Get Mystery Box with random crypto!

__ ➾'በአንዲት ገዳም የሚኖሩ የበቁ አባት ነበሩ። አንድ ወጣት ወደሳቸው ይመጣና አባቴ ወደ እ | 💠አምደ ሐይማኖት💠ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ⛪️

_<<የሚጠቅምህን_ብቻ_ተመልከት!!!!!>>_

➾"በአንዲት ገዳም የሚኖሩ የበቁ አባት ነበሩ። አንድ ወጣት ወደሳቸው ይመጣና አባቴ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እፈልጋለሁ ይህን አስቤ የእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሆንኩ ነገርግን በዛም እንዳልቆይ የወንድሞቼ ሀሜት አሉባልታ ከቤቱ እንድርቅ አረገኝ ምን ላድርግ አባቴ?

አባም ሲያዳምጡት ቆዩና አይ ልጄ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ማሰብህ መልካም ነበር ነገርግን እዛው አጠፋክ የሰዎች ሀሜትና አሉባልታ ሊያርቅህ አይገባም ነበር ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የሚጠቅምህ የእነሱን ትችት መመልከት ሳይሆን የእራስህን ኃጢአት መመልከትህ ስለሆነ።በል ተነስ ሂድና የማይጠቅምህን ትተህ የሚጠቅምህን ብቻ ተመልከት ብለው አሰናበቱት።"

➾እኛም ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር እንዳንቀርብ የሚያረገን ይሄ ነው።የሚጠቅመን ትተን የማይጠቅመንን መመልከታችን።የእራሳችንን ኃጢአት ትተን ስለነ እግሌ ማውራታች የእራሳችን ነውር በስራችን አርገን ሌላውን መኮነናችን እግዚአብሔርን ቀረብነው ብለን የምንገፈትረው ጥቂት አይደለንም።

➾አስተውሉ ስንት የአገልግሎት ጊዜ ያትን በማይጠቅም ሀሜትና አሉባልታ አቃጥለናል? ስንት የጸሎት ሰዓትን ስሌላው በማውራት ጨርሰናል? ስንቶቻችንስ የሚጠቅመንን ባለማወቃችን ለቤቱ ቀርበን ለጌታው እርቀናል?

➾ወደእግዚአብሔር እንድን ቀርብ የሚያደርገን ሌላውን መኮነናችን ሳይሆን የእራሳችንን ኃጢያትን መመልከታችን ነው። የቤተክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን ሲያጠይቅ "እኔ መላእክትን ከሚያይ ሰው ይልቅ ኃጢያቱን በሚያይ ሰው እቀናለሁ። ምክንያቱም መላእክቱን ስላየ ብቻ የጸደቀ የለም ኃጢያቱን ስለተመለከተ ግን የጸደቀ አለ።" በማለት ግልጽ ያደርግልናል።

➾የማይጠቅመንን ትተን የሚጠቅመንን እንድንመለከት እግዚአብሔር ይርዳን!!!