Get Mystery Box with random crypto!

ግን ሚካኤል ሆይ በአውላላ ሜዳ በጠራራ ፀሐይ ከአስፓልቱ አጠገብ ስኖር ጎዳና ላይ የበጋውን ንፋ | 💠አምደ ሐይማኖት💠ዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ⛪️

ግን ሚካኤል ሆይ

በአውላላ ሜዳ በጠራራ ፀሐይ
ከአስፓልቱ አጠገብ ስኖር ጎዳና ላይ
የበጋውን ንፋስ በዙሪያዬ ከቦኝ
እንደ ዥዋዥዌ ወዲያ ሲወስደኝ፡፡
...................ወዲህ ሲመልሰኝ

ዝናቡ በተራው ጉዴን ተመልክቶ
...................ጉድፌን አፅድቶ
ይወደኝ ይመስል ልብሴን ያጥብልኛል
ጎጆዬን አፈራርሶ በብርድ ይገርፈኛል፡፡

ከዚህ የባሰ ግን ሰዉ ነው 'ሚገርመኝ
በነጋ በጠባ መተንፈሻ ያሳጣኝ፡፡

ስለተናገርኩኝ ማጣት መከፋቴ
የእውነት ስለኖርኩኝ ውሸትን ጠልቼ
አፋቸውን ሞልተው እብድ ነው ይሉኛል
አንዳንዴ ሲያሻቸውም ድሃ ነው ይሉኛል፡፡

የሆነው ሆነና ቅር አላለኝም
አጣሁኝ ብዬም አላማረርኩም
ጌታ እንዳስተማረኝ ለበጎ ነው ብዬ
የማይቻል የለም እኖራሎህ ችዬ፡፡

ይሄውልህ ግን ሚካኤል ሆይ...
የሰው ልጅ ሲሸሸኝ ማንነቴን አይቶ
ሰላምታ ሲነፍገኝ ኑሮዬን ተመልክቶ
አንተ ግን አንተ ነህ የአምላክ መልእክተኛ
ሁሌ  'ምትጠብቀኝ መቼም የማተኛ፡፡
ምንም ሳይገድብህ ከቤቴ ገብተሀል
ድሃዋን ጎጆዬ በፍቅር ጎብኝተሀል፡፡

እናም ሚካኤል ሆይ....
ከኔ እንዳትርቅ ስለሳሳሁልህ
በንፁህ ልቤ ውስጥም ጎጆ ቀለስኩልህ፡፡

✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞