Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ ዓመት በቦታው ነበርኩ። ተደስቼ፣ ተደምሜም ውዬ ነበር። ዘንድሮ ግን በግል ምክንያት መገኜት | Amde Ezra

የዛሬ ዓመት በቦታው ነበርኩ። ተደስቼ፣ ተደምሜም ውዬ ነበር። ዘንድሮ ግን በግል ምክንያት መገኜት አልቻልኩም። ይሁን እንጂ በማማው ደብረታቦር (ጎንደር) አጅባር ሜዳ ላይ ሲካሄድ የዋለውን የፈረስ ጉግስ በዓል በኢትዮጵያ ተሌቪዥኝ (EBC) በቀጥታ ስርጭት ተከታትያለሁ። እጅግ የደመቀ ነበር። በቦታው ታድሜ ባለመዋሌ ቢቆጨኝም በዓሉ በደመቀ ሁኔታ በመከበሩ እጅግ ደስ ብሎኛል። ዓመታዊው የቅዱስ መርቆርዮስ በዓልና ባህላዊው የፈረስ ጉግስ ሥነ-ስርዓት እጅግ ደምቆና አምሮ ተከብሮ እንዲውል ጉልህ ሚና ላበረከታችሁ ወንድም፣ እህቶቼ በሙሉ በእጅጉ ልትመሰገኑ ይገባል።