Get Mystery Box with random crypto!

#ቋንቋዬ_ነሽ_ድንግል ቋንቋዬ ነሽ ድንግል መግባቢያዬ መልስ የማገኝብሽ ከጌታዬ (፪) በአንቺ ቀር | 💠አምደ ሐይማኖት💠ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ⛪️

#ቋንቋዬ_ነሽ_ድንግል

ቋንቋዬ ነሽ ድንግል መግባቢያዬ
መልስ የማገኝብሽ ከጌታዬ (፪)
በአንቺ ቀርቤአለሁ በአምላኬ ፊት
ቤቴ ሞልቶልኛል በበረከት(፪)

በምን ሥራዬ ነው ከፊቱ የቆምኩት
መቼ በቅቼ ነው ስሙን የጠራሁት
አስታራቂ እናት አንቺን ስለሰጠኝ
ስለ ቃል ኪዳንሽ አቤት ልጄ አለኝ(፪)
#አዝ
ቅድስና ህይወት ከእኔ ተሰውሮ
በውሸት በሐሜት አንደበቴ ታስሮ
በእመ አምላክ ምልጃ አዲስ ሰው ሆኛለሁ
እንደ መለእክቱ ይኸው እዘምራለሁ(፪)
#አዝ
ስለ እመ አምላክ ብሎ ያፈረ የለም
በአንቺ ያልከበረ ሰው አይገኝም
እንደ ባለማዕረግ እኔም ሰው መባሌ
አንቺን አግኝቼ ነው ድንግል መሰላሌ(፪)
#አዝ
ሰላም ለኪ ብዬ ስጀምር ፀሎቴን
ሐሴት ይመላዋል መላ ሰውነቴን
እንደ ቅዱስ ኤፍሬም በምስገናሽ ልፅና
በእጆችሽ ያለው አምላኬ ነውና(፪)

##ዘማሪ ልዑል ሰገድ


@Amdehaymanotzeortodoxtewahdo
@Amdehaymanotzeortodoxtewahdo