Get Mystery Box with random crypto!

#Update ዘመነ ካሴ ህገ ወጥ ቡድን በማደራጀት እና ኬላ ዘርግቶ ገንዘብ በመሰብሰብ መጠርጠሩ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

#Update
ዘመነ ካሴ ህገ ወጥ ቡድን በማደራጀት እና ኬላ ዘርግቶ ገንዘብ በመሰብሰብ መጠርጠሩ ተገለፀ

መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ፡ ባህር ዳር) ትላንትና በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ስር የዋለው ዘመነ ካሴ ፍርድ ቤት ቀርቦ የአስር ቀናት ቀጠሮ የተሰጠው ሲሆን ምርመራውን የያዘው የክልሉ ፖሊስ ዘመነ ካሴን "ህገ ወጥ ቡድን በማደራጀት እና "ኬላ ዘርግቶ ገንዘብ በመሰብሰብ" እንዲሁም "በፌስ ቡክ ቅስቀሳ ማድረግ" በሚሉ ወንጀሎች ጠርጥሬዋለሁ በማለት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

የዘመነ ካሴ ጠበቆችም እነዚህን ወንጀሎች ለማጣራት በሚል ፖሊስ ላለፉት አራት ወራት ምርመራ ያደረገ መሆኑን እና ሌሎችን መከራከሪያዎችን በማቅረብ የጊዜ ቀጠሮ መስጠት ሳያስፈልግ አርበኛ ዘመነ በዋስ እንዲለቀቅ ጥያቄ አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱ የምርመራ ቡድኑ ያቀረበው ምክንያት በቂ አለመሆኑን ጠቅሶ የ10 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ በመስጠት ፖሊስ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ምርመራውን እንዲያጠናቅቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ዘመነ ካሴም ወደ 2ኛ ጣቢያ ተመልሷል።
@AddisZeybe