Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የሰርጥ አድራሻ: @addiszeybe
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.27K
የሰርጥ መግለጫ

ለፈጣን መረጃዎች አዲስ ዘይቤ
Twitter : https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Website : https://addiszeybe.com/
YouTube : https://youtube.com/c/AddisZeybe
Instagram : https://bit.ly/3D1tEwC
ስልክ 251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 95

2022-09-07 15:23:33
በኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ማጭበርበር ወንጀል በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ዓቃቤ ህግ ክስ ሊመሰርት ነው

ጷጉሜ 2/2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ፣ አዲስ አበባ) በኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ማጭበርበር ዓቃቤ ህግ በ6 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ሊመሰርት መሆኑ ታወቀ።

በአጠቃላይ ተጠርጣሪዎቹ ከ14ኛው ዙር 20/80 እና የ3ኛ ዙር የ40/60 የአዲስ አበባ ከተማ ኮንዶሚኒዬም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ላይ ያልቆጠቡና በወቅቱ ያልተመዘገቡ ግለሰቦችን ያለአግባብ በዕጣው እንዲያካትቱ አድርገዋል ተብለው በቁጥጥር ስር ውለው ከአንድ ወር በላይ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደነበር ይታወሳል።

ገንዘብ እየተቀበሉ ያልቆጠቡ ግለሰቦችን ባልተገባ መንገድ በኮንዶሚኒዬም ዕጣ እንዲካተቱ አድርገዋል ተብለው በዓቃቤ ህግ የተጠረጠሩ የስራ ኃላፊዎች የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሐም ሰርሞሌ፣ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አይሲቲ ዘርፍ ዳሪክተር አቶ ኩምሳ ቶላ፣ የቤቶች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች አቶ ሚኪያስ ቶሌራ፣ የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሶፍትዌር ሲስተም ልማት ዳይሬክተር አቶ መብራቱ ኪዳነማርያም፣ የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የኮምፒዩተር ፕርግራሚንግ ባለሙያ አቶ ስጦታው ግዛቸው እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የኮምፒዩተር ፕርግራሚንግ ባለሙያና የሶፍትዌር ተቆጣጣሪ አቶ ባዬልኝ ረታ ናቸው።

ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ሲያከናውን የቆየውን የጊዜ ቀጠሮ ምርመራ አጠናቆ ለዓቃቤ ህግ ማስረከቡን ዛሬ በነበረው ቀጠሮ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አስታውቋል።

ዓቃቤ ህግ ከፖሊስ የምርመራ መዝገብ መረከቡን ተከትሎ የ15 ቀን ክስ መመስረቻ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።
502 viewsedited  12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 14:30:41 የቅዱስ አላዛር ማተሚያ ቤት በኢ.ፌ.ድ.ሪ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣንና በድሬዳዋ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት በቅርስነት ተመዝግቦ የሚገኝ አንዱ የድሬዳዋ ቅርስ ነው። ማተሚያ ቤቱ ከመንፈሳዊ ውጪ ያሉ ህትመቶችን በብዛት የሰራው በደርግ ዘመነ መንግስት ነበር። የአዲስ ዘይቤ የድሬዳዋ ሪፖርተር ይህን ተቋም ታስቃኘናለች። ሙሉ ጽሑፉን እነሆ
https://bit.ly/3x15LUk
#Ethiopia #DireDawa
@AddisZeybe
526 views11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 19:18:18 በተጨማሪም በጥቃቶቹ ምክንያት የተፈጠረው የደኅንነት ስጋት ያልተቀረፈ መሆኑን እና በዞኑ ውስጥ ካሉት ወረዳዎች መካከል በጃርደጋ ጃርቴ፣ ኪረሙ እና በአቤ ዶንጎሮ ወረዳዎች ተመሳሳይ ጥቃቶች ሊፈጸሙ እንደሚችሉ ስጋቶች መኖራቸውንም ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

ኮሚሽኑ ጥቃት በተፈጸመባቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እንዲሰማሩ እና ሰላምና ደኅንነትን በማረጋገጥ ነዋሪዎችን ወደ ተረጋጋ ሕይወት የመመለስና ተገቢውን ምርመራ አድርጎ ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሥራ እንዲሠራ ኢሰመኮ አሳስቧል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ኮሚሽኑ ክትትል ማድረጉን የሚቀጥል መሆኑንና በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመው አሳዛኝ ጥቃት ያሳሰበው መሆኑን ገልጸው በማንኛውም ጊዜ የፀጥታ ስጋት ካለባቸው አካባቢዎች የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ወደ ሌላ ቦታ በሚዘዋወሩበት ወቅት የነዋሪዎች በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነት እና የንብረት መብቶች ለአደጋ እንዳይጋለጡ ተገቢ የሆኑ ጥንቃቄዎች ሊደረጉ እንደሚገባ በድጋሚ አስታውሰዋል።
@AddisZeybe
387 views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 19:18:10
በሆሮ ጉዱሩ ዞን ኡሙሩ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት ከ60 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

ጳጉሜ 1፤ 2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ስር በሚገኘው ኡሙሩ ወረዳ ከነሐሴ 23 እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በታጣቂ ኃይሎች በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ነዋሪዎች የተገደሉ፣ የቆሰሉ እና ከ20 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለፀ።

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ አገምሳ ቀበሌ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ” ተብሎ የሚጠራ) ታጣቂዎች የወረዳው ዋና ከተማ የሆነችውን ኦቦራ ከተማን ለመያዝ ባደረጉት እንቅስቃሴ ሦስት የአማራ ብሔር ተወላጆች መግደላቸውን ተከትሎ ከኡሙሩ ወረዳ፣ ሀሮ አዲስ ዓለም ከተባለ ቀበሌ እና አጎራባች ከሚገኘው የአማራ ክልል፣ ቡሬ ወረዳ የተውጣጡ ታጣቂዎች በኡሙሩ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች የሚገኙ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ነዋሪዎች ላይ ነሐሴ 24 እና 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ጥቃት ፈጽመዋል።

በእነዚህ ሁለት ቀናት በተደረጉ ጥቃቶች ከ60 በላይ ሰዎች መገደላቸውን፤ ከ70 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን፣ የነዋሪዎች የቤት ንብረቶች እና የቀንድ ከብቶች መዘረፋቸውን ኮሚሽኑ ካነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እና የመንግሥት ኃላፊዎች ለመረዳት መቻሉን ኢሰመኮ አስታውቋል።

“ጥቃት ከተፈጸመባቸው ቀበሌዎች መካከል አሁንም ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን እና በጥቃቱ ምክንያትም ከ20 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ተፈናቅለው በኦቦራ ከተማ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል” ብሏል ኮሚሽኑ።
367 views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 16:44:12 የአዲስ ዓመት መምጣትን አስመልክቶ በጎጃም አካባቢ የሚከበረው የእንግጫ ነቀላ ክዋኔ ልጃገረዶች ተሰብስበው በየቤት እየዞሩ በመጨፈር ጎንጉነው የያዙትን የእንግጫ ሳር በየቤቱ ምሰሶ ላይ ያስራሉ። የእንግጫ ነቀላ አመታዊ ክዋኔን በተመለከተ የአዲስ ዘይቤ ባለደረባ ከባህርዳር የሚከተለውን አጭር ዳሰሳ አድርጓል። ሙሉ ጽሑፉን እነሆ
https://bit.ly/3RnLy3e
#Ethiopia #Bahirdar
@AddisZeybe
492 views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 19:05:49 A forum aimed at holding deliberation on the equitable and reasonable utilization of the Nile water among the Nile Basin riparian states commenced in Addis Ababa. Egypt and Rwanda were not in attendance. Read more
https://bit.ly/3wX1b9A
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
317 views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 15:00:17
የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዊሊያም ሩቶን አሸናፊነት አጸና

ነሓሴ 30፤ 2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) በኬንያ ለሀገሪቱ ፕሬዝዳንትነት ነሐሴ 9 ቀን በተካደው ምርጫ ዊልያም ሩቶ አሸናፊ በተደረጉበት ውጤት ቅር የተሰኙት ተቀናቃኛቸው ራይላ ኦዲንጋ ቅሬታቸውን ለፍርድ ቤት እንዳቀረቡ ይታወሳል። በዚህም መሰረት የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዛሬው የችሎት ውሎው የዊሊያም ሩቶን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ አሸናፊነት ማጽናቱ ተነግሯል።

የሩቶ ዋና ተቀናቃኝ የሆኑት ራኤላ ኦዲንጋ ያቀረቡትን ክስ ጨምሮ የምርጫ ውጤቱ እንዲሰረዝ የቀረቡትን ሁሉንም የክስ አቤቱታዎች የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ አድርጓቸዋል።

ይህንን ተከትሎም ዊልያም ሩቶ 5ኛው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ የሚፈፅሙ ይሆናል።
_____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።
Twitter : https://bit.ly/3uQBnvj
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Telegram : https://bit.ly/3JX93LY
Website : https://bit.ly/3JOUavm
YouTube : https://bit.ly/37rIyBa
529 viewsedited  12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 11:48:42
የደሴ ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር ቤት ተጨማሪ አስገዳጅ ውሳኔዎች አሳለፈ

ነሴ 30 ፤ 2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ ፤ ደሴ) የደሴ ከተማ አስተዳደር ነሐሴ 22/2014 ዓ.ም በሀገራችን ሰሜናዊ ክፍል በህወሃት እና በፌደራል መንግስቱ ዳግም የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በከተማው ልዩ ልዩ ክልከላዎችን ማስተላለፉ የሚታወቅ ነው። እነዚህ ህጎች እንደተጠበቁ ሆነው በተጨማሪ ከነሐሴ 30/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ ተጨማሪ ክልከላዎችን ያስቀመጠ መሆኑ ታውቆ ህዝቡ ተባባሪ እንዲሆን ጠይቋል።

በዚህም መሰረት የፀጥታ አካላት አባል ሳይሆን የደንብ ልብስ መልበስ፣ ተፈናቃይ ሆኖ በከተማው በየትኛውም ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ፣ ሀሰተኛ ወሬ በመልቀቅ የጥምር ጦሩን ስም ማጠልሸት እና ማንኛውም አካል ከመንግስት አደረጃጀት ውጭ ለጦርነቱ በሚል ገንዘብ መሰብሰብ በፍጹም የተከለከለ አንደሆነ ምክር ቤቱ አስታውቋል።

ምክር ቤቱ በተጨማሪም ፀጉረ ለውጥ የሆነ ሰው በሚገኝበት ሰአት ማህበረሰቡ ተከታትሎ በአቅራቢያው ለሚገኝ የፀጥታ አካል የመጠቆምና የማቅረብ ኃላፊነት እንዳለበትና በከተማዋ የሚገኙ ማንኛውም የመንግስት እና የግል ታጣቂ በመንግስት አደረጃጀት ውስጥ በመካተት በየደረጃው ካሉ የፀጥታ አካላት በመተባበር አካባቢውን መጠበቅ አለበት ብሏል።

በማንኛውም ሰዓት ታርጋ ቁጥር የሌለው ተሽከርካሪ ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀስ ከተገኘ በቁጥጥር ስር ውሎ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድበትም ምክር ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል።
@AddisZeybe
158 viewsedited  08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 10:48:04 አዲስ አመት እንቁጣጣሽ ሲመጣ ከባህላዊ የአከባበር ስርዓቱና በአሉን ከሚያደምቁት ሌሎች ሁነቶች በበለጠ አውድ አመቱን ከሚያጎሉትና ያለፈ ትዝታችንን ቀስቅሰው ፍንትው አድርገው ከሚያሳዩን ነገሮች መካከል በአሉን ለመዘከር የተሰሩ ዘፈኖችን የሚያክል ምንም የለም። ይህ ፅሁፍ የነዚህን ዜማዎች ምናባዊ ኃይል እንዲህ ያስቃኘናል።
https://bit.ly/3KUa9KQ
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
259 views07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 20:51:26 በቅርብ ከቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት ለኢትዮጵያዊ አይነ ስውራን የተበረከተው እጅግ ዘመናዊ መሳሪያ በቀላሉ ፅሁፍ ከማንበብና ሰዎችን ከመለየት ባሻገር ለተጠቃሚዎቹ ከፍተኛ ተስፋን ፈንጥቋል። የመሳሪያው ተጠቃሚ የሆነው የአዲስ ዘይቤ ሪፖርተር በጉዳዩ ዙሪያ አጭር ዳሰሳ አድርጓል
https://bit.ly/3CTVUUl
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
367 views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ