሚቀጥል ይሆናል
በአጠቃላይ የጎንደር ህዝብ ወራሪ ኃይሉን ለመመከትና ለመደምሰስ በሚደረገው ዘመቻ ከመቸውም ጊዜ በላይ አንድ በመሆን በግንባር በመዝመት፣ አካባቢን በመጠበቅ በሎጀስቲክ በማሰባሰብ ህዝባችን እንዲሳተፍ የፀጥታ ም/ቤቱ ጥሪ እያቀረበ ከላይ የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች ማንኛውም አካል የማክበርና ኃላፊነቱን የመወጣት ግዴታ ያለበት መሆኑንና ይህን ውሳኔ የማያከበር የፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል በአጽእኖት ያሳውቃል፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት
ነሀሴ 27/2014 ዓ.ም
ጎንደር፣
==================
ስለጦርነቱ ቶሎ ቶሎ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
http://t.me/ayuzehabesha http://t.me/ayuzehabesha
http://t.me/ayuzehabesha http://t.me/ayuzehabesha
"በውሸት አካውንት እንዳትሸወዱ
21.5K viewsAyu, edited 09:09