Get Mystery Box with random crypto!

💠አምደ ሐይማኖት💠ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ⛪️

የቴሌግራም ቻናል አርማ amdehaymanotzeortodoxtewahdo — 💠አምደ ሐይማኖት💠ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ⛪️
የቴሌግራም ቻናል አርማ amdehaymanotzeortodoxtewahdo — 💠አምደ ሐይማኖት💠ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ⛪️
የሰርጥ አድራሻ: @amdehaymanotzeortodoxtewahdo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.85K
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ;ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሳጽን ይንቃሉ " ምሳሌ 1:7
👉 የቻናሉ አላማ
✔️💠የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስርዓት የጠበቁ ትምህርቶዎችን
✔️💠መንፈሳዊ ጥያቄና ዝማሬዎች
✔️💠ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን መረጃ ያገኙበታል
አስታየት @Godoliyaswe28
☞ ለመቀላቀል ይሕንን ይጫኑ

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-24 05:56:17 እግዚአብሔርን የሚወድ እና በእግዚአብሔር የሚወደድ #መንፈሳዊ_ሰው ሁልጊዜ ደስተኛ ነው ። በምንም ሁኔታ ይሁን በምንም እግዚአብሔር በእርግጠኝነት እንደሚሰራለት ይሰማዋል በእርሱም ስራ ይደሰታል ። በእርግጥም እግዚአብሔር ሥራውን ባናየውም እንኳ ይሠራል ። ሥራውን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ልናየው እንችላለን በዚህም እንደሰታለን ። ይህን ደስታችንም ማንም አይወስድብንም ። ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጆች የሚደሰቱት በስጦታዎቹ ብቻ ሳይሆን በራሱ በጌታም ነው ።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
5 viewsDaniel dendir ጎዶሊያስ 28 .., 02:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 05:24:14 ወዳጄ ሆይ! ኃጢአተኛ ከኾንህ በደልህን ትናዘዝ ዘንድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፤ ጻድቅም ከኾንህ ከጽድቅ [ጎዳና] እንዳትወድቅ ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፤ ቤተ ክርስቲያን የኃጥኡም የጻድቁም ወደብ ናትና፡፡

ኃጢአተኛ ነህን? ተስፋ አትቁረጥ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህም ንስሐ ግባ፡፡ ኃጢአት ሠርተሃልን? እንግዲያውስ እግዚአብሔርን “በድያለሁ” በለው፡፡

እስኪ ንገረኝ! “በድያለሁ” ብለህ ለመናዘዝ ምን ውጣ ውረድ፣ ምን ዓይነት የሕይወት መርሕ፣ ምንስ መከራ አለው? “በድያለሁ” ብሎ አንዲት ቃል ለመናገር ክብደቱ ምኑ ላይ ነው? ምናልባት [ኃጢአት ሠርተህ ሳለ] በደለኛ አይደለሁም የምትል ከኾነ ዲያብሎስም አንተን አይወቅስህም፡፡ [በድያለሁ ብለህ ንስሐ የምትገባ ከኾነ ግን] ይህን [ዲያብሎስ ሊወቅስህ እንደሚችል] አስቀድመህ አስብ፡፡ …

ስለዚህ ክብርህን እንዳይወስድብህ ለምን አትከለክለውም? ለቅጽበት ያህልስ እንኳን የማይተኛ ከሳሽ እንዳለህ ዐውቀህ ለምን በደልህን ተናዝዘሃት አታስወግዳትም?

ኃጢአት ሠርተሃልን? እንግዲያውስ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ እግዚአብሔርን “በድያለሁ” ብለህ ንገረው፡፡ እኔ ከዚህ ውጪ ከአንተ የምፈልገው ሌላ ምንም ነገር የለኝም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስም፡- “ንግር አንተ ኃጣውኢከ ቅድመ ከመ ትጽደቅ - ትከብር ዘንድ አንተ አስቀድመህ ኃጢአትህን ተናገር” ይላል (ኢሳ.43፡26)፡፡ [ስለዚህ] ኃጢአትህን ታስወግዳት ዘንድ ተናዘዛት፡፡

ይህን ለማድረግ ውጣ ውረድ የለውም፤ ዙሪያ ጥምጥም የቃላት ድርደራም አያሻህም፤ ገንዘብ መክፈል አያስፈልግህም፤ ወይም እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ነገሮች አያስፈልጉህም፡፡ አንዲት ቃል ተናገር፤ በደልህን በአንቃዕድዎ አስባት፤ “በድያለሁ” ብለህም ተናዘዛት፡፡
9 viewsDaniel dendir ጎዶሊያስ 28 .., edited  02:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 11:18:20 *መልካሙ ገበሬ *

ቢፈልግባትም መልካሙ ገበሬ
አልተገኘባትም ከበለስዋ ፍሬ

ለስልሶላት ነበር ሃይማኖት መሬቱ
ተቀጥሮላት ነበር አጥር ስርዓቱ
ተነቅሎላት ነበር ድንጋይ ፈተናዋ
ፍሬ ግን ታጣባት በመጨረሻዋ

አዝ=====

ፍሬ የሌለባት ቅጠል ስለሆነች
ተካይዋን በምግባር ስላላስደሰተች
መልካሙን ገበሬ ሊቆርጣት ተነሳ
ሌሎች እንዳይጠፉ በእርሷ የተነሳ

አዝ=====

ለንስሐ የሚሆን እድሜ እንዲሰጣት
ጠባቂ መልዐኳ ተማጸነላት
ምክር እና ተግሳጽ ይጨመርላት
ታፈራ እንደሆነ ለዓመት እንያት

አዝ=======

ልመናውን ሰምቶ ጌታውም ፈቀደ
ጥቂት እድሜ ሊሰጥ ሊታገስ ወደደ
ዳግመኛ ሲመጣ ፍሬ ካላፈራች
ተቆርጣ ወደ ቶን እሳት ትጣላለች

ቀሲስ ዳዊት ፈንታዬ


@Amdehaymanotzeortodoxtewahdo
@Amdehaymanotzeortodoxtewahdo
138 viewsDaniel dendir ጎዶሊያስ 28 .., 08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 06:00:50 ✞ኪዳነ ምህረት✞

እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
ኪዳነምህረት ኪዳነምህረት
ኪዳነምህረት አንባ መጠጊያ ናት

አዝ..

ሔዋን ሰታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጓ እናቴ ቤተን አድምቀሻል

አዝ ..........

ለዘላለም ንጽህይት በመሆኗ
ከኔ ጋር ነው ህያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሀዘኔን አልፌ
አጽናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ

አዝ ......

ከጥፋቱ ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በህይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ

አዝ .....

በእናትነት ህይወቴን ጎብኝታው
ልቤ አረፈ ተነቀወሎ በሽታው
ሰንሰለቴ ከእጄ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ


ሊቀ መዘምራን ዲ.ን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

@Amdehaymanotzeortodoxtewahdo
@Amdehaymanotzeortodoxtewahdo
142 viewsDaniel dendir ጎዶሊያስ 28 .., 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 21:04:11
ኪዳነ ምህረት እናቴ

አውቃለሁ እኔ ጎስቋላ ነኝ
ምንም ጽድቅ ያልሰራሁኝ
ህይወቴን በሃጢያት ያሳለፍኩኝ
ዛሬም መመለስ የተሳነኝ
ራሴን መግዛት ያቃተኝ
አውቃለሁ አንዳችም ምግባር እንደሌለኝ።
ደንግል በኪዳንሽ ልብሽን ይራራልኝ
እንደ በላኤ ሰብዕ የሚያደርገኝ
አንቺ ግን እንኳንስ ለሰው
አምላክ በአምሳሉ ለፈጠረው
አይደለሽም እንዴ?
ለውሻ እንኳን ያዘንሽ
ውሀ ጽሙንም ያስታግስሽ።
አንድ ቀን በድንገት ቢጠራት
ነፍሴን ለፍርድ ቢያቆማት
አውቃለሁ በስራዋ እንዳትሟገት
በጽድቋም እንዳታገኝ ምህረት።
ግን አንዲት መመኪያ አለቻት
ዋስ ጠበቃዬ ምትላት
ከእሳት ለመዳን ከልቧ ምትጠራት
እርሷም አንቺው ነሽ ኪዳነ-ምህረት
አደራ ድንግል እንዳትተያት
ለነፍሴ መዳን ምክንያት ስለ ሆንሻት።

እኔም እወድሻለሁ ልበል እንደልጅነቴ
ንጽሕት ዘሥጋ ወነፍስ ኪዳነ ምህረት እናቴ

✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞
163 views𝑛𝑒𝑡𝑠𝑎𝑛𝑒𝑡 𝑙𝑒𝑚𝑚𝑎, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 20:59:06
«ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ» ተብሎ በዳዊት መዝሙር መዝ 88 ፥3 እንደተጻፈ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል የእመአምላክ ግን ይለያል አምላክ የመረጣት እናት እንድትሆነው ነው ።

በተሰጣት የምህረት ቃልኪዳን በእርሷ ምልጃ በልጇም በኢየሱስ ክርስቶስ
የማያልቅ ምህረት የኢትዮጵያና የልጆቿ እንባ ይቆማል # እናምናለን
16
ኪዳነምህረት
167 views𝑛𝑒𝑡𝑠𝑎𝑛𝑒𝑡 𝑙𝑒𝑚𝑚𝑎, 17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 12:17:21 ‹‹ #ጠላትህን_ውደድ›› ማቴ. 5፥45

‹‹ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ›› ማቴ. 5፥43-45

የዚህኛው ሕግ ዋና መልእክት ፍቅር ነው፡፡ ይህን ሕግ የሰጠን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠላቶችን በመውደድ እኛም እንዲሁ እንድናደርግ አስተምሮናል፡፡ ሰውን ሁሉ መውደድ የክርስትና ሕግ ነው፡፡ ይህ ሕግ ፍጹም የሚሆነው ደግሞ የሚያውቁትን ወዳጅን በማፍቀር ብቻ ሳይሆን ጠላትን በመውደድ በተግባር የተገለጠ እንደሆነ ነው፡፡ ክርስቶስ ሁሉንም በመውደድ በፍጹም ፍቅር እንደተገለጠ ክርስቲኖች ሁሉ ደግሞ ሁሉን በመውደድ ፍጹማን እንድንሆን ይህ ሕግ ግድ ይለናል፡፡ ማቴ. 5፥43-46

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ
188 viewsDaniel dendir ጎዶሊያስ 28 .., 09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 05:28:55 #ቋንቋዬ_ነሽ_ድንግል

ቋንቋዬ ነሽ ድንግል መግባቢያዬ
መልስ የማገኝብሽ ከጌታዬ (፪)
በአንቺ ቀርቤአለሁ በአምላኬ ፊት
ቤቴ ሞልቶልኛል በበረከት(፪)

በምን ሥራዬ ነው ከፊቱ የቆምኩት
መቼ በቅቼ ነው ስሙን የጠራሁት
አስታራቂ እናት አንቺን ስለሰጠኝ
ስለ ቃል ኪዳንሽ አቤት ልጄ አለኝ(፪)
#አዝ
ቅድስና ህይወት ከእኔ ተሰውሮ
በውሸት በሐሜት አንደበቴ ታስሮ
በእመ አምላክ ምልጃ አዲስ ሰው ሆኛለሁ
እንደ መለእክቱ ይኸው እዘምራለሁ(፪)
#አዝ
ስለ እመ አምላክ ብሎ ያፈረ የለም
በአንቺ ያልከበረ ሰው አይገኝም
እንደ ባለማዕረግ እኔም ሰው መባሌ
አንቺን አግኝቼ ነው ድንግል መሰላሌ(፪)
#አዝ
ሰላም ለኪ ብዬ ስጀምር ፀሎቴን
ሐሴት ይመላዋል መላ ሰውነቴን
እንደ ቅዱስ ኤፍሬም በምስገናሽ ልፅና
በእጆችሽ ያለው አምላኬ ነውና(፪)

##ዘማሪ ልዑል ሰገድ


@Amdehaymanotzeortodoxtewahdo
@Amdehaymanotzeortodoxtewahdo
193 viewsDaniel dendir ጎዶሊያስ 28 .., 02:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 05:28:04 ++የመድኃኒት እናት++
+++++++++++++++++++++++++
የመድኃኒት እናት ህመምተኛው ልጅሽ
ምህረትን ፍለጋ ቆሚያለሁ ከደጅሽ
ፀሎት ልመናሽን ታምኛለሁና
ከቤትሽ መልሽኝ ዳግም እንደገና
............
ዘማሪ
ቀሲስ ዳዊት ፍንታዬ ዘበሐታ


@Amdehaymanotzeortodoxtewahdo
@Amdehaymanotzeortodoxtewahdo
162 viewsDaniel dendir ጎዶሊያስ 28 .., 02:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 07:01:01 _<<የሚጠቅምህን_ብቻ_ተመልከት!!!!!>>_

➾"በአንዲት ገዳም የሚኖሩ የበቁ አባት ነበሩ። አንድ ወጣት ወደሳቸው ይመጣና አባቴ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እፈልጋለሁ ይህን አስቤ የእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሆንኩ ነገርግን በዛም እንዳልቆይ የወንድሞቼ ሀሜት አሉባልታ ከቤቱ እንድርቅ አረገኝ ምን ላድርግ አባቴ?

አባም ሲያዳምጡት ቆዩና አይ ልጄ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ማሰብህ መልካም ነበር ነገርግን እዛው አጠፋክ የሰዎች ሀሜትና አሉባልታ ሊያርቅህ አይገባም ነበር ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የሚጠቅምህ የእነሱን ትችት መመልከት ሳይሆን የእራስህን ኃጢአት መመልከትህ ስለሆነ።በል ተነስ ሂድና የማይጠቅምህን ትተህ የሚጠቅምህን ብቻ ተመልከት ብለው አሰናበቱት።"

➾እኛም ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር እንዳንቀርብ የሚያረገን ይሄ ነው።የሚጠቅመን ትተን የማይጠቅመንን መመልከታችን።የእራሳችንን ኃጢአት ትተን ስለነ እግሌ ማውራታች የእራሳችን ነውር በስራችን አርገን ሌላውን መኮነናችን እግዚአብሔርን ቀረብነው ብለን የምንገፈትረው ጥቂት አይደለንም።

➾አስተውሉ ስንት የአገልግሎት ጊዜ ያትን በማይጠቅም ሀሜትና አሉባልታ አቃጥለናል? ስንት የጸሎት ሰዓትን ስሌላው በማውራት ጨርሰናል? ስንቶቻችንስ የሚጠቅመንን ባለማወቃችን ለቤቱ ቀርበን ለጌታው እርቀናል?

➾ወደእግዚአብሔር እንድን ቀርብ የሚያደርገን ሌላውን መኮነናችን ሳይሆን የእራሳችንን ኃጢያትን መመልከታችን ነው። የቤተክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን ሲያጠይቅ "እኔ መላእክትን ከሚያይ ሰው ይልቅ ኃጢያቱን በሚያይ ሰው እቀናለሁ። ምክንያቱም መላእክቱን ስላየ ብቻ የጸደቀ የለም ኃጢያቱን ስለተመለከተ ግን የጸደቀ አለ።" በማለት ግልጽ ያደርግልናል።

➾የማይጠቅመንን ትተን የሚጠቅመንን እንድንመለከት እግዚአብሔር ይርዳን!!!
227 viewsA𝑠ℎ𝑒𝑛𝑎𝑓𝑖 A𝑘𝑙𝑖𝑙𝑢, 04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ