Get Mystery Box with random crypto!

Ayu zehabesha

የቴሌግራም ቻናል አርማ ayuzehabesha — Ayu zehabesha A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ayuzehabesha — Ayu zehabesha
የሰርጥ አድራሻ: @ayuzehabesha
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 139
የሰርጥ መግለጫ

@abretp

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 16

2022-07-14 20:50:36 #በጋምቤላ የሰዓት ገደብ ተጣለ
በጋምቤላ ከተማ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ሕገወጥ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የሰዓት እላፊ ተጥሎ እንደነበር ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ለማህበረሰቡ ደህንነት ታስቦ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ክፍተት መታየቱን ተገልጿል።

በዙህም በከተማው የሰዎች እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴን በመለየት ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11፡30 ድረስ የተጣለው ገደብ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል ተብሏል።

ከአንቡላንስና ከፀጥታ ሀይል ተሽከርካሪ በስተቀር ማንኛውም ተሽከርካሪና ሰዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ከንጋቱ 11፡30 እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት መሆኑ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በአሁኑ ወቅት በጋምቤላ ከተማ ሰላማዊ ሁኔታ መኖሩ የተገለፀ ሲሆን በየደረጃው የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች የተጠናከረ ጥበቃ እያደረጉ ነው ተብሏል።
ህብረተሰቡ በየአካባቢው ተደራጅቶ መረጃ በመስጠት እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
======================
ማሳሰቢያ
የውሸት አካውንት የከፈቱ ስላሉ እንዳትሸወዱ፣ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ ይሄ ብቻ ነው t.me/ayuzehabesha
"መረጃ ህይወት ነው"
9.6K viewsAyu, edited  17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:26:36
#ጣሊያን
#Ethiopia
የጣሊያኑ ጠ/ሚ ማሪዮ ደርጌሂ ስልጣናቸውን ለቀቁ, የራሺያና የዩክሬን ጉዳይ በአውሮፓ ሀገራት ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል። በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜም ዩሮ ከዶላር በታች መሆኑ አውሮፓ ለገባችበት ችግር አንዱ ማሳያ ነው። አሜሪካም የምትፈልገው እሱን ነው። ለአሜሪካ ሲሉ ራሺያ ላይ ሲረባረቡ የነበሩ ሀገራት ለራሳቸው ችግር ውስጥ ገብተዋል።
======================
ማሳሰቢያ
የውሸት አካውንት የከፈቱ ስላሉ እንዳትሸወዱ፣ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ ይሄ ብቻ ነው t.me/ayuzehabesha
"መረጃ ህይወት ነው"
10.6K viewsAyu, edited  17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 19:54:21
ኢትዮጵያ ሱዳን
ቁጥራቸው 4 የሚደርሱ የኢትዮጵያ አውሮፕላኖች በጉምና በጭጋግ ምክንያት ቦሌ ማረፍ ባለመቻላቸው ሱዳን ካርቱም ኤርፖርት ለማረፍ ተገደዋል። አዲስአበባ ያለው ጭጋግ ለፓይለቶቹ ከ800 ሜትር ርቀት ላይ መሬት ማየት ካልቻሉ ማረፍ ስለማይፈቀድላቸው ነው ተብሏል።
ማስታወቂያ ማሰራት ለምትፈልጉ፣ በዚች ሊንክ አሳውቁኝ @ayulaw
======================
ማሳሰቢያ
የውሸት አካውንት የከፈቱ ስላሉ እንዳትሸወዱ፣ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ ይሄ ብቻ ነው t.me/ayuzehabesha
"መረጃ ህይወት ነው"
11.9K viewsAyu, edited  16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 19:35:27 #Update
በድጋሚ ዛሬ በትግራይ ክልል ለ20 ደቂቃ ያህል ሞባይል ኔትወርክና ዳታ ለሙከራ ተለቆ እንደነበር ታውቋል። ምናልባት በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ሊለቀቅ ይችላል።
አዩ ዘ ሀበሻ
======================
ማሳሰቢያ
የውሸት አካውንት የከፈቱ ስላሉ እንዳትሸወዱ፣ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ ይሄ ብቻ ነው t.me/ayuzehabesha
"መረጃ ህይወት ነው"
12.2K viewsAyu, edited  16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 17:44:58
#Update
#አባይ በረሃ
በድንጋይ ናዳ መንሸራተት ምክንያት ተዘግቶ የነበረዉ መንገድ ተከፍቷል።
አባይ በርሃ ከኩራር ከተማ ከፍ ብሎ አርባቶንሳ ቤተክርስቲያን አካባቢና በተለምዶ ማንይንገስ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ የድንጋይ ናዳ አስፋልቱን መዝጋቱን መግለጻችን ይታወሳል።
ይሁን እንጅ የደጀን ወረዳ በፍጥነት ድንጋይ የሚያነሳ መኪና በማቅረቡና በተሳፋሪዎች ርብርብ ድንጋዩን በማንሳት መንገዱ ለተሽከርካሪዎች ክፍት ሆኗል።
አዩ ዘ ሀበሻ
======================
ማሳሰቢያ
የውሸት አካውንት የከፈቱ ስላሉ እንዳትሸወዱ፣ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ ይሄ ብቻ ነው t.me/ayuzehabesha
"መረጃ ህይወት ነው"
14.8K viewsAyu, 14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 17:39:01 መረጃ
የህውሃት ወራሪ ቡድን በሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ 022 ወትወት ቀበሌ ሃምሌ 02/2014 በአንድ ትንሽ መንደር ዘልቆ በመግባት የቁም እንሰሳት መዝረፉንና ሰዎችን አፍኖ መውሰዱን መዘገባችን ይታወቃል።
አንድ የቀበሌው ሚልሻ አባል ያደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ወረራውን ያካሄዱት ለሁለት ተከታታይ ቀን እንደሆነ አስረድቶ፦ በወረራውም 14 በሬ እና በርካታ ቁጥር ያለው ፍየል እንደወሰዱ ተናግሯል ፤ ሁለት ወጣት ልጆችንም አፍነው እንደወሰዱ እና ልጆቹን ለማስለቀቅ ለእያንዳንዳቸው ከ250 ሽህ ብር በላይ ሰለጠየቁን አሁን ልጆቹን ለማስለቀቅ ህብረተሰቡ ብር እያሰባሰበ መሆኑን ነው የገለፀልነው።
የአካባቢው ሚልሻና አርሶ አደር ምንም ዓይነት ትንኮሳ እንዳያደርግ እና ምንም ዓይነት የመሳሪያ ተኮስ ድምፅ እንዳያሰማ በመከላከያ በኩል ጥብቅ መለዕክት በመተላለፉ ዝርፊያውን መከላከል አልቻልነም ሲል አዝኖና ተስፋ በመቁረጥ ተናግሯል።
አዩ ዘ ሀበሻ
======================
ማሳሰቢያ
የውሸት አካውንት የከፈቱ ስላሉ እንዳትሸወዱ፣ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ ይሄ ብቻ ነው t.me/ayuzehabesha
"መረጃ ህይወት ነው"
14.8K viewsAyu, edited  14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 16:08:03
ከትናንቱ መረጃዬ በተጨማሪ
በምስራቅ ሸዋ ዞን በቦሰት ወረዳ ቆምቤ ጉግሳ ቀበሌ ሰሞኑን በተደረገ የተቀናጀ ኦፕሬሽን እየተሽሎከሎኩ ንፁሀን ዜጎች ላይ ጥቃት ለመፈፀም በቡድን ተደራጅተው ሲንቀሳቀስ በነበሩ የሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወሠዷል።

የአሸባሪው ሸኔ ሽፍቶችን በማሳደድ ላይ ከሚገኙ የሠራዊታችን ክፍሎች መካከል የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይል ሲሆን በኮማንዶ ክፍል ጦር የሠራዊት አዛዥ እንደተናገሩት የአሸባሪው ህወሓት ተላላኪ የሆነው የሸኔ አባላት በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት ሊፈፅሙ ሲንቀሳቀሱ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
በዚህ ኦፕሬሽን 5 ኤኬሜ (የክላሽ ) ጠብመንጃ፣ 2 የእጅ ቦንብ፣ 200 የክላሽ ጥይት፣ 164 የብሬን ጥይት ከነሸንሸሉ፣ 4 የወገብ ትጥቅ እና 12 የክላሽ ጠብመንጃ መጋዘን ከአሸባሪው ሸኔ እጅ መማረኩንም አዛዡ ገልፀዋል፡፡
ትናንት እንደዘገብኩት ይሄንን ኦፕሬሽን ለማከናወን መከላከያ ሰራዊቱ ከ50/60 ኪሎ ሜትር በእግር ተጉዟል። ክብር ለመከላከያ ሰራዊት
======================
ማሳሰቢያ
የውሸት አካውንት የከፈቱ ስላሉ እንዳትሸወዱ፣ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ ይሄ ብቻ ነው t.me/ayuzehabesha
"መረጃ ህይወት ነው"
16.4K viewsAyu, edited  13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 14:50:17
#Fias777
በኦንላይን እንደ Fias 777፣HDU በሚባሉ ፕላትፎርሞች ገንዘባቸውን የተጭበረበሩ አካላት የፌዴራል ፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። ነገር ግን የፌደራል ፖሊስ በ991 እና 987 ይደወሉ ተብሎ የተሰጠን ስልክ ላይ ስንደውል ስልካቸው ምንም ሊሰራልን አልቻለም የሚል ተደጋጋሚ ጥቆማዎች እየመጡ ነው። ቢስተካከል ለማለት ነው።
አዩ ዘ ሀበሻ
======================
ማሳሰቢያ
የውሸት አካውንት የከፈቱ ስላሉ እንዳትሸወዱ፣ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ ይሄ ብቻ ነው t.me/ayuzehabesha
"መረጃ ህይወት ነው"
16.7K viewsAyu, edited  11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 14:26:21
ከአባይ በርሃ የደረሰኝ ጥቆማ
አባይ በርሃ ላይ ሁለት ቦታዎች ላይ የድንጋይ ናዳ መንገዱን በመዝጋቱ በመንገደኞች ላይ እንግልት እየፈጠረ ነዉ።
አባይ በርሃ ከኩራር ከተማ ከፍ ብሎ አርባቶንሳ ቤተክርስቲያን አካባቢና በተለምዶ ማንይንገስ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ የድንጋይ ናዳ አስፋልቱን በመዝጋቱ መንገደኞች ለማለፍ ተቸግረዋል።
ተሳፋሪዎች ድንጋይ ለማንሳት ባደረጉት ጥረት ትናንሽ መኪኖች ማለፍ ጀምረዋል። አውቶብሶች ለማለፍ ተሳፋሪዎች ድንጋይ እያነሱ ነዉ።
ስለሆነም አዉራ ጎዳና ወቅቱ ክረምት በመሆኑ የድንጋይ ማንሻ መኪኖችን በመላክ ችግሩን እንዲፈታ እያሳሰብን ለማለፍ በሚደረግ ጥረት አደጋ እንዳይፈጠር የትራፊክ ፖሊሶች የተለመደ ትብብር ቢያደርጉ መልካም ነው ሲሉ ተሳፋሪዎች መልዕክታቸውን አድርሰውኛል።
ሀምሌ 07/2014 ዓ.ም
አሁንም ጥቆማ፣አስተያየት እና መረጃ ከላዎት በዚች ሊንክ ፃፉልኝ @ayulaw
አመሰግናለሁ
======================
ማሳሰቢያ
የውሸት አካውንት የከፈቱ ስላሉ እንዳትሸወዱ፣ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ ይሄ ብቻ ነው t.me/ayuzehabesha
"መረጃ ህይወት ነው"
16.7K viewsAyu, edited  11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 14:16:48 መረጃ
ከሰሜኑ ክፍል ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ መንገደኞች የአዲስ አበባ መታወቂያ የያዘ ብቻ ነው ወደ አዲስ አበባ መግባት የሚችለው በማለት ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ወከባ እየተደረገብን ነው ብለዋል። በዚህም የተነሳ አሌልቱ እና በኬ ላይ በርካታ ተሳፋሪዎች እየተጉላሉ ይገኛሉ። ይሄ ለምን እንደሚደረግ መንግሥት ግልፅ መረጃ አለመስጠቱ አበሳጭቷቸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግለፅ መረጃ በመስጠት አሁን ለሚጉላሉትም ቀጣይ ለሚጓዙትም አቅጣጫ መስጠት አለበት። በጣም አሳፋሪ ተግባር ነው።
ሀምሌ 07/2014 ዓ.ም
======================
ማሳሰቢያ
የውሸት አካውንት የከፈቱ ስላሉ እንዳትሸወዱ፣ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ ይሄ ብቻ ነው t.me/ayuzehabesha
"መረጃ ህይወት ነው"
16.3K viewsAyu, edited  11:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ