Get Mystery Box with random crypto!

✞ኪዳነ ምህረት✞ እናት አለኝ የምታብስ እንባ አያታለሁ ስወጣ ስገባ ኪዳነምህረት ኪዳነምህረት ኪዳ | 💠አምደ ሐይማኖት💠ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ⛪️

✞ኪዳነ ምህረት✞

እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
ኪዳነምህረት ኪዳነምህረት
ኪዳነምህረት አንባ መጠጊያ ናት

አዝ..

ሔዋን ሰታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጓ እናቴ ቤተን አድምቀሻል

አዝ ..........

ለዘላለም ንጽህይት በመሆኗ
ከኔ ጋር ነው ህያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሀዘኔን አልፌ
አጽናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ

አዝ ......

ከጥፋቱ ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በህይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ

አዝ .....

በእናትነት ህይወቴን ጎብኝታው
ልቤ አረፈ ተነቀወሎ በሽታው
ሰንሰለቴ ከእጄ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ


ሊቀ መዘምራን ዲ.ን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

@Amdehaymanotzeortodoxtewahdo
@Amdehaymanotzeortodoxtewahdo