Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የሰርጥ አድራሻ: @addiszeybe
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.27K
የሰርጥ መግለጫ

ለፈጣን መረጃዎች አዲስ ዘይቤ
Twitter : https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Website : https://addiszeybe.com/
YouTube : https://youtube.com/c/AddisZeybe
Instagram : https://bit.ly/3D1tEwC
ስልክ 251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 97

2022-09-02 09:52:58
Alemayehu Eshete, the Ethiopian Elvis Presley passed away a year ago today
361 viewsedited  06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 09:37:46
የሸዋ ሮቢት ከተማ ከንቲባ በተፈጸመባቸው ጥቃት ተገደሉ።

ነሃሴ 27/2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ፣ አዲስ አበባ) የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው በትላንትናው ትናንት ነሃሴ 26/2014 ዓ.ም ምሽት 3:00 ላይ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸው ተሰማ።

ውብሸት አያሌው ባለትዳር እና የአንድ ሴትና አንድ ወንድ አባት የነበሩ ሲሆን፤ ወደ ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር በሥራ ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት በቀወት ወረዳ አስተዳደር በተለያዩ ተቋማት በባለሙያነትና በሥራ ኃላፊነት ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል።
_____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።
Twitter : https://bit.ly/3uQBnvj
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Telegram : https://bit.ly/3JX93LY
Website : https://bit.ly/3JOUavm
YouTube : https://bit.ly/37rIyBa
415 viewsedited  06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 09:14:13 it was just a year ago that Ethiopia lost its beloved veteran vocalist Alemayehu Eshete. He was known for his deep patriotic sentiment and venerated musical acumen. We would like to dedicate this piece to paying homage to his dignified artistic service.
https://bit.ly/3PZvrHO
#Ethiopia #AddisAbaba #OBITUARY
448 views06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:59:00 The first Ethiopian private mobile money service, Kacha Digital Financial Service joined the national e-payment network Ethswitch which would enable Kacha users to easily transact & transfer money between Kacha and other banks. Read more
https://bit.ly/3B1CawD
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
499 views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:49:45
ከዩክሬን ወደ ኢትዮጵያ ስንዴ የጫነችው መርከብ ጅቡቲ እንደደረሰች ተነገረ

ነሐሴ 26፤ 2014 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) በኢትዮጵያ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ይደርሳል የተባለውን ስንዴ ከዩክሬን ያጓጓዘችው የመጀመሪያ መርከብ ጅቡቲ ወደብ መድረሷን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢስሊይ በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት “ከዩክሬን ወደ ኢትዮጵያ ስንዴ ያጓጓዘችው የመጀመሪያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም መርከብ ጅቡቲ ደርሳለች። አሁን የሚቀረው ስንዴውን ወደ ኢትዮጵያ ማጓጓዝ ነው” ሲሉ ገልፀዋል።

ከ14 ቀናት ጉዞ በኋላ ጅቡቲ የደረሰችው መርከብ 23 ሺህ ቶን ስንዴ መጫኗም ተሰምቷል። ጭነቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ ለረሃብ የተጋለጡ እና አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ለተባሉ 20 ሚልዮን ዜጎች የሚከፋፈል ሲሆን ተመሳሳይ ጭነት ከዩክሬን የሚያጓጉዝ ተጨማሪ መርከብ እንደሚኖርም ይጠበቃል።
@AddisZeybe
585 views12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:49:12
በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው እንግልት ተባብሶ እንደቀጠለ ታወቀ

ነሐሴ 26፤ 2014 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች “የመኖሪያ ፈቃድ የላችሁም” በሚል እየደረሰባቸው ያለው ወከባና እንግልት ተባብሶ መቀጠሉን የአዲስ ዘይቤ ምንጮች ተናገሩ።

“በዚህ ሳምንት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያንን አስረዋል። አስረው ገንዘብ ተቀብለው እና የእጅ ስልክ ወስደው የሚለቁ ቢኖሩም በድጋሚ መያዝ አይቀርም። በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ ደግሞ ቤት ለቤት እየዞሩ ማፈስም ጀምረዋል” ሲሉ በሱዳን የሚገኙት ዜጎች ስጋታቸውን ገልፀዋል።

በካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት መሰረታዊ የሆነውን ፓስፖርት ለመስጠት ከመዘግየቱም በላይ የዜጎች ሰብዓዊ መብት እንዲከበር ጥረት እንዲደረግ ስደተኞቹ ለሚያቀርቡት አቤቱታ “ዲፕሎማሲያችን የተበላሸ በመሆኑ ምንም ማድረግ አንችልም” የሚል ምላሽ እንደሰጣቸውም ተናግረዋል።

“ሌላው ቢቀር ዜጎችን ወደ ሀገር መመለስ እንኳን መቻል ነበረበት” የሚሉት ስደተኞች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ በመሆናቸው ከቤት መውጣትም አለመቻላቸውን አስረድተዋል።

አዲስ ዘይቤ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲንም ሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ምላሽ ለማካተት ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።
@AddisZeybe
506 viewsedited  12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:16:18
“ሁለቱም ወገኖች” እየተባለ የሚወጡ መግለጫዎችን መንግስት እንደማይቀበል አስታወቀ

ነሃሴ 26፤ 2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ፣ አዲስ አበባ) በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ “ሁለቱም ወገኖች” እየተባለ የሚሰጡ መግለጫዎች በመንግስት በኩል “ተቀባይነት የላቸውም” ተባለ።

የመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ “በህወሓት የሽብር ቡድን እየደረሱ የሚገኙ ጥፋቶችን ለማስቆም መንግስት ለሰላማዊ አማራጭ ያደረጋቸውን ጥረቶች ሁሉ እየመከኑ ባለበት ሁኔታ፤ አሸባሪው ህወሓትን መጫን ሲገባቸው 'ሁለቱም ወገኖች' ማለት ተቀባይነት የለውም" ብሏል።

ህወሓት በበኩሉ "ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በሰሜን ምዕራባዊ ትግራይ አቅጣጫ በአራት ግንባር የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጦር ከባድ ውጊያ ከፍተዋል" ሲል አስታውቆ ነበር። የህወሓት ማዕከላዊ ኮማንድ አባሉ ጌታቸው ረዳ ኃይላቸው ጥቃቱን እየመከተ እንደሚገኘ በትዊተር ገጻቸው አሳውቀዋል።

የመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው “ህወሓት በለኮሰውና እያስፋፋው ባለው እሳት ንፁሀን እየተገደሉ፣ ዜጎች እየተፈናቀሉ እና ንብረት እየወደመ ነው” ሲል አስታውቋል።
_____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።
Twitter : https://bit.ly/3uQBnvj
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Telegram : https://bit.ly/3JX93LY
Website : https://bit.ly/3JOUavm
YouTube : https://bit.ly/37rIyBa
340 views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:30:41
በጉራጌ ዞን ከክልል የአደራጀት ጥያቄ ጋር በተገናኘ ለሚነሱ የፀጥታ ችግሮች እርምጃ ይወሰዳል ተባለ።

ነሐሴ 25 ፤ 2014 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ : ሐዋሳ ) በጉራጌ ዞን ከክልል ጥያቄ ጋር ተያይዞ የስራ ማቆም እንዲሁም በቤት ዉስጥ የመቀመጥ አድማ መቀጠሉን አስመልክቶ ዉይይት ያደረገዉ ኮማንድ ፖስቱ ተግባራዊ የሚደረጉ ዉሳኔዎችን አሳልፏል።

በዛሬዉ ዕለት ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎች ማለትም እምድብር ከተማ ፣ ምሁር አክሊል ወረዳ ፣ ሶዶ ፣ ጌታ ጉመር እና አበሸጌ ወረዳ የአከባቢው የፀጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ዉይይት ሲያደርጉ ከአደረጃጀት ጥያቄ ጋር በተገናኘ ለሚፈጠሩ ችግሮች የኮማንድ ፖስቱ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን የክላስተር አወቃወርን በመቃወም በዞኑ ምክርቤት በክልል የመደራጀት ዉሳኔ ቢያፀድቅም በፌዴሬሽን ምክርቤት ባለበት በደቡብ ክልል ስር እንዲቆይ መወሰኑ ይታሳወሳል ። ከዚህ ጊዜ በኃላ የዞኑ ዋና ከተማ ከሆነችዉ ወልቂጤን ጨምሮ በሌሎች ወረዳዎች የስራ ማቆም እና በቤት ዉሰጥ የመቀመጥ አድማ ሊጀመር ችሏል።

በዞኑ ወረዳዎች የሚገኙ የፀጥታ አባላት ባደረጉት ስብሰባ ከኮማንድ ፖስቱ ፍቃድ ዉጪ አድማ ማድረግ ይህ ማለት የንግድ ሱቆችን እና የመንግስት ተቋማትን ያለምንም ምክንያት መዝጋት እና ቤት መቀመጥ ፣ የትኛዉም ስብሰባ እና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንዲሁም ሁከት አነሳሽ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ከልክሏል።

እንደ ፀጥታ ኮማንድ ፖስት ዉሳኔ የተቀመጡ ክልከላዎችን ወደ ጎን በመተዉ የተገኘ "የህጋዊ እርምት እርምጃ" እንደሚወስድ አሳዉቋል።
@AddisZeybe
444 viewsedited  12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:55:31 The locals say they used to climb up Hambericho, usually for the Mesqel celebration, every September. The steps have now made it easier for them to climb the mountain as often as they like. In the 2020/21 fiscal year alone, more than half a million local and international tourists visited Hambericho. Read more
https://bit.ly/3CEGAL8
#Ethiopia #Hawassa
@AddisZeybe
420 views11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:49:47
የሰሜኑ ጦርነት እና በኦሮሚያ ያለው ግጭት መላ ሀገሪቱን እና ህዝቦቿን የሚጎዳ ነው ሲል ኦፌኮ አሳሰበ

ነሃሴ 25፤ 2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት መላ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን የሚጎዳ ነው ሲል የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አሳስቧል።

ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ "በሁለቱም አካባቢዎች ያለው ግጭት ህዝብን ዳግም ለከፋ ሞት እና መፈናቀል የሚዳርግ እንዲሁም ሰፊ የመሰረተ ልማት ውድመት የገጠማቸው አካባቢዎችን ይበልጥ እንዳይረጋጉ የሚያደርግ ነው" ብሏል።

ችግሮቹ በዘላቂነት ሊፈቱ የሚችሉት “እውነተኛ እና ሁሉን አሳታፊ በሆነ ድርድር ብቻ ነው” ያለው ኦፌኮ ሁሉም ተፋላሚ ኃይሎች ለሰላማዊ መፍትሔ ፍላጎት እንዲኖራቸው ጥሪ አቅርቧል።

በኦሮሚያ ክልል ያለው “ጦርነት” ሊፈታ ቀርቶ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅናም ሊሰጠው አለመቻሉ አሳሳቢ ነው ሲል ፓርቲው በመግለጫው አስገንዝቧል።

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ገዢው ፓርቲ፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሚድያ ባለሙያዎች እና አክቲቪስቶች ግጭቱን ከሚያባብሱ ንግግሮች እንዲታቀቡም ተማፅኗል።
_____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።
Twitter : https://bit.ly/3uQBnvj
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Telegram : https://bit.ly/3JX93LY
Website : https://bit.ly/3JOUavm
YouTube : https://bit.ly/37rIyBa
428 viewsedited  11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ