Get Mystery Box with random crypto!

Amde Ezra

የቴሌግራም ቻናል አርማ amde123 — Amde Ezra A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amde123 — Amde Ezra
የሰርጥ አድራሻ: @amde123
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.51K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃ መስመር

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-02-04 19:42:50
2.9K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 19:42:46 ለአንድ ትልቅ አባቴ 'እኔን ደካማውን ዝቅ ብዬ ይስሙኝ እስቲ' ያልኳቸውን...

"የጫካው ሲኖዶስ" ወይም የፌድራሊስት ኃይሉ አሊያም ደግም "ኦነግ ሸኔ በመስቀል" ስም ዓላማው እንዳይሳካ በማስላት አንድ ለምቀርባቸው የሐይማኖት አባት ቢደረግና ባይደገም ብዬ ያዋራኋቸውንና ይጥቅማል ያልኩትን ብቻ ለሌሎች አባቶች ይደርሳል ብዬ ተስፋ በመሰነቅ እንዲሚከተለው አጠር አድርጌ አቅርበዋለሁ።

1ኛ በፖለቲካው ዓለም ጎልተው የወጡ፣ በተለይ ዋልታ እረገጥ ሃሳብ ያለቸው ሰዎች (ብሔርተኞች) "ኦርቶዶክን እንታደጋለን" በሚል እና በሚዲያው ፊት አውራሪ ሆነው የመጡ ግለሰቦችን የሐይማኖት አባቾች መክረውና ዘክረው ከኋላ እንዲሆኑ ቢያደርጉ። ምክንያቱ ግልጽ ነው። ፖለቲከኞቹ የተሳሉበት ፖለቲካዊ ስዕል ስላለ ነው። የፖለቲካዊ ርዕዮተ-ዓለም አጥር፣ ዘር፣ ደንበር፣ ቀለም፣ ብሔር...የማትለየውን ዓለም አቀፋዊቷን ኦርቶዶክስን በፖለቲካ ስዕላቸው ምክንያት አጥር እንዳያስጥሩባት በመስጋት ነው። ይህን የምለው የኦርቶዶክሳዊያንን አንድነት ለማጠናከር በማሰብ ነው። የጫካው ሲኖዶስ እኩይ ዓላማ በእንጭጩ እንዲከሽፍ ያደርጋል ከሚል ስሌት ነው።

2ኛ ብሔርን በጅምላ ፈርጀው ሲሳደቡ የሚውሉ ግለሰቦችን፣ ዩቱዩቨሮች...ቤትክርስቲያኒቱን ለማዳን ያለመውን የተቀደሰ ትግል ከፊት ቀድመው ወይም ጠለፈው የመጡትን እረፉ ቢባሉ። በተለይ እንደ እነ ቀዌ ዘመድኩን በቀለ አይነቶቹ...

3ኛ ዓለም አቀፋዊቷን ኦርቶዶክስን የአማራ ህዝብ ሐይማኖት ብቻ አስመስለው ስዕል እየፈጠሩ ያሉትን ኃይሎች እንዲመከሩ ቢያደርጉ።

4ኛ በቀጣይ ኦርቶዶክስን ለመታደግ ሰላማዊ ትግሎች እንደሚደረጉ ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል። ሰላማዊ ሰልፎችን ጨመሮ ማለት ነው። እናም ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ የቤትክርስቲያኒቱን ዓርማ ብቻ ተይዞ እንዲወጣ ቢደረግ። በዚሁ ሳምንት በአሜሪካን አገር ዋሽንግተን ዲሲ የተካሄደውን ሰልፍ አይተናል። በዚህ ሰልፍ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ፣ የህወሃት ባንዴራ፣ የአሜሪካ አርማ ጭምር አንድ ላይ ሲውለበለቡ ተመልክተናል። የሰንደቅ ዓላማውም ሆነ የባንዴራዎቹ በሰልፉ በአንድ ላይ መውለብለባቸው የተዛባ ትርጉም ለመስጠት አመች ይሆናል። በተለይ ኦርቶዶክስ ለማጥፋት ላለሙ እኩያን ኃይሎች ግብአት ይሆናል ባይነኝ። የተቀደሰውን ሰለማዊ ትግል ከፖለቲካ ጋር እንዲያይዙት በር ከፈች የሚሆን ይመስለኛል? እናም ከባለፈው ትምህርት ተወስዶ በቀጣይ የቤተክርሲቲያኒቱን ህጋዊ ዓርማ ብቻ እንዲያዝ ቢደረግ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታተርፋለች ባይነኝ።


ማስታወሻ:- ከላይ የገለጽኳቸውን ፖለቲከኞች ዩቱዩቨሮ... በተለይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆኑት የኦርቶዶክ ጉዳይ በቀናነት ካሰቡ አይመለከተው እያልኩ አይደለሁም። ከብፁዓን አባቶቻችን፣ በእየ ደረጃው ከላሉ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶችና አገልጋዮች በላይ ለእሱ የበለጠ እንደ ሚመለከታቸው አድርገው ጠርዝ ማሲያዝ አደጋ አለው ነው። ብሔር፣ ደንበር፣ ቀለም፣ ፖለቲካዊ አጥር፣ ቋንቋ፣ ዘር... የሌላትን ቅድስት ቤተክርስቲያን ግለሰቦቹ በተሳሉበት ፖለቲካዊ ምስል ወይም ፖለቲካዊ ውግንናቸው ምክንያት አጥር አስበጅተው እንዳያዳክሟት በመስጋት ነው። የኦርቶዶክሳዊያንን አንድነት በማጠናከር የጫካውን ሲኖዶስ ዓላማ በቀላሉ እንዳይሳክና እንዲኮላሽ ያደርጋል በማለት ነው።
2.8K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 17:04:35 የእነ አካለወልዱ ቡድን ወይም "የጫካው ሲኖዶስ" እንደገባኝ:-

1ኛ "የፌድራሊስት ኃይሎች" በማለት መቀሌ ላይ ትህነግ ሞክሮት የነበረው አይነት አምሳያ ነው። የእነ አካለወልድ ቡድን ልዩነቱ በሐይማኖት ስም መምጣቱና ጫካ ላይ መመስረቱ ነው።

2ኛ ሌላው "ኦነግ ሼኔ ከጠመንጃው በተጨማሪ በሐይማኖት ስም መስቀልም" ጭምር ጨብጦ መምጣቱን ያሳያል።

ማስታወሻ:- ኦርቶዶክስ ብሔር፣ ዘር፣ ቀለም፣ አጥር፣ ደንበር...የላትምና በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በግራም በቀኝም ያላችሁ ወገኖች ቅድስት ቤተክርስቲያንን የአንድ አካባቢ ሐይማኖት ለማስመሰል የምትጥሩ ለኦርቶዶክ ተጨማሪ ውድቀትን እንጂ ትንሣኤን አታመጡም። በመሆኑም እኔ ደካማውና ትንሹ፣ ሃጢአተኛውን አበቶቼ ይቅር በሉኝና ብፁአን አባቶች ኦርቶዶክን ለማጠር የሚጠሩትን ብትመክሩ ብትገስጹ ስል ዝቅ ብዬ ትዝብቴን አጋራለሁ። በተለይ እንደ እነ ቀዌ ዘመድኩን በቀለ አይነቶችን።
2.9K viewsedited  14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 14:56:54
3.2K views11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 14:56:45 አንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን!! አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ!! አንድ መንበረ ፓትርያሪክ!!
3.0K views11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 14:50:59
1.7K views11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 14:50:32 የዛሬ ዓመት በቦታው ነበርኩ። ተደስቼ፣ ተደምሜም ውዬ ነበር። ዘንድሮ ግን በግል ምክንያት መገኜት አልቻልኩም። ይሁን እንጂ በማማው ደብረታቦር (ጎንደር) አጅባር ሜዳ ላይ ሲካሄድ የዋለውን የፈረስ ጉግስ በዓል በኢትዮጵያ ተሌቪዥኝ (EBC) በቀጥታ ስርጭት ተከታትያለሁ። እጅግ የደመቀ ነበር። በቦታው ታድሜ ባለመዋሌ ቢቆጨኝም በዓሉ በደመቀ ሁኔታ በመከበሩ እጅግ ደስ ብሎኛል። ዓመታዊው የቅዱስ መርቆርዮስ በዓልና ባህላዊው የፈረስ ጉግስ ሥነ-ስርዓት እጅግ ደምቆና አምሮ ተከብሮ እንዲውል ጉልህ ሚና ላበረከታችሁ ወንድም፣ እህቶቼ በሙሉ በእጅጉ ልትመሰገኑ ይገባል።
1.7K views11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 14:29:58
1.7K views11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 14:29:51 ጀግና ከጀግና ጋር በማማው ደብረታቦር (ጎንደር)
1.7K views11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 15:32:56 የእኛ ቀይ መስመር ምንድ ነው?

የኤርትራ መንግስት የሚያስቀናኝ መርህ አለው። የማይደፈር ቀይ መስመር አለው።

1ኛ የኤርትራ ህዝብ
2ኛ የኤርትራ የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት
3ኛ የህግደፍ ስልጣን

ከአንድ እስከ ሶስት የዘረዘርኳቸው የኤርትራ መንግስት በጉልህ ያሰመራቸው ቀይ መስመሮች ናቸው። የማይጣሱና የማይገረሰሱ ሆነው እናገኛቸዋለን።

ግን ቀይመስመሩን አልፎ የተገኜ አካል ካለ "እሱን አያድርገው" ለምን የፕሬዝዳንት የኢሳይያስ አፈወርቂ ልጅ አይሆንም የእጁን ይሰጡታል። ለምን የአገሪቱ ከፈተኛ የጦር መኮንን አይሆንም ዋጋውን ያገኛታል። እንደ ኤርትራዊያን እምነት ዓላማ በውስጥ ባንዳ እየታመሰ ግቡን አይመታም እንዲያውም ይንኮላሻል፣ ይከሽፋል የሚል ጽኑ እምነት አላቸው። አንድ ሰው ያሰሙሩትን ቀይ መስመር ከጣሰ "ወንድሜ ነው፣ ልጄ ነው፣ ባለስልጣን ነው..." ብሎ ነገር የለም። ለዚህም ነው የኤርትራ መንግስት ያሰመረው ቀይ መስመር ያስቀናኛል፤ የምለው።

እኛ ያሰመርነውና የማንደራደርበት ቀይ መስመርስ ምንድን ነው? ይኖረን ይሆን?

ካለን አስረዱኝ እስቲ...
2.9K viewsedited  12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ