2022-09-07 15:35:33
ኦነግ ሸኔ በአርጆ ደዴሳ ስኳር ፋብሪካ ላይ ጥቃት ማድረሱ ተነገረ
ጷጉሜ 2፤ 2014 ዓ.ም
(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው እና መንግስት “ሸኔ” እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በአርጆ ዴደሳ ስኳር ፋብሪካ ጥቃት መፈፀሙ ተሰማ።
እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን በምሥራቅ ወለጋ ዞን የሚገኘውን ፋብሪካ ለሰዓታት ተቆጣጥሮ ከቆየ በኋላ ንብረት ማውደሙን እና ዘረፋ መፈጸሙን የስኳር ኮርፖሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት እና ተሳትፎ ዋና ክፍል ኃላፊ ረታ ደመቀ ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።
ታጣቂው ቡድን ስድስት የአርጆ ደዴሳ ተሸከርካሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ተሽከርካሪዎችንም ያቃጠለ ሲሆን የሠራተኞችን ሞባይልና ጫማ እንዲሁም ቁጥራቸ የማይታወቅ የድርጅቱን ላፕቶፕ እና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች ዘርፈዋል ነው የተባለው።
የቡድኑ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ በትዊተር ገፃቸው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት በስኳር ፋብሪካው እርምጃ መውሰዳቸውን ተከትሎ በቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ የመንግሥት ኃይሎች አካባቢውን ጥለው ወደ ደቡብ ሸሽተዋል ሲሉም አስታውቀው ነበር።
_______
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።
Twitter : https://bit.ly/3uQBnvj
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Telegram : https://bit.ly/3JX93LY
Website : https://bit.ly/3JOUavm
YouTube : https://bit.ly/37rIyBa
579 views12:35