2022-07-17 18:52:35
መቼ ይሆን የዘረኝነት ደዌ ፈውስ የሚያገኘው?
***
የኢትዮጵያ የእግርኳስ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ባለፈው ወር ግብጽን ድባቅ መቱ። ኢትዮጵያ ስላሸነፈች ሁላችንም በጋራ ፈነደቅን።
ትላንት የሴቶች የ10,000 ሺ ሜትር የዓለም ሻንፒዮናን ለተሰንበት ግደይ አሸነፋ ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ከፍ አደረገች። ኢትዮጵያዊያን የደስታ ሲቃ ተናነቃቸው።
ዛሬ ደግሞ የወንዶች የማራቶን ውድድር በኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተደመደመ። ወርቁም፣ ብሩም ወደ ኢትዮጵያ የክብር ካዝና ገብቶ ተቆለፈ። አትሌት ታምራት ቶላ በአንደኝነት አሸነፈ፡፡ አትሌት ሞስነት ገረመው ደግሞ 42 ኪሎ ሜትሩን በሁለተኛ ደረጃነት ደመደመው።
በአሜሪካን አገር ኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻንፒዮና የኢትዮጵያ ስም ደመቀ። ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጲያዊነት ስሜት ብቻ እንሆ በደስታ ስካር ተውጠው ፈጠዝያ ላይ ናቸው።
ይህን የኢትዮጵያዊነት ደስታ ስመለከት ምን አለ ፖለቲካውም እንደ ስፖርቱ በሆነ? ፖለቲከኞቻችን ምን አለ የስፖርተኞቻችን ኢትዮጵያዊነት ቢላበሱ? ስል ተመኘሁ...
ግን መቼ ይሆን ኢትዮጵያን ያጎበጣት የዘረኝነት ደዌ ከፖለቲከኞቻችን ልብ የሚፋቀው? መቼ ይሆን የዘረኝነት ደዌ ፈውስ የሚያገኘው?
3.3K viewsedited 15:52