Get Mystery Box with random crypto!

‹‹ #ጠላትህን_ውደድ›› ማቴ. 5፥45 ‹‹ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታ | 💠አምደ ሐይማኖት💠ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ⛪️

‹‹ #ጠላትህን_ውደድ›› ማቴ. 5፥45

‹‹ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ›› ማቴ. 5፥43-45

የዚህኛው ሕግ ዋና መልእክት ፍቅር ነው፡፡ ይህን ሕግ የሰጠን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠላቶችን በመውደድ እኛም እንዲሁ እንድናደርግ አስተምሮናል፡፡ ሰውን ሁሉ መውደድ የክርስትና ሕግ ነው፡፡ ይህ ሕግ ፍጹም የሚሆነው ደግሞ የሚያውቁትን ወዳጅን በማፍቀር ብቻ ሳይሆን ጠላትን በመውደድ በተግባር የተገለጠ እንደሆነ ነው፡፡ ክርስቶስ ሁሉንም በመውደድ በፍጹም ፍቅር እንደተገለጠ ክርስቲኖች ሁሉ ደግሞ ሁሉን በመውደድ ፍጹማን እንድንሆን ይህ ሕግ ግድ ይለናል፡፡ ማቴ. 5፥43-46

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ