Get Mystery Box with random crypto!

ATC UEE PREPARATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ atc_uee — ATC UEE PREPARATION A
የቴሌግራም ቻናል አርማ atc_uee — ATC UEE PREPARATION
የሰርጥ አድራሻ: @atc_uee
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.25K

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-07 18:31:15
1.7K views15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 20:16:32
መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለቅድመ ዩኒቨርሲቲ አቅም ማሻሻያ የተመደቡ ተማሪዎችን ውጤታማ ለማዲረግ እየሰራ ነው፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተለያዩ ሪፎረሞችን አውጥቶ እየሰራ ይገኛል ፡፡ የዚሁ አካል የሆነው የ12ኛክፍልን ሀገር አቀፍ ፈተና ኩረጃን በመከላከል በሚያስችችል በጠበቀ ድሲፕሊን የ2014ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በዩኒቨርቲዎች እንድፈተኑ ተደርጓል ፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎችን በቅድመ ዩኒቨርሲቲ የ4 ወር ያቅም ማሻሻያ እንድወስዱ በተደረገው መሰረት በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አቅም ማሻሻያ ለሚውስዱ ተማሪዎች ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በዙሪያው ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከ9-12ኛ ክፍል ያሉ መማሪያ መጽሃፍትን በማሰባሰብና በየትምህርት አይነቱ ከ9-12ኛክፍል የሚያገለግሉ መረጃ መጽሀፍትን በመግዛት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ፡፡
የ24 ሰዓት የቤተ-መፅሀፍት አገልግሎት መስጠት ከ9-12ኛ ክፍል በየትምህርት አይነቱ አጋዥ መፅሀፍትን በቤተመጽሃፍት በማስቀመጥ ሙሉ አገልግሎት በመስጠት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጣለበትን አደራ እየተወጣ ይገኛል ፡፡
ለዚህ ተግባር የተመደቡ የግቢው መምህራን የተፈቀደላቸውን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም በልዩ ሁኔታ ለተምህርት ጥራት የድርሻቸውን እየተወጡ ያገኛሉ ፡፡


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
746 views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 13:31:04
ተማሪዎችን ለጉብኝት ይዞ ሲጓዝ በነበረ መኪና ላይ በደረሰ አደጋ የ4 ህጻናትና የ1 መምህርት ህይወት አለፈ።

በአዊ ብሔረሰብ አሰተዳደደር በባንጃ ወረዳ የዳሳሽ አካዳሚ ት/ት ቤት ተማሪዎችን ወደቻግኒ ታሪካዊ ቦታዎችን ለማስጎብኘት ይዞ በመጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 4 ህፃናትና የአንድ መምህርት ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

አደጋው የደረሰው በባንጃ ወረዳ ዚቅ ጎመርታ ቀበሌ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ ሲሆን 3 የህፃናት ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ አንድ ህፃንና እና የአንዲት መምህር ወደህከምና እንደደረሱ ህይወታቸው ማለፉን ወረዳው አስታውቋል።

በመኪናው ውስጥ የነበሩ ሌሎች ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ህፃናት ወደ እንጅባራ ጠ/ሆስፒታል ገብተው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛልም ተብሏል። ወደ ህክምና ከገቡት መካከል 4ቱ አገግመው ወደ ቤተሠቦቻቸው መመለሳቸውም ነው የተገለጸው።

@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
289 views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 15:06:08
ከፀሐይ ክብደት 30 ቢሊየን እጥፍ የገዘፈ በርባኖስ ተገኘ

በአፅናፈ-ሰማይ ላይ ከተዘረጉ በርካታ “ጋላክሲዎች” ይልቅ የገዘፈ በርባኖስ ወይም ጥልቁ ጥቁር ጉድጓድ “ብላክ ሆል” መገኘቱን የእንግሊዝ ተመራማሪዎች አስታወቁ።

በዶክተር ጀምስ ናይቲንጌል የተመራው የእንግሊዙ ዱርሃም ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድን ያገኘው በርባኖስ የፀሐይን ክብደት በ30 ቢሊየን ጊዜ እጥፍ የሚልቅ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

ተመራማሪወቹ ይህን ያክል መጠን ያለው በርባኖስ መገኘቱን እንግዳ እንደሆነባቸውም ነው የጥናት ቡድኑ መሪ የሚናገሩት።

በህዋ ላይ ከሚገኙ አካላት በመጠኑ ትልቁ ነው የተባለው ይህ በርባኖስ እንደ ሚልክዌይ (ፀሐይን ጨምሮ የፕላኔቶችን ስብስብ በያዘው) ጋላክሲ ባሉ ትላልቅ ጋላክሲዎች መሃል ላይ እንደሚገኝም ይታመናል።

የበርባኖሱ ግኝት ከዳር እንዲደርስ ሂደቱን በማሳለጥ ረገድ የጀርመኑ ማክስ ፕላንክ ኢንስቲትዩት ድጋፍ ማድረጉ ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም የናሳው “ሃብል ቴሌስኮፕ” ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምሥሎች በማንሳት እና ትርጉም እንዲያገኙ ለዱርሃም ዩኒቨርሲቲ በመላክ በሱፐር ኮምፒዩተር በርባኖሱ መኖሩ ተረጋግጧል፡፡

ጥናቱ ትናንትና ይፋ የሆነው በሮያል የሥነ-ፈለክ ማኅበር መሆኑንም አር ቲ ዘግቧል፡፡

በርባኖስ ወይም በእንግሊዝኛው አጠራር “ብላክ ሆል” በኅዋ ላይ ያለ ጥልቅ ጉድጓድ ሲሆን ከፍተኛ የስበት ኃይል ያለውና ብርሃን እንዳይታይ አድርጎ የማስቀረት ዐቅም ያለው መሆኑን የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ።

@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
969 views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 13:17:33
#Ad

ከ9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ የ #Mathematics ሁሉንም ቻፕተሮች ቲቶርያል ቪድዮ ከፍላቹህ መጠቀም ለምትፈልጉ የ2015 የዩንቨርሲቲ መግቢያ ተፈታኝ ተማሪዎች #ምዝገባ ጀምረናል።


ሺድዮዎቹ የተዘጋጁት በቀጥታ ከተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍት ነው።

ቪዲዮዎቹ በአብዘሃኛው የተዘጋጁት በ Screen recorder ሲሆን ሰፊ ማብራሪያ የሚፈልጉ ርዕሶች በቦርድ ተሰርተዋል።

ሁሉም ቪድዮዎች ክፍያ የፈፀሙ ተማሪዎች ብቻ የሚገቡበት Private የቴሌግራም ቻናል ላይ ተጭነዋል።

ክፍያ ፈፅመው ቪድዮዎቹ የሚገኙበት ቻናል ላይ የሚቀላቀሉ ተማሪዎች በራሳቸው ፕሮግራም መሰረት በቲቶርያሎቹ ይማራሉ።

እነኚህን ቪዲዮዎች ከፍለው የሚማሩ ተማሪዎች በቲቶርያሉ ላይ ያልገባቸውን ማንኛውም ጥያቄ መጠየቅ ይችላሉ።

ክፍያ የፈፀሙ ተማሪዎች ቪድዮዎቹ የሚገኙበት ቻናል ላይ የሚቆዩት የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና እስኪወስዱ ድረስ ብቻ ነው።


ቪድዮዎቹ የቀረቡበት ዋጋ
*G9 all Chapters 200ብር
*G10 all Chapters 200ብር
*G11 all Natural Chapters 250ብር
*G12 all Natural Chapters 250ብር

4ቱንም ለሚፈልጉ ተማሪዎች የ2010 እና የ2011 #UEE Solution Video ተጨምሮ በ1000 ብር ቀርቧል።


#REMEDIAL ፕሮግራም ለምትማሩ ተማሪዎች የምትማሯቸውን የ #Mathematics ሁሉንም ቻፕተሮች ከዚሁ ቲቶርያል ተቀንሰው በ300 ብር ቀርቦላቹሃል።

ፊዚክስ መማር ለምትፈልጉ በነፃ Click

ለመመዝገብ @muedu
ለተጨማሪ መረጃ 0977894547
802 views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 12:31:39
ከዛሬው የፓርላማ ውሎ
1.3K views09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 15:58:43 #ተጨማሪ

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ድረስ ለመደበኛና የማታ ተማሪዎች በመንግሥት የመደበኛ ትምህርት ቤቶች ለድጋሜ ተፈታኞች እና የርቀት ትምህርት ተማሪዎች በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች አማካኝነት በበይነ መረብ #ብቻ እንደሚያካሂዱ ተገልጿል።

መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ 9 እስከ 12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 በመማር ላይ ያሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

ተማሪዎች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ እንደሚጠበቅባቸውም ተገልጿል።

በመግለጫውም ተማሪዎ፣ ወላጆች፣ መዝጋቢዎች እና ከመምህራን የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጥሪ አቅርቧል።

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለጽ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ከ9-12 ያሉ #Mathematics የሁሉንም ቻፕተሮች የገፅ ለገፅ ቲቶርያል መግዛት ለምትፈልጉ ተፈታኝ ተማሪዎች
https://t.me/ATC_EUEE/48

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
183 views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 15:48:12
#EAES

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ አማካይነት እንደሚከናወን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንዳይፈጠር ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለባቸው ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።

ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን እንደማይፈተንም ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

፨ፈተናው እንደ ቀድሞ ተፈታኞች በዩንቨርሲቲዎች ይሰጣል

ከ9-12 ያሉ #Mathematics የሁሉንም ቻፕተሮች የገፅ ለገፅ ቲቶርያል መግዛት ለምትፈልጉ ተፈታኝ ተማሪዎች
https://t.me/ATC_EUEE/48


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
224 views12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 13:10:16

682 views10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 11:29:25

798 views08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ