Get Mystery Box with random crypto!

ዘመኑ ከፍቷል ወገን ሚስት ለአንድ ዩትዩበር ብር ከፍላ ባሏን እሷ በሌለችበት ሰዓት በካሜራ የታ | ATC UEE PREPARATION

ዘመኑ ከፍቷል ወገን

ሚስት ለአንድ ዩትዩበር ብር ከፍላ ባሏን እሷ በሌለችበት ሰዓት በካሜራ የታገዘ ክትትል ይደረግላት ዘንድ ታዛለች። ዩትዩበሩም ስራዬ ነው ብሎ በድብቅ ካሜራ ባልን ይከታተላል።

አቶ ባል ሚስት በሌለችበት የሰፈሩ ሴት ልጅ ጋር በር ዘግተናል ብለው በነፃነት አሸሸ ገዳሜ ይላሌ።መርፌና ክሩን ሳይቀር ድብቁ ካሜራ በመያዝ ለሚስት ሪፖርት ያቀርባል።

ሚስት ጥርጣሬ አድሮባት ባሏን በዚህ መልኩ በተደጋጋሚ ታሰልላለች። የሆነ ቀን ላይ ዩትዩበሩ ለሚስት ሆዬ ነይ በአካል ጉድሽን ተመልከች ብሎ ወደ ቤቷ ተያይዘው ይሄዳሉ። በር ከፍታ ስትገባ አቶ ባል ቅምጧን የሆነ ቦታ ወሽቆ ቢለዋ ይዞ ወጥ እንደመስራት ተፍ ተፍ ይላል። ሚስት እርርር ትክን ብላ ሁሉንም ነገር እንደምታውቅ ብትነግረውም ራቀቱን በመሆን ለሷ ምግብ እየሰራላት እንደሆነ በመንገር ግግም ይላል።

በኋላም ዩትዩበሩ ድብቅ ካሜራዎቹ ያሉበትን ቦታ እና እያንዳንዱን ነገር እንዳዩ ይነግረዋል። ሙሉ ክስተቱን በዚህ ሊንክ

በኩል መመልከት ትችላላቹህ።

===================

ሁላችንም ፈጣሪ ሸፍኖልን እንጂ ብዙ ነውሮች አሉብን። ሰውን በዚህ ልክ እየተከታተሉ እንጀራ መብላት ለኔ ደስ አይልም።ፈጣሪም የሰውን ነውር እንከታተል ዘንድ አልሾመንም።የዩትዩበሩ ስራ ከላይ ሲታይ ጥሩ ነገር ቢመስልም በኔ ምልክታ ግን ልክ አይደለም።ቢያንስ የቀረፀውን ቪዲዮ ለጉዳዩ ባለቤት ብቻ ቢያሳይና ቪድዮውን ከምድረ ገፅ ቢያጠፋው ከዚያም ባልና ሚስት ለችግራቸው መፍትሄ ቢያበጁ ይሻላል ነኝ።(ከሆነ እንኳን)

ሚስትዬዋን በተመለከተ ምንም ማለት አልፈልግም። ልክም ናት ተሳስታለችም ማለት ይከብደኛል።

ይህንን ቪዲዮ ያያቹህ ወይም ታሪኩ በከፊል የገባቹህ ሰዎች በዚህ ጉዳይ ምን ትላላቹህ?