Get Mystery Box with random crypto!

*መልካሙ ገበሬ * ቢፈልግባትም መልካሙ ገበሬ አልተገኘባትም ከበለስዋ ፍሬ ለስልሶላት ነበር ሃይ | 💠አምደ ሐይማኖት💠ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ⛪️

*መልካሙ ገበሬ *

ቢፈልግባትም መልካሙ ገበሬ
አልተገኘባትም ከበለስዋ ፍሬ

ለስልሶላት ነበር ሃይማኖት መሬቱ
ተቀጥሮላት ነበር አጥር ስርዓቱ
ተነቅሎላት ነበር ድንጋይ ፈተናዋ
ፍሬ ግን ታጣባት በመጨረሻዋ

አዝ=====

ፍሬ የሌለባት ቅጠል ስለሆነች
ተካይዋን በምግባር ስላላስደሰተች
መልካሙን ገበሬ ሊቆርጣት ተነሳ
ሌሎች እንዳይጠፉ በእርሷ የተነሳ

አዝ=====

ለንስሐ የሚሆን እድሜ እንዲሰጣት
ጠባቂ መልዐኳ ተማጸነላት
ምክር እና ተግሳጽ ይጨመርላት
ታፈራ እንደሆነ ለዓመት እንያት

አዝ=======

ልመናውን ሰምቶ ጌታውም ፈቀደ
ጥቂት እድሜ ሊሰጥ ሊታገስ ወደደ
ዳግመኛ ሲመጣ ፍሬ ካላፈራች
ተቆርጣ ወደ ቶን እሳት ትጣላለች

ቀሲስ ዳዊት ፈንታዬ


@Amdehaymanotzeortodoxtewahdo
@Amdehaymanotzeortodoxtewahdo