Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የሰርጥ አድራሻ: @addiszeybe
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.27K
የሰርጥ መግለጫ

ለፈጣን መረጃዎች አዲስ ዘይቤ
Twitter : https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Website : https://addiszeybe.com/
YouTube : https://youtube.com/c/AddisZeybe
Instagram : https://bit.ly/3D1tEwC
ስልክ 251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 96

2022-09-04 16:50:11 Ethiopia’s age-old traditional tattoo, Nikisat, has its own unique practice along with aesthetic, cultural, religious & identity values, though left aside today. Addis Zeybe’s Gondar correspondent explores this remarkable practice in Northern Ethiopia.
https://bit.ly/3BaXPTa
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
197 viewsedited  13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 17:52:51 The Council approved the policy after having detailed deliberation and decided on its implementation including further inputs Recent reports indicated there were efforts of revising the banking regulation aiming at allowing foreign investors in the sector. Read more
https://bit.ly/3wTI2Wn
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
366 views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 16:03:57 የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት በጦርነት ጊዜ እና ሌሎችም
ሙሉ ቪድዮውን ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ


475 views13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 11:38:19
የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት በጦርነት ጊዜ እና ሌሎችም
10 ሰዓት ላይ ይጠብቁን
https://youtube.com/c/AddisZeybe
117 views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 09:40:04 The mission rebuked Dr. Tedros for using WHO's platforms to attack the Ethiopian government with impunity and said it submitted a complaint to the Executive Board to initiate an independent investigation. It also vowed to continue challenging Tedros in every avenue possible. Read More
https://bit.ly/3egFuuS
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
277 views06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 15:59:00
በጉራጌ ዞን የሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በመዘጋታቸዉ ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንዳልቻሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

ነሐሴ 27 ፤ 2014 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ:ሐዋሳ) በጉራጌ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች እና ከተማዎች ለሁለት ቀናት ከተደረገዉ የስራ ማቆም እና የቤት ዉስጥ የመቀመጥ አድማ ወዲህ በዞኑ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች መዘጋታቸዉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በዚህም በወልቂጤ ከተማ እንዲሁም በሌሎች ወረዳዎች ከሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች አገልገሎት እየሰጡ ባለመሆናቸዉ ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንዳልቻሉ ገልፀዋል።

ለአዲስ ዘይቤ ስለ ጉዳዩ ሁኔታውን ያስረዱት የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ አቶ አንዋር ዩሱፍ "ባንኩ ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ከሰኞ ጀምሮ ዝግ በመሆኑ ገንዘባችንን ማንቀሳቀስ አልቻልም። በዚህ ምክንያት ዩኒቨርስቲ ለሚገኘዉ ልጄ ገንዘብ ለመላክ ሌላ ባንክ ለመጠቀም ተገድጃለሁ" በማለት ይናገራሉ። በተጨማሪም የመንግሥት ሰራተኞች ደሞዛቸው የሚገባዉ በንግድ ባንክ በኩል ቢሆንም ዝግ በመሆኑ መቸገራቸውን አንስተዋል።

በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎችም በተመሳሳይ ሁኔታ የባንኩ ቅርንጫፎች ዝግ በመሆናቸው ተጠቃሚዎች ፊታቸውን ወደ "ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ" ማድረጋቸዉን ሰምተናል።

በምሁር አክሊል ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች በሰጡን አስተያየት “ወቅቱ የበዓል ሰሞን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በስራ ምክንያት በሀገሪቱ ተበታትነዉ የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች በሚሰባሰቡበት ወቅት ገንዘባቸውን በአብዛኛው የሚለዋወጡበት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መዘጋቱ አግባብ አይደለም" ብለዋል።

አዲስ ዘይቤ በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ለማናገር ያደረገችዉ ጥረት አልተሳካም።
@AddisZeybe
687 views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 15:52:10 የጎዳና አዳሪዎች የአዲስ አበባ ድልድዮች ባለውለታችን ናቸው ይላሉ። በተለይም በክረምት ወራት ከባድ ዝናብ ሲጥል ሌላው ሰው ወደ ቤቱ ለመግባት እንደሚሯሯጠው ጎዳና አዳሪዎች ወደ ድልድዮች ያቀናሉ፤ ይህም ካልተቻለ ፖሊስ ጣቢያ ለማደር ፀብና ግርግር መፍጠር ሁለተኛ አማራጫቸው እንደሆነ ይናገራሉ። ሙሉ ጽሑፉን እነሆ
https://bit.ly/3CSyGxB
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
570 views12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 15:35:48
የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት በጦርነት ጊዜ እና ሌሎችም በአርትስ ቴሌቭዥን
ማታ 1:30 ላይ ይጠብቁን
https://youtube.com/c/AddisZeybe
572 views12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 10:57:48
በኢትዮጵያዊ ባለሀብት ብቻ የለማ የመጀመሪያው የኢንዱስትሪ ፓርክ ተቋቋመ

ነሐሴ 27፤ 2014 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ: አዲስ አበባ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው እና በኢትዮጵያዊ ባለሀብት ብቻ የለማ የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ተቋቋመ።

ከ5.7 ቢልየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሬዳዋ የኢንዱስትሪ ፓርክ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ውስጥ 116 ሔክታር መሬት ላይ የሚያርፍ እንደሆነ አልሚ ባለሀብቱ ኢንጂነር ታደሰ አድማሱ ገልፀዋል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር በበኩላቸው የኢንዱስትሪ ፓርኩ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከ17 ቢልየን ብር በላይ ፈሰስ እንደሚደረግበት ገልፀው ፓርኩ የውጭ ባለሀብቶችን ለመሳብ የሰራቸው ስራዎችን አድንቀዋል።

ባለሀብቱ ኢንጂነር ታደሰ ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፁት የኢንዱስትሪ ፓርኩ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ የግል ሄሊኮፕተር እና አነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲሁም የጥገና ስፍራ ይኖረዋል።

በአጠቃላይ 27 ኢንዱስትሪዎች የሚኖሩት ሬዳዋ የኢንዱስትሪ ፓርክ ከአውቶሞቲቭ ማምረቻ በተጨማሪ የጨርቃጨርቅ፣ የምግብ ማቀነባበሪያ እና ሌሎችንም ይይዛል።

ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ የሞተር ኢንዱስትሪ የነበረው ሬዳዋ በዛሬው እለት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያደገበትን የፊርማ ስነ ስርዓት አካሄዷል።

ባለ 3 እና 4 እግር ተሽከርካሪዎችን የሚያመርተው ፋብሪካ በቅርብ ጊዜ ወደ ውጭ ገበያ ለመቀላቀል እና ደቡብ ሱዳንን የመጀመሪያ መዳረሻ ለማድረግ ማቀዱ ተገልጿል።
@AddisZeybe
343 views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 10:52:01
የባህርዳር ከተማ ፀጥታ ምክር ቤት ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የቤት ኪራይ የሚጨምሩ አከራዮችና ነጋዴዎችን አስጠነቀቀ

ነሃሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ ባህር ዳር) የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር ቤት ባደረገው ክትትልና ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ያለውን ሀገራዊ ሁኔታ እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ የሚያደርጉ አንዳንድ አከራዮች መኖራቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

ስለሆነም በኪራይ ቤት የሚኖሩ የከተማው ነዋሪዎች ያልተገባ የኪራይ ጭማሪ ሲገጥማቸው ወደሚኖሩበት ቀበሌ በመሄድ ሪፖርት እንዲያደርጉ የፀጥታ ምክር ቤቱ አሳስቧል።

በተያያዘ አዲሱን ዓመትና ወቅታዊ ሆኔታውን ግምት ውስጥ በማስገባት ሆም ብሎ የምርት እጥረትን በመፍጠር የመሠረታዊ ፍጆታ ዕቃዎች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ እንደሆነ በመግለፅ በዚህ ድርጊት የሚሳተፉ የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ከድርጊታቸው እንድጥቆጠቡ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር ቤት አስጠንቅቋል።
_____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።
Twitter : https://bit.ly/3uQBnvj
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Telegram : https://bit.ly/3JX93LY
Website : https://bit.ly/3JOUavm
YouTube : https://bit.ly/37rIyBa
298 viewsedited  07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ