Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የሰርጥ አድራሻ: @addiszeybe
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.27K
የሰርጥ መግለጫ

ለፈጣን መረጃዎች አዲስ ዘይቤ
Twitter : https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Website : https://addiszeybe.com/
YouTube : https://youtube.com/c/AddisZeybe
Instagram : https://bit.ly/3D1tEwC
ስልክ 251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 99

2022-08-29 18:38:25
በሲዳማ ክልል ከ3 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተጋልጧል መባሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስተባበለ

ነሐሴ 23 ፤ 2014 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ: ሐዋሳ) በሲዳማ ክልል ወቅቱን የጠበቀ ዝናብ ባለመዝነቡ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተጋልጧል የተባለዉ መረጃ ሀሰት እንደሆነ የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልጿል።

ከአዲስ ዘይቤ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሰብል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለሙ በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት በ 17 ወረዳዎች በአየር ንብረት ለዉጥ ምክንያት በተከሰተዉ አደጋ ከ 3 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለረሃብ ተጋልጧል መባሉ “የተሳሳተ እና መሰረተ ቢስ መረጃ ነዉ" ብለዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ በወቅቱን ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት በክልሉ በሚገኙ 15 ወረዳዎች ከ 25 ሺህ ሄክታር በላይ በቆሎ እና የቦለቄ ምርት መውደሙን በማንሳት "በዚህም ምክንያት ከ62 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እና በቤተሰብ ደረጃ ደግሞ ከ 30 ሺህ በላይ ሰዎች ለአደጋዉ ተጋላጭ" መሆናቸውን ጨምረዉ ገልፀዋል ።

የሲዳማ ክልል የግብርና ቢሮ ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር ለችግሩ ተጋላጭ ለሆኑ አርሶ አደሮች ማካካሻ የሚሆን 47 ሚሊዮን ብር በመበጀት ዘር እንዲገዛ መደረጉ የተነገረ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ለሰብአዊ እርዳታ የሚዉል 50 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ 97 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ወደ ስራ መገባቱን አዲስ ዘይቤ ያገኘችው መረጃ ያሳያል።
@AddisZeybe
671 views15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:59:55
የሚድያ አጠቃቀም ክህሎትን ለማሳደግ ያለመ ስልጠና ለመምህራን እና ተማሪዎች መሰጠት ጀመረ

ነሐሴ 23፤ 2014 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን መቀነስ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራንና ተማሪዎች መሰጠት ጀመረ።

ስልጠናውን አዲስ ዘይቤ ዲጂታል ሚድያ ከሚድያ ልማት አጋሩ ኢንፎርም አፍሪካ ጋር በመተባበር የሚሰጡት ሲሆን በሚድያ አጠቃቀም ክህሎት እንዲሁም የሐሰተኛ መረጃ ስርጭቶችን መለየት እና መቆጣጠር በሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ ያተኮረ ነው።
ከዛሬ ጀምሮ እየተሰጠ በሚገኘው ስልጠና ከአዲስ አበባ 11ዱም ክፍለ ከተሞች ከሚገኙ 22 የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 66 መምህራንና ተማሪዎች ይሳተፋሉ።

ስልጠናው በተጨማሪም ከሻሸመኔ እና ምዕራብ አርሲ ለተውጣጡ ሰልጣኞች በሻሸመኔ ከተማ እንዲሁም ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ለተውጣጡ ሰልጣኞች ደግሞ በደሴ ከተማ ስልጠናው የሚሰጥ ይሆናል።

ኢንፎርም አፍሪካ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለማህበራዊ ሚድያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ ለመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች እና ለተለያዩ ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ የሚገኝ ተቋም ሲሆን “አሪፍ ነጋሪ” የተሰኘ የሚድያ አጠቃቀም ክህሎት ዘመቻ ላለፉት ስምንት ወራት ሲያከናውን ቆይቷል።
_____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።
Twitter : https://bit.ly/3uQBnvj
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Telegram : https://bit.ly/3JX93LY
Website : https://bit.ly/3JOUavm
YouTube : https://bit.ly/37rIyBa
772 views11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:39:03
በጉራጌ ዞን የስራ ማቆም አድማውን ማስቆም አለመቻሉ ከክልል ጀምሮ ያለ ክፍተት ነው ተባለ

ነሐሴ 23፤ 2014 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) በጉራጌ ዞን ከአደረጃጀት ጥያቄ ጋር በተያያዘ እየተደረገ ያለው የስራ ማቆም አድማን ማስቆም አለመቻሉ የፀጥታ መዋቅሩ ክፍተት ነው ተባለ።

የዞኑ የመንግስት ኮምኒኬሽን ቢሮ እንዳስታወቀው በዞኑ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ትላንት ነሐሴ 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ግምገማ የተካሄደ ሲሆን አድማውን ማስቆም አለመቻሉ ከክልል መዋቅር ጀምሮ ያለ ክፍተት ነው ተብሏል።

“የአደረጃጀት ጥያቄ በተመለከተ ህዝቡ በህጋዊ መንገድ ከመጠየቅ ውጪ ህብረተሰቡን ከስራ ውጪ ሊያደርጉና የጸጥታ ስጋት ለመፍጠር የአድማ እንቅስቃሴ ለማድረግ በሚሞክሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ” ተገልጿል።

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. የስራ ማቆም እና ቤት ዉስጥ የመቀመጥ አድማ እየተደረገ እንደሚገኝ አዲስ ዘይቤ የዞኑ ነዋሪዎችን አነጋግራ መዘገቧ ይታወሳል። ነዋሪዎቹ እንደሚናገሩት ከሆነ የስራ ማቆም አድማው “የሰላማዊ ትግል” አካል ሲሆን በኮማንድ ፖስት እና በፀጥታ አካላት ወጣቶችና አመራሮች ለእስር እየተዳረጉ እንደሚገኙም መግለፃቸው ይታወሳል።

የአዲስ ዘይቤ የሐዋሳ ዘጋቢ ከወልቂጤ ባሰባሰበው መረጃ የስራ ማቆም አድማው በተወሰነ ደረጃ እየቀረ እና ከጥቂት የንግድ ተቋሞች ውጪ ወደ ስራ የመመለስ ሁኔታ መኖሩን አረጋግጧል። ይሁን እንጂ አሁንም የፀጥታ ኃይል በአካባቢው በመኖሩ ከወትሮው የተቀዛቀዘ ድባብ መኖሩን ነዋሪዎች አስረድተዋል።
@AddisZeybe
684 viewsedited  11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:57:45 The current higher inflation rate in the country and the soaring price of commodities don’t seem to be affecting the car dealing business. Cramming up and overflowing the companies’ compounds, Dzire cars are even parked outside on the streets, crowding up the space. Read more
https://bit.ly/3KsIqk4
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
726 viewsedited  08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:17:23
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድሬዳዋ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ነሐሴ 23፤ 2014 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ከተማ የሙከራ ስራውን መጀመሩን አስታውቋል። ደንበኞችም የፈልጉትን ስልክ ቁጥር መርጠው ሲም ካርድ መግዛት እንደሚችሉ አስታውቋል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እንደገለፀው በድሬዳዋ በጀመረው የሙከራ ትግበራ የ2G፣ 3G እና 4G ኔትዎርኮችን ያስጀመረ ሲሆን የተቋሙ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች ደንበኞች ሲም ካርድ መግዛት ይችላሉ ብሏል። ከሲም ካርድ በተጨማሪም የስልክ ቀፎ እንደሚሸጥ ተገልጿል።

ሲም ካርዶቹ የደንበኛነት ማስጀመሪያ ጥቅል እንዳላቸው የተገለፀ ሲሆን የአየር ሰዓቱ ሲያልቅ በተመሳሳይ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሽያጭ ማዕከላት እና መደብሮች መግዛት እንደሚቻል አስታውቋል።

በተጨማሪም የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ የሚረዳ ‘700’ አጭር ቁጥር የደንበኞች አገልግሎት የጥሪ መስመር ድርጅቱ ያቀረበ ሲሆን በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ሶማልኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች ድጋፍ ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

የሳፋሪኮም ደንበኞች የኢንተርኔት ዳታ መጠቀም፣ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር የድምፅ እና የፅሁፍ መልዕክት መለዋወጥ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ጥሪዎች ማድረግ እንደሚችሉ ተገልጿል።
_____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።
Twitter : https://bit.ly/3uQBnvj
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Telegram : https://bit.ly/3JX93LY
Website : https://bit.ly/3JOUavm
YouTube : https://bit.ly/37rIyBa
749 views08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:17:08 ወቅቱ የክረምት ጊዜ እያለቀ ወደ ፅጌ መሻገሪያ ላይ እንደመሆኑ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ በዓላት እንደሚከበሩ ይታወቃል። እንደአብዛኞቹ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሁሉ የአዲስ ዘመን መጥባት በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ስፍራና ተወዳጅ የአከባበር ለዛ አለው። ሙሉ ጽሑፉን እነሆ
https://bit.ly/3e8tT12
#Ethiopia #AddisAbaba #Oromia
@AddisZeybe
747 views07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 19:54:34
በደባርቅ ከተማ የሰአት እላፊ ገደብና አስገዳጅ ውሳኔዎች ተላለፉ

ነሃሴ 22 ቀን 2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ: ጎንደር) የደባርቅ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የፀጥታ ስጋት ምክንያት የሰአት እላፊ ገደብና በከተማው የሚከናወኑ አስገዳጅ ተግባራት ላይ ውሳኔ አስተላለፈ።

በዚህም በከተማዋ የሚገኙ ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 1 ሰአት በኋላ የመንቀሳቀስ ገደብ ሲጣልባቸው፣ ነዋሪዎች ፀጉረ ለውጥ ሲያጋጥማቸው ለህግ አካል ጥቆማ እንዲሰጡ እንዲሁም በከተማዋ የሚገኙ ባለሆቴሎች እና መኝታ ቤቶች ማንነቱ ያልታወቀ ሰው ሲያጋጥም ለህግ አካላት እንዲያሳውቁ ተጠቁሟል።

በውሳኔው በከተማዋ የሚገኙ የተፈናቃይ መጠለያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከምሽት 12 ሰዓት በኋላ ወደ ካምፑም ሆነ ወደ ከተማዋ መግባት እንደማይቻል ገልጿል።

በተጨማሪም በከተማዋ የሚገኙ ቤት አከራዮች ያከራዩትን ግለሰብ መረጃ ፎርም ሞልተው ለፀጥታ ፅ/ቤት እንዲያሳውቁ እና አዲስ የሚያከራዩትንም ግለሰብ ማንነቱን እንዲያጤኑ የተነገረ ሲሆን እነዚህን ውሳኔዎች የጣሰ ማንኛውም አካል ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት የከተማው የፀጥታ ምክር ቤት አሳስቧል።
@AddisZeybe
953 viewsedited  16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 19:42:15 አልጋ ቤት፣ የመኖሪያ ቤት ወይም መደብ ቤት አከራዮች የየትኛውንም ተከራይ ማንነት የሚገልፅ መረጃ ለፀጥታ ተቋማት የመስጠት ግዴታ የተጣለባቸው ሲሆን ነዋሪዎች በከተማው ውስጥ የሚስተዋሉ ፀጉረ- ልውጦችን በመከታተል በፍጥነት ለፀጥታ ሃይሉ ጥቆማ እንዲያደርሱ የአስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት አሳስቧል።

በተጨማሪም ወጣቶች አካባቢያቸውን በመጠበቅ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ እና የከተማው የፀጥታ ሃይሎች ከምንጊዜውም በላይ በመቀናጀትና በመደራጀት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
@AddisZeybe
832 views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 19:42:01
በደሴ ከተማ ላልተወሰነ ጊዜ የሚተገበሩ አስገዳጅ ውሳኔዎች ተላለፉ

ነሃሴ 22/2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ: ደሴ) የደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የከተማው ሰላምና ደህንነት ላይ ከመከረ በኋላ በከተማው ላልተወሰነ ጊዜ የሚተገበሩ አስገዳጅ ውሳኔዎችን ማስተላለፉን አስታወቀ።

በከተማ ደረጃ የምግብ ቤቶች ፣ የምሽት መጠጥ ቤቶች/ግሮሰሪዎች/ ከምሽቱ 1፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት የተከለከሉ ሲሆን በተጨማሪም ማህበረሰቡን ወይም የከተማውን ነዋሪዎች ለተጨማሪ ችግር ለመዳረግ በማንኛውም ምርት ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የፀጥታ ምክር ቤቱ ገልጿል።

በመፈናቀልም ሆነ በሌላ ማንኛውም ምክንያት ወደ ደሴ ከተማ የገቡ ተፈናቃዮችን በተመለከተ የከተማውን ደህንነት ለማስጠበቅ ለጋራ ደህንነት ለሚተገበሩ የፍተሻና የቅድመ-ጥንቃቄ ስራዎች ተባባሪ እንዲሆኑ ተጠይቋል።

በውሳኔው ወደ ከተማው በማንኛውም ምክንያት የገቡ እንግዶች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ፣ ከተፈቀደላቸው የከተማው የፀጥታ ሃይሎች ውጭ ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ፣ ከነሀሴ 22/2014 ዓ.ም ጀምሮ የትኛውም የከተማው ነዋሪ ከምሽቱ 2:00 /ሁለት/ ሰዓት ጀምሮ በተናጠልም ሆነ በጋራ መንቀሳቀስ፣ የሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጆች) እስከ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት እንዳይሰጡ እንዲሁም የትኛውም የከተማው ነዋሪ ከምሽቱ 2:00 /ሁለት/ ሰዓት ጀምሮ በተናጠልም ሆነ በጋራ መንቀሳቀስ ተከልክለዋል።
867 views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 17:50:44
በወልደያ ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ

ነሃሴ 22/2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ: ደሴ) የወልደያ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን አካባቢ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ከነሐሴ 22 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ አውጥቷል።

በዚህም መሰረት ለጸጥታ ስራ ከተመደበ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ሰው መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። በተጨማሪም ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጠው ተሽከርካሪ ውጭ ማንኛውም ተሽከርካሪ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ የማይችል መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

የመንግስት ኮሚኔኬሽን አገልግሎት ትላንት ባወጣው መግለጫ የህወሓት ኃይሎች የቆቦ ከተማን ከተለያየ አቅጣጫ እያጠቁ እንደሆነ በመግለፅ “የህዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ ሲባል” የመከላከያ ሰራዊት የቆቦ ከተማን በመልቀቅ ለመከላከል የሚያስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ እንደተገደደ መግለፁ ይታወሳል።

የሰአት እላፊ ገደብ የተጣለባት ወልደያ ከቆቦ ከተማ ወደ 50 ኪሜ ርቀት ላይ ትገኛለች።
@AddisZeybe
870 views14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ