Get Mystery Box with random crypto!

ለአንድ ትልቅ አባቴ 'እኔን ደካማውን ዝቅ ብዬ ይስሙኝ እስቲ' ያልኳቸውን... 'የጫካው ሲኖዶ | Amde Ezra

ለአንድ ትልቅ አባቴ 'እኔን ደካማውን ዝቅ ብዬ ይስሙኝ እስቲ' ያልኳቸውን...

"የጫካው ሲኖዶስ" ወይም የፌድራሊስት ኃይሉ አሊያም ደግም "ኦነግ ሸኔ በመስቀል" ስም ዓላማው እንዳይሳካ በማስላት አንድ ለምቀርባቸው የሐይማኖት አባት ቢደረግና ባይደገም ብዬ ያዋራኋቸውንና ይጥቅማል ያልኩትን ብቻ ለሌሎች አባቶች ይደርሳል ብዬ ተስፋ በመሰነቅ እንዲሚከተለው አጠር አድርጌ አቅርበዋለሁ።

1ኛ በፖለቲካው ዓለም ጎልተው የወጡ፣ በተለይ ዋልታ እረገጥ ሃሳብ ያለቸው ሰዎች (ብሔርተኞች) "ኦርቶዶክን እንታደጋለን" በሚል እና በሚዲያው ፊት አውራሪ ሆነው የመጡ ግለሰቦችን የሐይማኖት አባቾች መክረውና ዘክረው ከኋላ እንዲሆኑ ቢያደርጉ። ምክንያቱ ግልጽ ነው። ፖለቲከኞቹ የተሳሉበት ፖለቲካዊ ስዕል ስላለ ነው። የፖለቲካዊ ርዕዮተ-ዓለም አጥር፣ ዘር፣ ደንበር፣ ቀለም፣ ብሔር...የማትለየውን ዓለም አቀፋዊቷን ኦርቶዶክስን በፖለቲካ ስዕላቸው ምክንያት አጥር እንዳያስጥሩባት በመስጋት ነው። ይህን የምለው የኦርቶዶክሳዊያንን አንድነት ለማጠናከር በማሰብ ነው። የጫካው ሲኖዶስ እኩይ ዓላማ በእንጭጩ እንዲከሽፍ ያደርጋል ከሚል ስሌት ነው።

2ኛ ብሔርን በጅምላ ፈርጀው ሲሳደቡ የሚውሉ ግለሰቦችን፣ ዩቱዩቨሮች...ቤትክርስቲያኒቱን ለማዳን ያለመውን የተቀደሰ ትግል ከፊት ቀድመው ወይም ጠለፈው የመጡትን እረፉ ቢባሉ። በተለይ እንደ እነ ቀዌ ዘመድኩን በቀለ አይነቶቹ...

3ኛ ዓለም አቀፋዊቷን ኦርቶዶክስን የአማራ ህዝብ ሐይማኖት ብቻ አስመስለው ስዕል እየፈጠሩ ያሉትን ኃይሎች እንዲመከሩ ቢያደርጉ።

4ኛ በቀጣይ ኦርቶዶክስን ለመታደግ ሰላማዊ ትግሎች እንደሚደረጉ ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል። ሰላማዊ ሰልፎችን ጨመሮ ማለት ነው። እናም ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ የቤትክርስቲያኒቱን ዓርማ ብቻ ተይዞ እንዲወጣ ቢደረግ። በዚሁ ሳምንት በአሜሪካን አገር ዋሽንግተን ዲሲ የተካሄደውን ሰልፍ አይተናል። በዚህ ሰልፍ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ፣ የህወሃት ባንዴራ፣ የአሜሪካ አርማ ጭምር አንድ ላይ ሲውለበለቡ ተመልክተናል። የሰንደቅ ዓላማውም ሆነ የባንዴራዎቹ በሰልፉ በአንድ ላይ መውለብለባቸው የተዛባ ትርጉም ለመስጠት አመች ይሆናል። በተለይ ኦርቶዶክስ ለማጥፋት ላለሙ እኩያን ኃይሎች ግብአት ይሆናል ባይነኝ። የተቀደሰውን ሰለማዊ ትግል ከፖለቲካ ጋር እንዲያይዙት በር ከፈች የሚሆን ይመስለኛል? እናም ከባለፈው ትምህርት ተወስዶ በቀጣይ የቤተክርሲቲያኒቱን ህጋዊ ዓርማ ብቻ እንዲያዝ ቢደረግ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታተርፋለች ባይነኝ።


ማስታወሻ:- ከላይ የገለጽኳቸውን ፖለቲከኞች ዩቱዩቨሮ... በተለይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆኑት የኦርቶዶክ ጉዳይ በቀናነት ካሰቡ አይመለከተው እያልኩ አይደለሁም። ከብፁዓን አባቶቻችን፣ በእየ ደረጃው ከላሉ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶችና አገልጋዮች በላይ ለእሱ የበለጠ እንደ ሚመለከታቸው አድርገው ጠርዝ ማሲያዝ አደጋ አለው ነው። ብሔር፣ ደንበር፣ ቀለም፣ ፖለቲካዊ አጥር፣ ቋንቋ፣ ዘር... የሌላትን ቅድስት ቤተክርስቲያን ግለሰቦቹ በተሳሉበት ፖለቲካዊ ምስል ወይም ፖለቲካዊ ውግንናቸው ምክንያት አጥር አስበጅተው እንዳያዳክሟት በመስጋት ነው። የኦርቶዶክሳዊያንን አንድነት በማጠናከር የጫካውን ሲኖዶስ ዓላማ በቀላሉ እንዳይሳክና እንዲኮላሽ ያደርጋል በማለት ነው።