Get Mystery Box with random crypto!

💠አምደ ሐይማኖት💠ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ⛪️

የቴሌግራም ቻናል አርማ amdehaymanotzeortodoxtewahdo — 💠አምደ ሐይማኖት💠ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ⛪️ አ
የቴሌግራም ቻናል አርማ amdehaymanotzeortodoxtewahdo — 💠አምደ ሐይማኖት💠ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ⛪️
የሰርጥ አድራሻ: @amdehaymanotzeortodoxtewahdo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.85K
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ;ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሳጽን ይንቃሉ " ምሳሌ 1:7
👉 የቻናሉ አላማ
✔️💠የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስርዓት የጠበቁ ትምህርቶዎችን
✔️💠መንፈሳዊ ጥያቄና ዝማሬዎች
✔️💠ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን መረጃ ያገኙበታል
አስታየት @Godoliyaswe28
☞ ለመቀላቀል ይሕንን ይጫኑ

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-20 12:57:19 ✢✢✢
በተረጋጋ መንፈስ፤ በንጹሕ አእምሮ ስለቅዱሳን ማሰብ ስንጀምር ወንጌል ምን ማለት እንደሆነ እንገነዘባለን። ቅዱሳን ወንጌልን በጸሎታቸውም በሕይወታቸውም ያለማቋረጥ ይደግሙታል። ሐዋርያት ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ተምረው ክርስቶስን እንደመሰሉ በእግረ ሐዋርያት የተተኩም ቅዱሳን ከሐዋርያት ተምረው ሐዋርያትን መሰሉ።
"እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ"እንዳለ 1ኛቆሮ 11÷1።

ሐዋርያት ዓለምን ዞረው እንዳስተማሩ እነሱም ይህንን አደረጉ። በዐቢይ ተጋድሎ ተጠመዱ በመጋዝ ተተረተሩ፣ በመስቀል ተሰቀሉ፣ በሰይፍ ተቆረጡ፣ እንደበግ ታረዱ፣ እንደ ሽንኩርት ተቀረደዱ እንደ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በንጽሕና ኑረው በሐሰት ተከሰው በጭካኔ ተገድለዋል። እንደ አምላካችን ክርስቶስም ይነሣሉ።
"ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን" እንዲል ሮሜ 6÷5።

እርሱ ያከበራቸውን ማንም አያዋርዳቸውምና ፤ጆሮቹም ሁልጊዜ ወደእነርሱ ነውና ቅዱሳንን ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረትን እንዲለምኑልን እንለምናቸዋለን። ስለእነሱም ብሎ ይቅር እንዲለን
በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ
በእንተ መላእክት መሐረነ ክርስቶስ
በእንተ ቅዱሳን መሐረነ ክርስቶስ እንለዋለን።
ሰው በወዳጁ ሲማጸኑት ልቡ እንዲራራ አምላካችን እግዚአብሔርም ስለወዳጆቹ ራርቶ ይቅር ይለናል። እንጂማ እኛ እንኳን ጸሎታችን ኃይል ኖሮት(በንጹሕ ሕሊና ፣በአንቃዕድዎ ልቡና፣ በጽኑዕ ፍቅር አንጸልይምና )ሊሰማ በቅጡ መች እንጸልያለን።

እግዚአብሔር ያከበራችሁ ቅዱሳን ሆይ እግዚአብሔር ራሱ እንዳከበራችሁ መጠን ምስጋና ይድረሳችሁ።

እኛ ደካሞች በኃጢአት ሀሳብ፣በኃጢአት ንግግር፣በኃጢአት ተግባር የዛልን ነንና ረዳትነታችሁ ከእኛ አይለየን።

አሜን

ዲ/ን ሳሙኤል በላቸው
233 views𝑛𝑒𝑡𝑠𝑎𝑛𝑒𝑡 𝑙𝑒𝑚𝑚𝑎, 09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 08:27:51 #ስለማስመሰል_ርኅራኄው_ሰይጣንን_ተጠንቀቀው
,,,, የቀጠለ

ሐ/ #ዓለማዊ_አስተሳሰቦችን_መንፈሳዊ_በማስመሰል

በተለይ ዛሬ ላይ የዲያብሎስ ዋናው ማታለያው በመንፈሳዊነትና በዓለማዊነት መካከል ያለውን ድንበር በማጥፋት ለዓለማዊ አስተሳሰቦች መንፈሳዊ ሽፋን መስጠት ነው፡፡ በተደጋጋሚ የምንሰማቸው የድኅረ ዘመናዊነት፣ የባህል እና የሃይማኖት ብዝኃነት፣ የሉላዊነት እና የዓለማዊነት እይታዎች በግለሰቦች ነፃነት ስም ሃይማኖት የሰዎችን ነፃነት እንደሚገድብ አድርጎ በማቅረብና ሃይማኖተኛ መሆንን እንደጽንፈኛ አድርጎና አስመስሎ ያቀርባል፡፡ ሰዎችንም ሳያውቁት በእነዚህ አስተሳሰቦች ተጽዕኖ ከሃይማኖታቸው ወጥተው ሃይማኖት የለሽ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡

#ከዲያብሎስ_የማስመሰል_ርህራሔው_እንዴት እንጠንቀቅ?

ሀ #ሕሊናችንን_በመርመር

ዘወትር በሕሊናችን የሚመላለሱትን ሀሳቦች በጥንቃቄ ልንመረምራቸው፣ ወደ ውሳኔ ከመድረሳችንም አስቀድመን ‹‹ለምን?፣ እንዴት?፣ ከዚያስ?›› ብለን መጠየቅ ይጠበቅብናል፡፡ ባለን ዕውቀትም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከምናገኘው ትምህርት ጋር በማጣቀስ መረዳት መቻል አለብን፡፡ ‹‹የቀደመ የሕይወት ተሞክሮዬ ምን አስተምሮኛል?›› ብለንም ልንመረምረው ያስፈልጋል፡፡ ‹‹አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ እርሱ ነውና››፤ (ምሳ. ፬፥፳፫) ቅዱስ ጴጥሮስ በዲያብሎስ የማስመሰል ርኅራኄው ወጥመድ እንዳንያዝ በንቃት እንድንኖር ያስገነዝበናል፡፡ ‹‹በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና›› እንዲል፡፡ (፩ኛ ጴጥ. ፭፥፰)

ለ #በትሕትና

ሰይጣን በማስመሰል ርኅራኄው በመቅረብ የበቃውንም ሰው በትዕቢት በከንቱ ውዳሴ ለመጣል የተንኮል ወጥመዱን ይዘረጋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እንደቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ›› (፩ቆሮ. ፲፥፲፪) እንዳለ ጠላት ቀርቦ በትዕቢት እንዳይጥለን ትሕትናን ገንዘብ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ‹‹ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል›› ተብሎም ተጽፏልና፡፡ (፩ኛ ጴጥ. ፭፥፭)

ሐ #በጸሎት_በመትጋት

ጸሎት ከዲያብሎስ የሚላኩብንን የጥፋት ፍላጻዎች ጋሻ ሆኖ የሚመክት መሣሪያችን ነው፡፡ ስለዚህ ዘወትር ሳናቋርጥ በጸሎታችን እግዚአብሔርን በማመስገን፣ ልዕልናውን፣ ቸርነቱንና አዳኝነቱን በማሰብ፣ በፍጹም ልባችን ሆነን ወደ እግዚአብሔር እንጸልይ፤ ‹‹ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤›› (ማቴ. ፳፮፥፵፩) ተብሎ ተጽፏልና፡፡ ስለሆነም የዲያብሎስን ፈተና ልንቋቋም ከምንችልባቸው መንፈሳውያት ኃይሎቻችን መካከል ጸሎት ዋነኛው መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል፡፡

መ #ሕዋሶቻችን_ከክፉ_ሥራ_በመጠበቅ

ዲያብሎስ እኛን ለማሳት የሚጠቀመው የገዛ ሕዋሶቻችን ነው፡፡ እነርሱን መቆጣጠር ከቻልን በዲያብሎስ የማስመሰል ርኅራኄ አንታለልም፡፡ ዓይናችን የሚያየውን ክፉና በጎ ነገር፣ ጆሮዋችን የሚሰማውን ሐሰትና እውነቱን ነገር መምረጥ ስንችል፣ አንደበታችን እውነትን ሲናገር፣ እግሮቻችን ወደተቀደሱ ሥፍራዎች ሲያዘወትር ዲያብሎስ በቀላሉ ቀርቦ አያስተንም፡፡ በአጠቃላይ ሕዋሶቻችን ከኃጢአት ሥራ ተለይተው በጎ ነገርን መሥራት ሲጀምሩ በጎን ከክፉ ስለምንለይ በዲያብሎስ የማስመሰል ርኅራኄው ወጥመድ በቀላሉ አንወድቀወም፡፡

ሠ #የእግዚአብሔርን_ዕቃ_ጦር_ሁሉ_በመልበስ

ክርስቲያን ዘወትር በንቃት በመዘጋጀት ሕይወቱን ይመራል እንጂ በዘፈቀደ አይመራም፡፡ ‹‹ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን›› (ሉቃ.፲፪፥፴፭) ተብሎ በወንጌል እንደተጻፈው፤ ቅዱስ ጳውሎስ የዲያብሎስን ውጊያዎች በድል አድራጊነት ለመወጣት ምን ማድረግ እንዳለብን ሲያጠይቅ ‹‹የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ሥፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ›› ብሎናል፡፡ (ኤፌ ፮፥፲፩) የጦር ዕቃ የተባሉትን ጾም ጸሎትና መንፈሳዊ ተጋድሎን ጋሻና ጦር አድርገን ከዲያብሎስ የማስመሰል ርኅራኄው ወጥመድ ማምለጥ ይቻላል፡፡

ረ #በረድኤተ_እግዚአብሔር_በማመን

ዲያብሎስ በማስመሰል ርኅራኄው ለፈተና ወደ በሕይወታቸን ሲመጣ ‹‹ለምን ወይም እንዴት›› አንበል፤ ይልቅስ በእግዚአብሔር ረድኤት ማመን ይገባናል፤ እግዚአብሔር ማንንም በክፉ አይፈትንምና፡፡ ‹‹ማንም ሲፈተን በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈትንምና››፡፡ (ያዕ. ፩፥፲፫) ይልቅስ እንኳን እኛ ጌታችንም ተፈትኗል፤ ‹‹እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና›› (ዕብ. ፪፥፲፰) ተብሎ የተጻፈልን በፈተናችን ሁሉ መጽናኛ ይሆነን ዘንድ ነው፡፡ ስንፈተን ልንጨነቅ አይገባም፤ ጌታችንም ተፈትኗልና፤ ድል አድርጎም ድል የምናደርግበትን ኃይል ሰጥቶናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ›› (ፊል. ፬፥፲፫) ብሎ እንዳስተማረን ኃይልን የሚሰጠን አምላክ እንዳለ አምነን ዲያብሎስ በማስመሰል ርኅራኄው የሚያመጣብንን ሥውር ፈተናን በማለፍ ድል ማድረግ እንችላለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ምንጭ፤ ከ‹‹መንፈሳዊ ውጊያዎች›› ፪ኛ መጽሐፍ፤ በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
269 viewsDaniel dendir ጎዶሊያስ 28 .., 05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 20:33:23 #ስለማስመሰል_ርኅራኄው_ሰይጣንን_ተጠንቀቀው

አምላካችን እግዚአብሔር አዳምን ሲፈጥረው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም እንዳልሆነ በማየቱ ከጎኑ አንዲት አጥንትን ወስዶ ሔዋንን ፈጠረለት፡፡ በገነት እንዲኖሩም አደረጋቸው፤ ከአንዲት ዕፅ (የሞት ዛፍ) በቀር ሁሉን እንዲበሉም አዘዛችው፤ ‹‹ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና››፡፡ (ዘፍ. ፪፥፲፮) ነገር ግን ዲያብሎስ ወደ እነርሱ ቀርቦ ለእነርሱ ያዘነ በማስመሰል ክፉ ምክርን መከራቸው፡፡ ‹‹ሞትን አትሞቱም፤ ከእርስዋ በበላችሁ ቀን፥ ዐይኖቻችሁ እንዲከፈቱ፥ እንደ እግዚአብሔር እንደምትሆኑ፥ መልካምንና ክፉን እንደምታውቁ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው›› (ዘፍ ፫፥፬) አላቸው፡፡ እነርሱም ዲያብሎስ ለእነርሱ አስቦና ራርቶ የመከራቸው ስለመሰላቸው ክፉ ምክሩን ተቀብለው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አፈረሱ፡፡ አስቀድሞ ፈጣሪያቸው ለእነርሱ ያደረገላቸውን ነገር ረስተው በዲያብሎስ የሐሰትና የማስመሰል ምክር ተታለሉ፡፡ ከዚያም ከፍሬው ቆርጠው በሉ፤ ሞትንም ሞቱ፤ ገነትን ያህል ቅዱስ ሥፍራ፤ እግዚአብሔርን ያህል ኃያል ፈጣሪ አስከፉ፡፡

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሰይጣን በማስመሰል ርኅራኄው ሰዎችን እያባበለ ኃጢአት ሲያሠራ እና ከአምልኮተ እግዚአብሔር ሲለይ ኖረ፡፡ ሰይጣን ሰዎችን የሚያስትበት መንገድ ረቂቅ፣ እንደየዘመኑ ሁኔታም ተለዋዋጭ ነው፡፡ ሰይጣን ሰውን ሊያስት ሲመጣ እኔ ሰይጣን ነኝ፣ እነሆ ላስታችሁ መጥቻለሁ ተዘጋጅታችኋልን? ብሎ አይመጣም፡፡ ሰዎችን፣ ጊዜን፣ ሁኔታንና ቦታን ምክንያት እያደረገ በማታለያ ንግግሩ ቀርቦ በማስመሰል ሰዎችን ሸንግሎ ያስታል፡፡ የሰይጣን የማስመሰል ርኅራኄው የቱን ያህል አሳሳች እንደሆነ እንኳን አንረዳውም፡፡ ካሳተን በኋላም ያሳተን እርሱ መሆኑን መረዳት እየተሳነን ለውድቀታችን ሰዎችን፣ ዕድልን፣ ሁኔታዎችን እና ጊዜን ሰበብ እንድናደርግ ያደርገናል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው በተለይ በየጠበሉ ‹‹እከሊት ናት መድኃኒት ያደረገችብሽ፤ እከሌ ነው መድኃኒት ያደረገብህ›› እያለ ራሱን ሲያጋልጥ የምንሰማው የሰዎች ታሪክ እማኝ ነው፡፡ ‹‹ሐሰተኛ ነውና፤ የሐሰት አባትም ነው›› እንደተባለው፡፡ (ዮሐ. ፰፥፵፬) በዚህ ሐሰተኛነቱም አንዳንዶችን የአጋንንቱን ምስክርነት አምነው እንዲካሰሱ ባስ ሲል ወደከፋ ነገር እንዲደርሱ ያደርጋቸዋል፡፡

የሰይጣንን የማስመሰል ርኅራኄው አለማወቃችን ለጊዜ ከሚደርስብን ውድቀት በተጨማሪ በተደጋጋሚና በተመሳሳይ በኀጢአት እንድንወድቅ ያደርገናል፡፡ እርሱ ዘወትር እኛን በድካማችን ለማሳት አይሰለችምና እኛም እርሱ በእንዴት ያለ የማስመሰል ርኅራኄ ቀርቦ እንደሚያስተን ልናውቅበት እና ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡

#ዛሬ_ላይ_ሰይጣን_እንዴት_ባለ_የማስመሰል_ርኅራኄው_ሰውን_እየጣለ_ነው?

ሀ/ ለራሳችን በምንሰጠው የተሳሳተ ግምት የተነሣ

ዲያብሎስ ትሕትናን ስለሚፈራ ሰዎች ለራሳቸው ከፍ ያለ የተሳሳተ ግምት እንዲኖራቸው ለማድረግ የሰዎችን አንደበት እየተጠቀመ ‹‹አንተ እንዲህ ነህ፤ አንች እንዲህ ነሽ›› እያለ በተሳሳተ መንገድ ይመራል፡፡ ዲያብሎስ ወጣቶችን ለማሳት ‹‹አንተ ወጣት አይደለህ?፤ በዕድሜህ ተዝናና›› በማለት በመዝናናት ውስጥ ያለውን ድቀት በመሸሸግ ለእነርሱ የራራ መስሎ ይመክራል፡፡ እኅቶቻችንን ‹‹አንቺ ወጣት አይደለሽ በዕድሜሽ አጊጪ››፤ ‹‹እግዚአብሔር ልብን ነው የሚያየው›› በማለት የምንዝር ጌጥ እንዲያጌጡ እና ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን ውጪ እንዲሆኑ በማድረግ ባላሰቡትና ባልገመቱት መንገድ በፈተና እንዲወድቁ ያዳርጋቸዋል፡፡

የአንዳንድ ሰዎችን አንደበት እየተጠቀመ ዲያብሎስ መንፈሳውያንን ‹‹አንተ የእግዚአብሔር ሰው፣ አንቺ የእግዚአብሔር ሰው፣ ቅን ሰው፣ የዋህ ሰው፣ ጸሎተኛ ነህ፤ ጸሎተኛ ነሽ፤ ጾመኛ ነው፤ ጾመኛ ናት›› በማለት ልባችን ውስጥ ትዕቢት እንዲፈጠር ያደርጋል፤ እያታለለም የሌለንን ቅድስና ያለን እንዲመስለን ያደርገናል፤ በፍጻሜያችንም መንፈሳዊ ተጋድሎዋችን ላይ ድል ይነሣናል፤ ከዚያም በኋላ በቀላሉ በኃጢአት ይጥለናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ጌታችንን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጠቅሶ ሊፈትነው እንደሞከረው መንፈሳውያንንም ‹‹እነሆ፥ ጊንጦችንና እባቦችን፥ የጠላትንም ኃይል ሁሉ ትረግጡ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠኋችሁ፤ የሚጎዳችሁም ምንም የለም›› (ሉቃ. ፲፥፲፱) በማለት ራሳቸውን ከአደጋና ከወረርስኝ እንዳይጠብቁ፣ በሕይወታቸው ላይ ያላቸውን ድርሻ አስረስቶ ሳያውቁት እግዚአብሔርን እንዲፈታተኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ጌታችን በዲያብሎስ በተፈተነ ጊዜ ዲያብሎስ ወደ ቅድስቲቱ ከተማ ወሰደውና በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ ‹‹ስለ አንተ መላእክቱን ያዝልሃል፤ እግርህንም በድንጋይ እንዳትሰነካከል በእጃቸው ያነሡሃል፤ ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ወደታች ራስህን ወርውር አለው፡፡ ኢየሱስም ጌታ አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው፡፡›› (ማቴ ፬፥፮-፰) ዲያብሎስ በእምነታችን የጸናን እንዲመስለን በማድረግ የእግዚአብሔርን ጠብቆት እንድንፈታተን ያደርገናል፡፡

ባለጸጎችን ሀብትን የሰጠ እግዚአብሔር መሆኑን፤ በተገቢውም ሥርዓት ሊያስተዳድሩ እንደሚገባና በሀብት በንብረታቸው ላይ በእግዚአብሔር የተሾሙ መሆናቸውን ያስረሳቸዋል፡፡ ለድሆች ጥቂት ነገር ሲመጸውቱ፣ ለቤተክርስቲያን ሲረዱ፣ መመስገንን አጥብቀው እንዲሹ የማይገባቸውን ክብር እንዲመኑ ያደርጋቸዋል፡፡ የሰዎችን አንደበት እየተጠቀመ ‹‹የአንተ ቤት የአብርሃም ቤት ነው፤ እስኪ ሌሎችን ባለጸጎች ተመልከት! ንፉጎች ናቸው›› እያለ ራሱን ከአብርሃም ጋር እያነጻጸረ ለራሱ ያልተገባ ክብር እንዲሰጥ እያደረገ በከንቱ ውዳሴ ይጥላቸዋል፡፡

አገልጋዮችን ‹‹አንተ ስትቀድስ፣ አንተ ስትሰብክ፣ አንተ ስትዘምር ይደምቃልና ጠጠር መጣያ ይጠፋል›› እያስባለ አገልጋዮች እያገለገሉ የሚገለገሉ መሆናቸውን ያዘናጋቸዋል፡፡ አንዳንዴ ከንቱ ውዳሴን ሳያውቁት እንዲሹ ያደርጋቸዋል፡፡

ለ/ ወቅታዊ የሀገር ሁኔታዎችን በመጠቀም

ዲያብሎስ አጥብቆ ከሚጠላው አንዱና ዋነኛው ነገር የሰውን በአንድ ልብ በአንድ ሀሳብ ሆኖ እግዚአብሔርን ማምለክ ነው፡፡ ስለዚህም ሰዎችን የሚለያዩ ልዩ ልዩ መንገዶችን ይጠቀማል፡፡ መገኛችን አባታችን አዳም መሆኑን አስዘንግቶ ሰዎች በብሔር በመከፋፈል በሰዎች መካከል ልዩነትን እንዲፈጠር አድርጎ የባላጋራነት ስሜትን ይፈጥራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰዎች በሚሰሙትና በሚናገሩት ቋንቋ መገልገልና ማገልገል የተከለከለ አስመስሎ ‹‹ለምን በቋንቋዬ አይሰበክም እና አይቀደስም›› በሚሉ ሀሳቦች ነገር ግን በውስጣቸው ምእመናን ከመንጋውና ከእረኛ አባቶች የመለየት ሥውር ተልዕኮውን ይፈጽማል፡፡
,,,,,,,,,

ይቀጥላል

ሐ/ #ዓለማዊ_አስተሳሰቦችን_መንፈሳዊ_በማስመሰል,,,,,,,,,
#ከዲያብሎስ_የማስመሰል_ርህራሔው_እንዴት_እንጠንቀቅ?,,,,,,,
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
230 viewsDaniel dendir ጎዶሊያስ 28 .., 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 14:49:48 ግን ሚካኤል ሆይ

በአውላላ ሜዳ በጠራራ ፀሐይ
ከአስፓልቱ አጠገብ ስኖር ጎዳና ላይ
የበጋውን ንፋስ በዙሪያዬ ከቦኝ
እንደ ዥዋዥዌ ወዲያ ሲወስደኝ፡፡
...................ወዲህ ሲመልሰኝ

ዝናቡ በተራው ጉዴን ተመልክቶ
...................ጉድፌን አፅድቶ
ይወደኝ ይመስል ልብሴን ያጥብልኛል
ጎጆዬን አፈራርሶ በብርድ ይገርፈኛል፡፡

ከዚህ የባሰ ግን ሰዉ ነው 'ሚገርመኝ
በነጋ በጠባ መተንፈሻ ያሳጣኝ፡፡

ስለተናገርኩኝ ማጣት መከፋቴ
የእውነት ስለኖርኩኝ ውሸትን ጠልቼ
አፋቸውን ሞልተው እብድ ነው ይሉኛል
አንዳንዴ ሲያሻቸውም ድሃ ነው ይሉኛል፡፡

የሆነው ሆነና ቅር አላለኝም
አጣሁኝ ብዬም አላማረርኩም
ጌታ እንዳስተማረኝ ለበጎ ነው ብዬ
የማይቻል የለም እኖራሎህ ችዬ፡፡

ይሄውልህ ግን ሚካኤል ሆይ...
የሰው ልጅ ሲሸሸኝ ማንነቴን አይቶ
ሰላምታ ሲነፍገኝ ኑሮዬን ተመልክቶ
አንተ ግን አንተ ነህ የአምላክ መልእክተኛ
ሁሌ  'ምትጠብቀኝ መቼም የማተኛ፡፡
ምንም ሳይገድብህ ከቤቴ ገብተሀል
ድሃዋን ጎጆዬ በፍቅር ጎብኝተሀል፡፡

እናም ሚካኤል ሆይ....
ከኔ እንዳትርቅ ስለሳሳሁልህ
በንፁህ ልቤ ውስጥም ጎጆ ቀለስኩልህ፡፡

✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
258 views𝑛𝑒𝑡𝑠𝑎𝑛𝑒𝑡 𝑙𝑒𝑚𝑚𝑎, 11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 08:36:32 ✟......"ጌታ ሆይ....
አንተ.... #ቃል፣ #ሕሊናና #ልቡና ነህና ስለ አንተ የሚናገር ሁሉ በአንተ አነሳሽነት ይናገራል። የልብ አሳቦችም ካላንተ አይቀሰቀሱም፤ ቃላትም ባንተ ካልሆነ በቀር ከናፍርትን አያንቀሳቀሱም። ከናፍርት ካላንተ ትዕዛዝ ድምፅን አያወጡም፤ ማድመጥም ካለፈቃድህ ለጆሮ አይሆንለትም።..... ሁሉም በአንተ ባለጸጋ ነው፤ አንተም ሁሉንም ካለ ቅድመ ሁኔታ ባለጸጋ ታደርጋለህ። #ንግግሬ_ውበት_እንዲኖረው_በአንተ_ጸጋ_ይመላ፤ #መናገሬ_ላንተ_ይሁን።

#የድንግል_ልጅ_ሆይ፣ #ስለ_እርሷ_የሚነገር_ቃል_በእኛ_ዘንድ_እጅግ_የከበረ_ነውና_ስለ_እናትህ_እናገር_ዘንድ_ጸጋውን_አድለኝ።"......✟

✥✥✥ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ✥✥✥
309 viewsA𝑠ℎ𝑒𝑛𝑎𝑓𝑖 A𝑘𝑙𝑖𝑙𝑢, 05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 20:50:13
"ድካሜንና ውድቀቴን አውቃለሁ። በራሴ መንገድ ኃጢአትን ለመተው ሞክሬአለሁ። አሁን በሕይወቴ አንተ ጣልቃ ትገባ ዘንድ ያስፈልጋል። እኔ በራሴ ኃይል ኃጢአትን መተው አልቻልኩምና።"

በልብ መታሰቡ፣ በቃል መነገሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም" ያለን። ያለእርሱ ምንም ማድረግ ስለማንችል ነው። ንስሐ መግባት፣ መጸለይ፣ መጾም፣ ከቅዱሳት ምሥጢራት መሳተፍ በአጠቃለይ ከኃጢአትን ነጽተን በንጽሕና መኖርን እንፈልጋለን። ማሳካት የምንችለው ግን በእርሱ በእግዚአብሔር ነው። ስለዚህ የጸሎታችን ይዘት የእኛን አለመቻል የእግዚአብሔርን ከሀሌ ኩልነት የሚገልጥና በተሰበረ ልቡና በትሑት ቃል ሊኾን ይገባዋል። ያን ጊዜ ከእርሱ ጋር በእርሱ ሀሳብና ፈቃድ እንኖር ዘንድ ያድለናል።
"በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?" ዘፍ፲፰
ዲ/ን ሳሙኤል በላቸው
ሐምሌ ፲ ፳፻፲፬ ዓም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
https://t.me/Amdehaymanotzeortodoxtewahdo
297 views𝑛𝑒𝑡𝑠𝑎𝑛𝑒𝑡 𝑙𝑒𝑚𝑚𝑎, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 08:13:59 ስለ ግእዝ አኃዝ ( ቁጥሮች )

የግእዝ ቁጥሮችን በዝርዝር ጽፈን መጨረስ ባንችልም ከብዙ በጥቂት እንመልከት


አኀዝ በፊደል - በዓረብኛ - በአማርኛ

(አልቦ) 0 (ዜሮ)

፩ (አሐዱ) 1 (አንድ)

፪ (ክልኤቱ) 2 (ሁለት)

፫ (ሠለስቱ) 3 (ሶስት)

፬ (አርባዕቱ) 4 (አራት)

፭ (ኃምስቱ) 5 (አምስት)

፮ (ስድስቱ) 6 (ስድስት)

፯ (ሰብዓቱ) 7 (ሰባት)

፰ (ሰመንቱ) 8 (ስምንት)

፱ (ተስዐቱ) 9 (ዘጠኝ)

፲ (ዐሠርቱ) 10 (አስር)

፳ (እስራ) 20 (ሃያ)

፴ (ሠላሳ) 30 (ሠላሳ)

፵ (አርባ) 40 (አርባ)

፶ (ሃምሳ) 50 (ሃምሳ)

፷ (ስሳ) 60 (ስድሳ)

፸ (ሰብዓ) 70 (ሰብዓ)

፹ (ሰማንያ) 80 (ሰማንያ)

፺ (ተስዓ) 90 (ዘጠና)

፻ (ምእት) 100 (መቶ)

፲፻ (ዐሠርቱ ምእት) 1000 (አንድ ሺህ)

፼ (እልፍ) 10,000 (አስር ሺህ)

፲፼ (ዐሠርቱ እልፍ) 100,000 (መቶ ሺህ)

፼፻ (አእላፋት) 1000,000 (አንድ ሚሊየን)

፲፼፻ (ትእልፊት) 10,000,000 (አስር ሚሊየን)

፻፼፻ (ትልፊታት) 100,000,000 (መቶ ሚሊየን)

፲፻፼፻ (ምእልፊት) 1,000,000,000 (አንድ ቢልየን)


#ቁጥሮች
፩፪፫፬፭፮፯፰፱፲



https://t.me/Amdehaymanotzeortodoxtewahdo
357 views𝑛𝑒𝑡𝑠𝑎𝑛𝑒𝑡 𝑙𝑒𝑚𝑚𝑎, 05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 08:09:14 ስለ ግእዝ ፊደላት

የግእዝ ፊደላት ከሌሎች ቋንቋዎች ፊደል የሚለየው ፊደላቱ እያንዳንዳቸው የራሳቸው ትርጉም ስላላቸው ነው።
ለምሳሌ፦


ሀ - ማለት የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው፡፡
- ብሂል ሀልዎቱ ለአብ እም ቅድመ ዓለም።

ለ - ማለት የእኛን ሥጋ ለበሰ።
- ብሂል ለብሰ ሥጋ ዚአነ።

ሐ - ማለት ስለእኛ ታሞ ሞተ።
- ብሂል ሐመ ወሞተ በእንቲአነ።

መ - ማለት የእግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው፡፡
- ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር።

ሠ - ማለት ከድንግል በሥጋ ተወለደ(ተገለጠ)
- ብሂል ሠረቀ በሥጋ እምድንግል፡፡

ረ - ማለት በጥበቡ ፤ ሰማይና ምድር ረጋ።
- ብሂል ረግዓ ሰማይ ወምድር፡፡

ሰ - ማለት እንደእኛ ሰው ሆነ።
- ብሂል ሰብአ ኮነ ከማነ።

ቀ - ማለት በመጀመሪያ ቃል ነበረ።
- ብሂል ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ።

በ - ማለት ለዓለም ሁሉ ቤዛነት በትሕትናው ወረደ፡፡
- ብሂል በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኩሉ ዓለም።

ተ - ማለት ፍፁም ሰው ሆነ።
- ብሂል ተሰብአ ወተሰገወ።

ኀ - ማለት ራሱን (ባህሪውን )ሰወረ (ሸሸገ)
- ብሂል ኀብአ ርእሶ።

ነ - ማለት ደዌያችንን ያዘል ሕማማችንንም ተሸከመልን።
- ብሂል ነስአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ።

አ - ማለት እግዚአብሔርን ፈፅሞ አመሰግነዋለሁ።
- ብሂል አአኲቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር።

ከ - ማለት እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው፡፡
- ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር።

ወ - ማለት ከሰማያት ወረደ።
- ብሂል ወረደ እምሰማያት።

ዐ - ማለት እግዚአብሔር ታላቅ ነው።
- ብሂል ዐቢይ እግዚአብሔር።

ዘ - ማለት እግዚአብሔር ሁሉን የሚይዝ (የሚገዛ ነው)።
- ብሂል ዘኲሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር።

የ - ማለት የእግዚአብሔር ቀኝ ኀይልን አደረገች።
- ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኀይለ።

ደ - ማለት መለኮቱን ከሥጋችን ጋር አንድ አደረገ።
- ብሂል ደመረ መለኮቶ ምስለ ሥጋነ፡፡

ገ - ማለት ምድርና ሰማያትን የፈጠረ ነው፡፡
- ብሂል ገባሬ ሰማያት ወምድር።

ጠ - ማለት እግዚአብሔር ጠቢብ ነው፡፡
- ብሂል ጠቢብ እግዚአብሔር።

ጰ - ማለት ጰራቅሊጦስ የእውነት መንፈስ ነው፡፡
- ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ፡፡

ጸ - ማለት እግዚአብሔር ጸጋና እውነት ነው።
- ብሂል ጸጋ ወጽድቅ እግዚአብሔር፡፡

ፀ - ማለት እግዚአብሔር የእውነት ፀሐይ ነው።
- ብሂል ፀሐየ ጽድቅ እግዚአብሔር፡፡

ፈ - ማለት በጥበቡ ዓለምን ፈጠረ።
- ብሂል ፈጠረ ዓለመ በጥበቡ።

ፐ - ማለት የእግዚአብሔር ስሙ ፓፓኤል ነው፡፡
- ብሂል ፓፓኤል ስሙ ለእግዚአብሔር።


ይቀጥላል...
#ፊደሎች

https://t.me/Amdehaymanotzeortodoxtewahdo
327 views𝑛𝑒𝑡𝑠𝑎𝑛𝑒𝑡 𝑙𝑒𝑚𝑚𝑎, 05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 03:27:30
"እግዚአብሔር ይሬእየኒ፤
ወአልቦ ዘየኃጥአኒ፤" መዝ ፳፪፥፩
289 views𝑛𝑒𝑡𝑠𝑎𝑛𝑒𝑡 𝑙𝑒𝑚𝑚𝑎, 00:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 09:08:58 ምን ፍሬ አፈራን ?

ልጆቼ ! እስኪ ፍቀዱልኝና አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ። ብዙውን ጊዜ ቤተክርስቲያን ትመላለሳላችሁ። መልካም ነው ። ግን ምን ለውጥ አመጣችሁ ? ምን ፍሬ አፈራችሁ ? ታገለግላላችሁን ? ታዲያ ከአገልግሎታችሁ ምን ረብሕ አገኛችሁ ? ጥቅምን ካገኛችሁ በእውነት ምልልሳችሁ የብልህ ሰው ምልልስ ነበር ማለት ነው።

ነቢያት ፣ ሐዋርያት ፣ ወንጌላውያን እንዲህ እያስተማሩን ሳለ የማንለወጥ ከኾነ ግን የእስከ አሁን ምልልሳችን የአይሁድ ምልልስ ነበር ማለት ነው። አይሁዳውያን ሕገ ኦሪት የተሰጠቻቸው ኃጢአታቸውን በእርሷ መስታወትነት ዐይተው ንስሐ እንዲገቡባት ነበር። እነርሱ ግን የንስሐ ፍሬ ሳያፈሩባት እንዲኹ ይመኩባት ነበር። ስለኾነም ለሕይወት የተሰጠቻቸውን ሕግ ሞት ኾና አገኟት። እኛም እንዲህ ለኩነኔ ያይደለ ለጽድቅ የተሰጠችን ወንጌል ፍሬ የማናፈራባት ከኾነ ከአይሁዳውያን የባሰ ቅጣት ትፈርድብናለች።

እስኪ ምሳሌ መስዬ ላስተምራችሁ። አንድ የሚታገል ሰው በየጊዜው ተጋጣሚውን እንደ ምን ማሸነፍ እንዳለበት ልምምድ የሚያደርግ ከኾነ ክህሎቱ ይዳብራል። ተጋጣሚውንም በቀላሉ ማሸነፍ ይቻለዋል። በየጊዜው የሚያነብና ራሱን የሚያሻሽል ሐኪም ጐበዝ ዐዋቂና ሕመምተኞችን በአግባቡ የሚረዳ ይኾናል። በየቀኑ ቃሉ የሚነገረን እኛስ ምን ለውጥ አመጣን ? ምንስ ፍሬ አፈራን ?

እየተናገርኩ ያለሁት ለአንድ ዓመት ብቻ በቤተክርስቲያን የቆዩትን ምእመናን አይደለም። እየተናገርኩ ያለኹት ከልጅነታችን አንሥተን በቤቱ ለምንመላለስ እንጂ። ይህን ያህል ዘመን በቤቱ እየተመላለስን ፍሬ ካላፈራን ቤተክርስቲያን ደርሰን ብንመጣ ምን ጥቅም አለው ? አባቶቻችን አብያተክርስቲያናትን ያነጹልን ለምንድን ነው ? ዝም ብለን እንድንሰባሰብ ነውን ?
መሰባሰቡንማ በገበያ ቦታም መሰባሰብ እንችላለን ።
አበው አብያተክርስቲያናትን ያነጹልን ቃሉን እንድንማርበት ፣ በተማርነው ቃልም የንስሐ ፍሬ እንድናፈራበት ፣ ሥጋ ወደሙን እንድንቀበልበት ፣ ርስ በርሳችን እንድንተራረምበት ነው እንጂ ለሌላ አይደለም ። ታዲያ ምን ፍሬ አፈራን ?


#ሰማዕትነት አያምልጣችሁና ሌሎችም በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
365 viewsA𝑠ℎ𝑒𝑛𝑎𝑓𝑖 A𝑘𝑙𝑖𝑙𝑢, 06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ