Get Mystery Box with random crypto!

Amde Ezra

የቴሌግራም ቻናል አርማ amde123 — Amde Ezra A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amde123 — Amde Ezra
የሰርጥ አድራሻ: @amde123
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.51K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃ መስመር

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-02-21 16:16:19 ራህማቶ ኪታ “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል”ብላለች

በአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ላይ ለመታደም የመጣችው የኒጀር ዜግነት ያላት የፊልም ባለሙያዋ ራህማቶ ኪታ  አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም በማድረግ አፍሪካዊያንም እንዲያውቁት ማድረግ ይገባል ብላለች።

ባለሙያዋ የፍራንኮ አፍሪካን ፊልም አዋርድን አሸንፋለች። በሥራዎቿ ዙሪያ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥታለች። የፊልም ጸሐፊ፣ ዳይሬክተር እና ፕሮዲውሰር ራህማቶ ኪታ አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲኾን በአደባባይ ጥረት የጀመረችው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር በማነጋገር መኾኑን አብራርታለች።

በቅርቡም ይፋዊ ደብዳቤዋን ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት መሥጠቷን አብራርታለች። በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የታየላት  "የጋብቻ ቀለበቱ" የተሰኘው ፊልሟ በፊልሙ ዕይታ ማጠናቀቂያ ላይ የተሳታፊዎችን ስም እና ምስጋናዋን በምትገልጽበት ቦታ፤ ጽሑፉን በአማርኛ ቋንቋ በማስፈር ቋንቋውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ጥረት አድርጋለች።

በዓለማችን በርካታ ቋንቋዎች ያሉ ቢኾንም የራሳቸው የፊደል ገበታ ከታደሉ ጥቂት ቋንቋዎች መካከል አንዱ የኾነው አማርኛ ቋንቋ ፤ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ መኾን ይገባዋል፤ ይህንን ማድረግ ስንችል የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን አማርኛ ቋንቋ የአፍሪካውያንም ሐብት መኾን ይችላል ስትል ራህማቶ ኪታ አብራርታለች።

የአማርኛ ቋንቋ 7ተኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እስኪኾን ጥረቴን አላቋርጥም ብላለች።

አማርኛ ከምሥራቅ አፍሪካ ውጭ በእስራኤል፣በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች እና በደቡብ አፍሪካ በብዙዎች ዘንድ የሚነገር ውብ ቋንቋ ስለመኾኑ አብራርታለች።
   አሚኮ
1.4K views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 16:37:38
1.5K views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 16:37:35 በነገራችን ላይ ጎንደር ዓመት እስከ ዓመት በጸሎቷ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ እየተማለደች፣ በነፍጧ ደግሞ ደንበር እየጠበቀች ኢትዮጵያን ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር ክንዷን አጠንክራ የቀጠለች!! የምትቀጥል ግንድ ሀገርነች!!
1.5K views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 18:21:53
2.1K views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 18:21:36 መጠራጠር ዓለማዊ ህይወት እና ፖለቲካ ላይ ይሰራ እንደሆን እንጂ በእምነት ላይ ቦታ የለውም። በመሆኑም ብጹአን አባቶቻችን በመንፈስቅዱስ መሪነት የወሰኑትን ውሳኔ በፍጹም እምነት እቀበላለሁ። ውሳኒያቸውን ያላንዳች ማስተሃቀር አከብራለሁ!!

፩ ቅድስት ቤተክርስትያን!!
፩ ቅዱስ ሲኖዶስ
፩ መንበረ-ፓትርያሪክ

#ሰላም ለኢትዮጵያ!!
2.0K views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 21:32:51 ሃሳባችንን በቪዲዮ፣ በኦዲዮ...ለማጋራት እንዲሁ የበሰሉ ሃሳብ ከላቸው ከሌሎች ወገኖች ለመጋራት ወደ Tiktok መንደር ገብተናል። በመሆኑም ከስር ያስቀመጥኩት የቲክቶክ አካውንቴ ሊንክ ነውና ሊንኩን በማስፈጠር ፎሎው ብታደርጉኝ ጉዳት እንደማይገጥማችሁ አረጋግጥላችኋለሁ

https://www.tiktok.com/@amdeezra0?_t=8Zqjk8ESJqX&_r=1
1.2K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 16:04:40
1.5K views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 16:04:28 ቅዱስ ሲኖዶስ በተደጋጋሚ ለይቅርታ መንፈሳዊ በሩ ክፍት መሆኑንን አረጋግጧል።

በመሆኑም የቤተክርስቲያንን ሥርዓተ-ቅኖና በመጣስ ተሹመው ከነበሩና ከተወገዙት መካከል "አባ ንዋዬ ስላሴ አክሊሉ" ለቅዱስ ሲኖዶስ የይቅርታ ደብዳቢያቸውን አስገብተዋል።
1.5K viewsedited  13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 20:10:55
1.0K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 20:10:48 አንዳንድ ሰዎች ስለትላንትናው የፍ/ቤት ትእዛዝ የሚያወሩትን አወዛጋቢ ጉዳይ በተመለከተ

ከ Andualem Buketo Geda ፌስቡክ ገፅ የተወሰደ።

##########################

የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ እና መግለጫውን ተከትሎ በብጹእ አቡነ አብርሃም የተሰጠውን ማብራሪያ ሰምታችኋል ብዬ አስባለሁ!

አንዳንድ ሰዎች ስለትላንትናው የፍ/ቤት ትእዛዝ የሚያወሩትን አወዛጋቢ ጉዳይ በተመለከተ ለብጹአን አባቶች ዛሬ ጠዋት ገለጻ አቀረብን።

'ህገወጡ ቡድን የያዛቸውን ቦታዎች ለምን ይዞ እንዲቀጥል ተባለ?!' የሚለውን ጠየቁን።

እስከ አሁን የእግድ ፋይል እንጂ(ያውም ክስ ሳይጀመር በእግድ ጉዳይ ብቻ በቀጥታ የተከፈተ የመጀመሪያው የፍ/ቤት ፋይልም ነው) ዋናው ክስ እንዳልተከፈተ :ከጉዳዩ ውስብስብነት አንጻር ክስ ለመክፈት ጊዜ ለማግኘት ሰው እንዳይሞት ሲባል ለፍርድ ቤት እግድ ጠይቀን በዚህ ጉዳይ ያሉ አከራካሪ ነገሮች እስኪጠናቀቁ ብቻ የተሰጠ ጊዜያዊ የእግድ ትእዛዝ መሆኑን :የቤተክርስትያን ንብረቶችን የማስመለስ ክስ በቀጣይ የምንከፍት መሆኑን ነገርናቸው ።

...ለአንዳንዶች 'ኒውክለር ሳይንስ' የሆነባቸው የእግድ እና የውሳኔ ልዩነት ብጹአን አባቶች ለመረዳት 30 ሰከንድ ነው የፈጀባቸው!!

ያስገኘነውን ውጤት በተመለከተ በመላው ብጹአን አባቶች አጥንት ድረስ የሚደርስ ምርቃት እና መባረክ ተችሮናል!!

ከዛ በተረፈ ቅድም እንደሰማችሁት አንዳንዶች እኔን እና አንዳንድ የህግ ኮሚቴ አባላትን በተመለከተ እላፊ ሄደው የሚናገሩት ለቤተክርስትያን ካላቸው ቀናኢነት እና መንፈሳዊ ቅናት የመነጨ መሆኑን በብጹአን አባቶች ደስስ በሚል ሁኔታ ምክር ስለተለገሰኝ ማንም እኔን በተመለከተ በሰጠው ትንታኔ ቂም ላልይዝ ነገሩን ሁሉ እርግፍ አድርጌ ትቻለሁ!!
( ትንሽ የከበደኝ ለሰማይ ለምድር የከበዱ ብጹአን አባቶች በካሜራ ፊት ቆመው እባካችሁ ከእንደዚህ አይነት ነገር ተቆጠቡ ሲሉ እና ሲማጸኑ ሳይ ነው!!)

በነገራችን ላይ ይሄን ስራ የምሰራው ከበርካታ የህግ ባለሙያዎች ጋር ነው! በእውቀት በልምድና ቤተክርስትያንን በምንወክልበት ሁሉ የፈጣሪ እርዳታ እንዳይለየን ተባርከንም ጭምር ነው!!

ስራውን ስንሰራ አሁንም ወደፊትም ከበረከት በቀር የምንቀበለው አምስት ሳንቲም የለም!!

ለኔ እስከዛሬ ከያዝኳቸው ጉዳዮች ሁሉ የምንግዜም ከባዱ እና ወሳኙ ጉዳዬ ነው!

ያው በፌስቡክ እና በዩቲዩብ ጥቆማ አልተመረጥኩምና በፌስቡክ እና በዩቲዩብ የነቀፌታ ጋጋታ የተጣለብኝን ሃላፊነት አልለቅም!!

ገና ብዙ ስራ እንሰራለን!!

አብረውኝ ባሉት ባልደረቦቼ :እና በሁሉም ጉዳይ በሚመሩን የቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች እተማመናለሁ:እጸናለሁም!!

አንድ ነገር ግን ልለምናችሁ...

እኔን ተፋቱኝ እና ዋናው ጉዳይ ላይ (እንደዚህ ሰሞኑ ሁሉ) አተኩሩ!!
መልካም ቀን!!
1.0K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ