Get Mystery Box with random crypto!

Amde Ezra

የቴሌግራም ቻናል አርማ amde123 — Amde Ezra A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amde123 — Amde Ezra
የሰርጥ አድራሻ: @amde123
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.51K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃ መስመር

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-02-10 19:35:19 #ቅዱስ_ሲኖዶስ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት አጭር መግለጫ ከተናገሩት የተወሰደ

" ... ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በደንብ አውርተናል።

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችን መሪነት በመንፈሳዊ ግርማ ፣ በቤተክርስቲያኒቱ ታላቅ ክብር ሆነን እግዚአብሔርም አክብሮን ብዙ ጥያቄዎቻችን ተመልሰዋል እነዛን አጠቃላይ ነገ ነው የምንገልፀው። የነበረን ጥያቄ አጠቃላይ በመንግስት ፣ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩም እንዲሁም በሌሎች እዛ ባሉት ተገቢ ጥያቄ እንደሆነ ተገንዝበዋል።

ስለዚህ ጉዳይ ነገ በሰፊው እንገልፃለን። የተገኘውን ውጤትም አጠቃላይ ነገ በሰፊው እንገልፃለን።

ዛሬ ይሄን አጭር መግለጫ ለመስጠት የወደድነው ምእመናኖቻችን ህዝባችን ስለሚጠብቅ ፤ ህዝባችን ምንም ከቆምንበት ዓላማ ወደኃላም ሆነ ወደፊት እንዳላልን ሁል ጊዜ የህገ ቤተክርስቲያን አቋም የፀና እንደሆነ፣ የቀኖና ቤተክርስቲያን የፀና እንደሆነ ይሄንን ለማረጋገጥ ነው።

ይሄ መፍትሄ እስካላገኘ ድረስ ተጋድሏችን ይቀጥላል። ስለዚህ ምእመናንን ወገኖቻችን ስለምታደርጉ የፀሎት ፣ የምክር አጠቃላይ የሞራል ድጋፍ በቤተክርስቲያን ስም እናመሰግናለን፤ እግዚአብሔር ይስጥልን።

በፀሎት ትጉ፣ በምዕላ ትጉ ፤ እግዚአብሔር ፀሎታችንን ሰምቷል ፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው አንዳንድ የምሰማቸው እና የምናያቸው ነገሮች ስላሉ ነው ዛሬ ጠቅላላ መግለጫ ያላወጣነው።

ነገ ጥዋት 3 ሰዓት ላይ መግለጫ እንሰጣለን። "
1.3K views16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 18:42:28
1.4K views15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 18:42:08 "ነገ ጠዋት 3:00 ላይ አጠቃላይ መግለጫ እንሰጣለን..."


"ዛሬ ከጥቅላይ ሚኒስተሩ ጋር በደንብ አውርተናል። ብዙ ጥያቄዎቻችን ተመልሰዋል። እነዚህን አጠቃላይ ነገ ጠዋት 3:00 ላይ እንገልጻለን። እግዚአብሔር ጸሎታችን ሰምቷል።"

ብጹዕ አቡነ ጴጥሮ አሁን ከሰጡት አጭር መግለጫ የተወሰደ።
1.4K views15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 17:25:57 "የችሎት ውሎ በተመለከተ መልካም ዜና አለ!
በተለመዱት ሚዲያዎች ከአፍታ ደቂቃዎች በኋላ ጠብቁን!"

በማለት

ጠበቃና የህግ አማካሪ Andualem Buketo Geda አስታውቋል።
1.6K views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 17:04:32 "ሰበር ዜና"

"እንዲህ ተወሰነ፣ እንዲያ ተወሰነ" እያሉ ሰበር ዜና የሚሉትን አሁንም መስማት የለብነም። ብዬ አስባለሁ። መስማት ያለብን አባቶቻችን በይፋ የሚሰጡትን መግለጫ ብቻ ነው። በእርግጥ በሰበር ዜና የመጡት ወገኖች የዜናቸው እውነትነት ሊኖረውም ይችላል። ቢሆንም ግን በአባቶቻችን ሳይገለጽና በአባቶቻችን ሳይረጋገጥ "ሰበር ዜና" እያሉ መረጃ መልቀቅ አንድም የአባቶቻችንን ቃል እንደ ማስተሃቀር ወይም እንደመናቅ ይቆጠራል። ሁለትም ነገሩ ከተባለው በግልባጩ ከሆነ ሌላ ችግር ይፈጥራል። በእዝና ሰንሰለት የሚመራ ትግል ምን እንደሚፈጥር ሰሞኑን የተገነዘብንም ይመስለኛል። እናም እንቆጠብ ባይነኝ።

፩ ቅድስት ቤተክርስቲያን
፩ ቅዱስ ሲኖዶስ
፩ መንበረ-ፓትርያሪክ
1.7K viewsedited  14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 15:32:09 የመንግስት ሚዲያዎች...

ቅድስት ቤቴክርስቲያን ችግር ውስጥ ገብታ፣ ምዕመኖቿ በጾም፣ በጸሎት ማቅለብሰው፣ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች እየተገደሉ፣ እየተደበደቡ፣ እየታሰሩ፣ የአቢያተ-ክርስቲያናት በሮች እየተሰበሩ...ባላዬ ባልሰማ ላሽ ሲሉ የሰነበቱ እነ ኢትቪ፣ እነ ፋና፣ እነ ዋልታ...

ግን ዛሬ "የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አቢይ አህመድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሐይማኖት አባቶች ጋር ተወያዩ" አይነት ዜናዎችን የሚያሰደምጡን ይመስለኛል? ኧረ እንዲያውም መግለጫም ሊያነቡልን ይችላሉ።

ግራም ነፈሰ ቀኝ የሚዲያዎቹ ልሳን ተዘግቶ መሰንበቱ ገርሞኝና እንድታዘብ አዳርጎኝ እንጂ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ገጥሟት የነበረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከአባቶች ጋር ስምምነት ተደረሰ" ብለው ቢያበስሩን በበኩሌ ደስታየ ወደር አይኖረውም። በሚዲያዎቹ ላይ ያለኝን ትዝብት ግን አይሽረውም።

ቼር ያሰማን

፩ ቅድስት ቤተክርስቲያን
፩ ቅዱስ ሲኖዶስ
፩ መንበረ-ፓትርያሪክ
1.9K viewsedited  12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 14:09:25
2.0K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 14:09:18 አባቴ ሃቀኛ መሪ ያለው ትግል ምን አይነት ለውጥ እንደሚያመጣ ሰሞኑን የተመለከት ይመስለኛል? ከዳር...ዳር ህዝብን እንዴት እንዳነቃነቀ፣ መንግስትን እንዴት እንዳስጨነቀ የተገነዘብክ ይመስለኛል?

ምን ለማለት ነው በአሁን ሰአት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ከብጹአን አባቶች ጋር እየተወያየ ነው። አሁንም የአባቶቻችንን ትዕዛዝ ብቻ እንጠብቃለን። ከእነሱ ውጭ የምንሰማው የለም።

፩ ቅድስት ቤተክርስቲያን
፩ ቅዱስ ሲኖዶስ
፩ መንበረ-ፓትርያሪክ
1.9K viewsedited  11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 13:49:29
1.9K views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 13:49:18 ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የላኩት መልእክት
1.7K views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ