2022-09-23 10:02:53
በአዳማ ከተማ የመስቀልና ኢሬቻ በዓላት እስኪያልፉ የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴ ታገደ
መስከረም 13፤ 2015 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፡ አዳማ) በቅርቡ የሚከበሩትን የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላትን ምክንያት የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ላልተወሰነ ጊዜ የሞተር ሳይክል እንቅስቀሴን ሙሉ ለሙሉ ማገዱን አስታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪ የባለ-ሶስት እግር ተሽከርካሪ ‘ባጃጆች’ ደግሞ ከጠዋት 12 ሰዓት እስከ ማታ 12 ድረስ ብቻ እንዲንቀሳቀሱ እንደተወሰነ አዲስ ዘይቤ ከፖሊስ መምሪያው ሰምታለች።
በዓላቱን ምክንያት አድርጎ የተጣለው እገዳ የሚቆይበትን ጊዜ በተመለከተ አዲስ ዘይቤ የጠየቀቻቸው የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ገደቡ እስከ ኢሬቻ በዓል መጠናቀቂያ ድረስ እንደሚቆይ ገልጸዋል።
የእንቅስቃሴ ግደቦቹ ከትላንት መስከረም 12 ቀን የጀመረ ቢሆንም መረጃው ተደራሽ ባለመሆኑ በትላንትናው እለት በአዳማ ከተማ ከፍተኛ የተሽከርካሪ እጥረት በማጋጠሙ ነዋሪዎች ተቸግረው እንደነበረ አዲስ ዘይቤ ታዝባለች።
___
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።
Twitter : https://bit.ly/3uQBnvj
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Telegram : https://bit.ly/3JX93LY
Website : https://bit.ly/3JOUavm
YouTube : https://bit.ly/37rIyBa
765 viewsedited 07:02