Get Mystery Box with random crypto!

በአማሮ ልዩ ወረዳ የሸኔ ቡድን በድጋሚ ፈፅሞታል በተባለዉ ጥቃት አራት አርሶ አደሮች ተገደሉ መስ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

በአማሮ ልዩ ወረዳ የሸኔ ቡድን በድጋሚ ፈፅሞታል በተባለዉ ጥቃት አራት አርሶ አደሮች ተገደሉ

መስከረም 12፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ ሐዋሳ) በአማሮ ልዩ ወረዳ ዶርባዴ ቀበሌ ከምዕራብ ጉጂ ዞን ተነስተዋል በተባሉ መንግስት ሸኔ እያለ የሚጠራው ቡድን ታጣቂዎች በትላንትናው ዕለት አራት አርሶ አደሮችን ሲገድሉ ሶስት ሰዎች ማቁሰላቸው ተገለፀ።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡድን አባላት በተደጋጋሚ በአካባቢው ላይ ጥቃት መክፈታቸዉ የተነገረ ሲሆን በትላንትናው ዕለትም የደፈጣ ጥቃት በማድረግ አራት አርሶአደሮችን ሲገድሉ በሶስቱ ላይ ደግሞ የቁስለት አደጋ አድርሰዋል ተብሏል።

አዲስ ዘይቤ ልዩ ወረዳ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ባገኘችዉ መረጃ ከጥቃቱ በተጨማሪ “ለጊዜዉ ግምታቸው ያልታወቀ ንብረቶች በመዝረፍ በፍጥነት ከአከባቢ መሰወራቸው” ተነግሯል ።

መንግስት በሌሎች አከባቢዎች ላይ እያከናወነ የሚገኘውን የሠላም ማስከበር ሥራ በአማሮ በኩል በመሥራት የአካባቢዉን ሠላም ለማስጠበቅ መሥራት እንዳለበትም ጽ/ቤቱ ገልጿል።

ከአማሮ ልዩ ወረዳ አጎራባች ከሆነው ምዕራብ ጉጅ ዞን በሚነሱ የተደራጁ ታጣቂዎች ምክንያት በሚፈጠሩ ግጭቶች በልዩ ወረዳው በርካቶች ሲፈናቀሉ የንብረት እና የአካል ጉዳት መድረሱን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል።
@AddisZeybe