2022-09-22 14:32:22
የቴዲ አፍሮ ‘ናዕት’ ሙዚቃ ለአህጉር አቀፍ ሽልማት እጩ ሆነ
መስከረም 12፤ 2014 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና ሔዋን ገብረወልድን ጨምሮ ስድስት የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች በየዓመቱ በሚካሄደው የመላው አፍሪካ የሙዚቃ ሽልማት (አፍሪማ) ላይ እጩ መሆናቸው ታወቀ።
ቴዲ አፍሮ ከጥቂት ወራት በፊት የለቀቀው ‘ናዕት‘ የተሰኘው ነጠላ ዜማ በአፍሪማ አዋርድ በአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ የሬጌ እና ዳንስሆል ሙዚቃ ዘርፍ ታጭቷል። ድምፃዊት ቤቲ ጂ ‘አዲስ ሰማይ’ በሚለው ስራዋ እና ሌንጮ ገመቹ ‘ሳግሊ’ በተባለው የኦሮሚኛ ቋንቋ ሙዚቃው በሀገረሰብ ዘርፍ እጩ ሆነዋል።
ድምፃዊት ሔዋን ገብረወልድ ‘ሼሙና’ በሚለው ሙዚቃዋ “በአመቱ ጎልቶ የወጣ ሙዚቀኛ” እና “የምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ሴት ሙዚቀኛ” በሚሉ ዘርፎች በእጩነት ቀርባለች።
ድምፃዊ አዲስ ለገሰ ‘እንጃ’ በሚለው ሙዚቃው ምርጥ የአፍሪካ ጃዝ ሙዚቃ እንዲሁም ካስማሰ ‘ሠዋሠው‘ በተሰኘው ሙዚቃው “የመነሳሳት ስሜት በሚፈጥር የሙዚቃ ዘርፍ” የታጨ ሲሆን ሁለቱ ድምፃውያን በየግላቸው የምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ወንድ ሙዚቀኛ ለመሆንም ይፎካከራሉ።
ለእጩ ድምፃውያን በኦንላይን ድምፅ መስጠት የሚቻልበት ስርዓት ከእሁድ መስከረም 15 የሚጀመር ይሆናል።
___
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።
Twitter : https://bit.ly/3uQBnvj
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Telegram : https://bit.ly/3JX93LY
Website : https://bit.ly/3JOUavm
YouTube : https://bit.ly/37rIyBa
771 viewsedited 11:32