2022-07-18 21:00:54
ሁላችንም ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ጠንክረን እንስራ። አቅማችን አሟጥጠን እንጠቀም።
ሰሞኑንን በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻንፒዮና ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በማሸነፋቸው ኢትዮጵያዊያን በደስታ ሰክረናል። የኢትዮጵያዊነት መአዛ በሚያውደው ከርቤ ሶሻል ሚዲያው እየታጠነ ይገኛል። አጥንት ሲያሸት የሚውለው የማህበራዊው ሚዲያ መንደር መአዛው ተለውጧል።
ኢትዮጵያዊነት ከፍ ሲል ሁላችንም ከፍ እንላለን። በዘረኝነት ደዌ ስንሰቃይ ደግሞ አእምሯችን የተመሰቃቀለ፣ ህዝባችን ለፍጅት፣ ለስቃይ፣ ለመፈናቀል...ተዳርጓል።
የደበዘዘው ኢትዮጵያዊነት እንዲያጸባርቅ ከተፈለገ ቅንነት ብቻ ሳይሆን ጥላቻ የሚሰብኩ ሰነዶች ሊታገዱ ወይም ሊሻሻሉ ይገባል። ማሻሻሉን መጀመር ያለበት ህገ-መንግስቱ ላይ ነው።
ኢትዮጵያን እየናዳት ያለውን፣ ኢትዮጵያዊያንን አገር አልባ ያደረገውን ቋንቋን መሰረት አድርጎ የተዋቀረውን የጎሳ ፈድራሊዝም (Ethnic Federalism) በጥልቅ ጥናት ማስካከል።
ብሔራዊ መግባባት ፈጥሮ፣ አገራዊ እርቅ ማድረግ።
የሚዲያ ተቋማቶቻችን ኤዲቶሪያል ፖሊሲ (Editorial Policy) ማስተካከል። ወይም በኢትዮጵያዊነት ፎርማት (Format ) መቃኘት።
የትምህርት ካሪክለማችን ኢትዮጵያዊነትን በሚያጎላ መልኩ ተቀርጾ ትውልድ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ተኮትኩቶ እንዲያድግ ማድረግ ይጠበቃል።
በኢትዮጵያ የታሪክ ሂደት በጎዎቹን እያጎላን፣ የተሰሩ ስህተቶች ለዛሬ መፋጃችን ሳይሆኑ ዳግም እንዳይደገሙና ትውልድ እንዲማርባቸው ማድረግ ብልህነት ነው። ታሪክን በእየ ዘመኑ የታሪክ ሚዛን መመዘንም ልባምነት ነው።
ሲይጠቃለል:-
ታሪክ ለኢትዮጵያዊያን ዋርካ እንጂ ምድረበዳ መሆን የለበትም። ታሪክ ለኢትዮጵያዊያን የህይወት ዋስትና እንጂ ኢትዮጵያን የደም መሬት ማድረግ ኢትዮጵያ ከዓለም ካርታ ማሰረዝ ብቻ ሳይሆን ሃጢአትም ነው።
የፌስቡክ ገጼን ለመወዳጄት ቀጣዩን የፌስቡክ ሊንክ ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=100015846551462
2.0K viewsedited 18:00