Get Mystery Box with random crypto!

ኪዳነ ምህረት እናቴ አውቃለሁ እኔ ጎስቋላ ነኝ ምንም ጽድቅ ያልሰራሁኝ ህይወቴን በሃጢያት ያ | 💠አምደ ሐይማኖት💠ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ⛪️

ኪዳነ ምህረት እናቴ

አውቃለሁ እኔ ጎስቋላ ነኝ
ምንም ጽድቅ ያልሰራሁኝ
ህይወቴን በሃጢያት ያሳለፍኩኝ
ዛሬም መመለስ የተሳነኝ
ራሴን መግዛት ያቃተኝ
አውቃለሁ አንዳችም ምግባር እንደሌለኝ።
ደንግል በኪዳንሽ ልብሽን ይራራልኝ
እንደ በላኤ ሰብዕ የሚያደርገኝ
አንቺ ግን እንኳንስ ለሰው
አምላክ በአምሳሉ ለፈጠረው
አይደለሽም እንዴ?
ለውሻ እንኳን ያዘንሽ
ውሀ ጽሙንም ያስታግስሽ።
አንድ ቀን በድንገት ቢጠራት
ነፍሴን ለፍርድ ቢያቆማት
አውቃለሁ በስራዋ እንዳትሟገት
በጽድቋም እንዳታገኝ ምህረት።
ግን አንዲት መመኪያ አለቻት
ዋስ ጠበቃዬ ምትላት
ከእሳት ለመዳን ከልቧ ምትጠራት
እርሷም አንቺው ነሽ ኪዳነ-ምህረት
አደራ ድንግል እንዳትተያት
ለነፍሴ መዳን ምክንያት ስለ ሆንሻት።

እኔም እወድሻለሁ ልበል እንደልጅነቴ
ንጽሕት ዘሥጋ ወነፍስ ኪዳነ ምህረት እናቴ

✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞