Get Mystery Box with random crypto!

ATC UEE PREPARATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ atc_uee — ATC UEE PREPARATION A
የቴሌግራም ቻናል አርማ atc_uee — ATC UEE PREPARATION
የሰርጥ አድራሻ: @atc_uee
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.25K

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-02 19:18:05
ስለ ውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ከሰሞኑ የወጡ መረጃዎች፦


° ከእስያና ከአውሮፓ ሀገራት ጋር የስምምነት ሥራዎችን ተጀምረዋል።

° የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን ጭምር በማሰልጠን ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነወ።

° ዜጎች ስራው ካልተመቻቸው መጥፋት ሳያስፈልጋቸው ይቀየርልን የሚሉበትን አሰራር ተዘርግቷል።

° ዜጎች ለፓስፖርት፣ ለጤና ምርመራ ለአሻራ ከሚከፍሉት ውጪ የሚያወጡት ወጪ የለም።

° ባለፉው ዘጠኝ ወራት ስድስት ሚሊዮን ዜጎች በሥራ ፈላጊነት ተመዝግበዋል።

° ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን የውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች ከሚኒስቴሩ ድረ-ገጽ መመልከት ይቻላል።

° በውጪ ሃገር የሥራ እድል ላይ መመዝገብ የሚቻለው በዲጂታል አማራጭ ብቻ ነው።


፨ክፍያውን ማን ይሸፍናል?

"የትኬት እና የኢንሹራነስ ወጪን የሚከፍሉት የመዳረሻ ሀገር ላይ ያሉ አሰሪዎች ናቸው ከዜጎች የሚጠበቀው የፓስፖርት እና የጤና ምርመራ በተወሰነ ደረጃ የአሻራ ከዛ ውጪ ዜጎች የሚያወጡት ወጪ የለም አንዳንድ ህገወጦች ግን ከ60-80 ሺህ ይቀበላሉ ዜጎች መብታቸውን አውቀው አውቀው ሊጠነቀቁ ይገባል" ሲሉም ገልጸዋል።

ለመመዝገብ ይህን ፎርም ይሙሉ
https://www.lmis.gov.et

ኦንላይን ፎርም አሞላሉን የሚያሳይ የቪዲዮ ማብራሪያ






፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
915 views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 14:08:31

ባሳለፍነው ቅዳሜ ማለትም በቀን #21/08/2015 ከጥዋቱ 1፡50 ላይ በእንጅባራ ዩንቨርሲቲ በተምዶ ኪዳነምህረት መግቢያ በመባል በሚታወቀው በር በኩል የዩንቨርሲቲው የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት ተማሪ የሆነችው ተማሪ ኤደን ገብሩ ከቤተክርስቲያን መልስ የግቢ መታወቂያ ( ID Card ) አለመያዟን ተከትሎ ከዩንቨርሲቲው ተረኛ የጥበቃ ሠራተኞች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በደረሰባት አካላዊ ጥቃት ምክንያት በአሁኑ ሰዓት ተማሪዋ ከባድ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ በርካታ የእንጅባራ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ጥቆማ አድርሰውናል።

ይህንን ጥቆማ በመቀበል ጉዳዩን ለማረጋገጥ ጉዳት የደረሰባት ተማሪ ጋር እንዲሁም የዩንቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረትን አናግረናል።


<ተማሪ ኤደን ገብሩ ጋር በደወልንበት ጊዜ ተማሪዋ በስልክ ለማውራት አቅም ስላጠራት አጠገቧ ከነበሩት ጓደኞቿ ነው መረጃውን ያገኘነው>

ጉዳት በደረሰባት ተማሪ የእጅ ስልክ ደውለን ያገኘነውን መረጃ በአጭሩ ለመግለፅ

[ተማሪዋ ወደ ቤተክርስትያን ስትሄድ የግቢ መታወቂያ ትረሳለች። ወደ ግቢ ስትመለስ የግቢ መታወቂያ እንዳልያዘች በመንገር በመመገቢያ ካርድ ያስገቧት ዘንድ የጥበቃ ሠራተኞችን ስትጠይቅ አንዱ ጥበቃ ይገፈትራታል። አትገፍትረኝ ብላ እጁን ለማስለቀቅ ስትሞክር በጥፊ ይመታታል። ለምን በጥፊ ትመታኛለህ ስትለው በድጋሚ ገፍትሮ ጥሎ ጭኗ አካባቢ ይረግጣታል። ጭኗ አካባቢ የረገጣት ህመም ሲበረታባት ሌሌች ጥበቃዎች ጣልቃ ገብተው ወደ ግቢ እንድትገባ ይፈቅዱላታል። ዶርም ገብታ መታወቂያዋን ይዛ ክስ ለመመስረት ዲሲፕሊን ቢሮ ሄዳ ሰኞ ትመለስ ዘንድ ነግረዋት ከቢሮ ስትወጣ ራሷን ሳተች።አሁን ላይ ማህፀኗ አካባቢ የተቋጠረ ደም እንዳለ እንደተነገራትና ህመሙ ምናልባትም ቀዶ ህክምና ሊያስፈልገው እንደሚችል በእጅ ስልኳ መረጃ የሰጡን ከጎኗ ያሉ ጓደኞቿ ነግረውናል። ጓደኞቿ በተጨማሪ እንደነገሩን ከሆነ ተማሪዋ ሽንት ለመሽናትና ለመንቀሳቀስ እጅጉን እየተቸገረች እንደሆነ ገልፀው ዩንቨርሲቲው ጉዳዩን አለባብሶ ለማለፍ እንዳይሞክር ድምፅ እንሆንላት ዘንድ ጠይቀዋል።]


ይህን ጉዳይ በተመለከተ የእንጅባራ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዘዳንት የሰጠን ምላሽ

ዩንቨርሲቲው መረጃው የደረሰው ቢሆንም ጉዳዩ በመጣራት ሂደት ላይ እንዳለ ፕሬዝዳንቱ ነግረውናል።አሁን ላይ ተማሪዋ የህክምና እርዳታ እያገኘች እንዳለ ገልፀው የህመሟን ምክንያት ማለትም ተማሪዋ ያቀረበችውን ምክንያት በተጨማሪም ራሷን ስታ በምትወድቅበት ጊዜ የመታት ነገር መኖር አለመኖሩን የባለሙያ ማረጋገጫ እንደሚያስፈልግና እንደ ፀጥታም መጠየቅ ያለባቸው ነገሮች በመኖራቸው ጉዳዩን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እያጣሩ እንደሚገኙና በሚናፈሱ ወሬዎች ላይ ብቻ ተመስርቶ የግል አስተያየት መስጠት እንደማይገባ ገልፀውልናል።


፨የተማሪ ኤደን ገብሩን ጉዳይ በተመለከተ የሚኖሩ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
1.3K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 14:08:31
1.2K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 10:26:54
wollo university
freshiman program dean office

remedial student mid exam schedule

የሪሜድያል ተማሪዎች የmid-exam ፕሮግራም
2.6K views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 10:52:45
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሚያስተምሩ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ለአራት ቀን የሚቆይ ውይይት በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።

ውይይቱ በዛሬው እለት በ77 ክላስተሮች 63,470 መምህራን እና የትምህርት አመራሮችን ተሳታፊ በማድረግ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በዛሬው እለት ውይይቱን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸው በውይይቱ 1,368 ቡድኖች ከመደራጀታቸው ባሻገር 2,736 አወያዮች መመደባቸውን አስታውቀዋል።

ውይይቱ በዋናነት ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት ያስመዘገበቻቸውን ውጤቶችና በሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መሰረት በማድረግ የሚካሄድ መሆኑን ዶክተር ዘላለም ገልጸው ለትምህርት ልማት ስራው ውጤታማነት መምህራንም ሆኑ የትምህርት አመራሮች የአንበሳውን ድርሻ እንደመውሰዳቸው የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የተማሪዎችን ውጤት እና ስነምግባር ለማሻሻል ውይይቱ የጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት መሆኑንም አስረድተዋል።

ውይይቱ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀን በክላስተር ደረጃ ተካሂዶ እሁድ እለት ከየትምህርት ቤቱ ከተውጣጡ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ጋር በየክፍለከተማው ተመሳሳይ ውይይት ከመካሄዱ ባሻገር እሁድ 500 የሚሆኑ መምህራን በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ ታላላቅ የልማት ስራዎችን የሚጎበኙበት መርሀ ግብር መዘጋጀቱን ኃላፊው ጠቁመው ሰኞ ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም በከተማ ደረጃ የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት 5,000 ከሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።



@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
2.2K views07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 17:58:07
"የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል":- ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶችና ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱም የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

ፈተናው ልክ እንደባለፈው ዓመት በኹለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን አብራርተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በ2016 የሚካሄደው ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸው የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
2.0K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 12:36:52
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ ነገ ይጠናቀቃል

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ ነገ ሚያዚያ. 20/2015 ዓም ከቀኑ 11:30 ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታዉቋል።

እስካሁን ያልተመዘገቡ ተፈታኝ ተማሪዎች እስከ ነገ እንዲመዘገቡ አገልግሎቱ ማሳሰቡን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል። በማንኛውም ምክኒያት ያልተመዘገቡ ተፈታኞችንም አገልግሎቱ ከነገ በኋላ የማያስተናግድ መሆኑን አሳስቧል።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
2.4K views09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 10:15:18
ዘመኑ ከፍቷል ወገን

ሚስት ለአንድ ዩትዩበር ብር ከፍላ ባሏን እሷ በሌለችበት ሰዓት በካሜራ የታገዘ ክትትል ይደረግላት ዘንድ ታዛለች። ዩትዩበሩም ስራዬ ነው ብሎ በድብቅ ካሜራ ባልን ይከታተላል።

አቶ ባል ሚስት በሌለችበት የሰፈሩ ሴት ልጅ ጋር በር ዘግተናል ብለው በነፃነት አሸሸ ገዳሜ ይላሌ።መርፌና ክሩን ሳይቀር ድብቁ ካሜራ በመያዝ ለሚስት ሪፖርት ያቀርባል።

ሚስት ጥርጣሬ አድሮባት ባሏን በዚህ መልኩ በተደጋጋሚ ታሰልላለች። የሆነ ቀን ላይ ዩትዩበሩ ለሚስት ሆዬ ነይ በአካል ጉድሽን ተመልከች ብሎ ወደ ቤቷ ተያይዘው ይሄዳሉ። በር ከፍታ ስትገባ አቶ ባል ቅምጧን የሆነ ቦታ ወሽቆ ቢለዋ ይዞ ወጥ እንደመስራት ተፍ ተፍ ይላል። ሚስት እርርር ትክን ብላ ሁሉንም ነገር እንደምታውቅ ብትነግረውም ራቀቱን በመሆን ለሷ ምግብ እየሰራላት እንደሆነ በመንገር ግግም ይላል።

በኋላም ዩትዩበሩ ድብቅ ካሜራዎቹ ያሉበትን ቦታ እና እያንዳንዱን ነገር እንዳዩ ይነግረዋል። ሙሉ ክስተቱን በዚህ ሊንክ

በኩል መመልከት ትችላላቹህ።

===================

ሁላችንም ፈጣሪ ሸፍኖልን እንጂ ብዙ ነውሮች አሉብን። ሰውን በዚህ ልክ እየተከታተሉ እንጀራ መብላት ለኔ ደስ አይልም።ፈጣሪም የሰውን ነውር እንከታተል ዘንድ አልሾመንም።የዩትዩበሩ ስራ ከላይ ሲታይ ጥሩ ነገር ቢመስልም በኔ ምልክታ ግን ልክ አይደለም።ቢያንስ የቀረፀውን ቪዲዮ ለጉዳዩ ባለቤት ብቻ ቢያሳይና ቪድዮውን ከምድረ ገፅ ቢያጠፋው ከዚያም ባልና ሚስት ለችግራቸው መፍትሄ ቢያበጁ ይሻላል ነኝ።(ከሆነ እንኳን)

ሚስትዬዋን በተመለከተ ምንም ማለት አልፈልግም። ልክም ናት ተሳስታለችም ማለት ይከብደኛል።

ይህንን ቪዲዮ ያያቹህ ወይም ታሪኩ በከፊል የገባቹህ ሰዎች በዚህ ጉዳይ ምን ትላላቹህ?
2.5K views07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 12:29:58
#Update

ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ለአምስት ቀናት ተራዝሟል።

ምዝገባው ከመጋቢት 20/2015 ዓ.ም ጀምሮ በኦንላይን ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል።

የተፈታኞቹ ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንደሚካሄድ የትምህትርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ከሚያዚያ 20/2015 ዓ.ም በኋላ በግለሰብም ሆነ በተቋም የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን #የማያስተናግድ መሆኑን አገልግሎቱ አሳስቧል።

በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ2015 ትምህርት ዘመን ፈተና የመፈተኛ ጊዜን ከምዝገባው መጠናቀቀ በኋላ የሚገለጽ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
1.8K views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 10:21:41
ቴሌግራም ላይ ቪዲዮው ቶሎ ዳውንሎድ ለማድረግ
2.1K viewsedited  07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ