Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የሰርጥ አድራሻ: @addiszeybe
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.27K
የሰርጥ መግለጫ

ለፈጣን መረጃዎች አዲስ ዘይቤ
Twitter : https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Website : https://addiszeybe.com/
YouTube : https://youtube.com/c/AddisZeybe
Instagram : https://bit.ly/3D1tEwC
ስልክ 251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 98

2022-08-31 12:21:21
ህወሓት በዋግ፣ ወልቃይትና በሱዳን ድንበር በኩል ወረራ ከፍቷል ሲል መንግስት ገለፀ

ነሐሴ 25፤ 2014 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) የህወሓት ኃይል በዋግ፣ በወልቃይት እና በሱዳን ድንበር በኩል ወረራ ከፍቷል ሲል የመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል።

የመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው መግለጫ መከላከያ ሰራዊት ወረራውን እየተከላከለ እንደሚገኝም አስታውቆ “የኢትዮጵያ መንግስት በተለያዩ አቅጣጫዎች የተከፈቱበትን ጥቃቶች በፅናት እየተከላከለ፣ አሁንም ለሰላም አማራጮች የዘረጋቸውን እጆች ዛሬም ድረስ አላጠፈም” ብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የህወሓት ማዕከላዊ ኮማንድ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ "ትላንት ምሽት በመቀሌ ከተማ የመንግስት ኃይል በወሰደው የድሮን ጥቃት የህክምና ተቋም ተመቷል" ብለዋል። ይህን በተመለከተ የፌዴራል መንግስት በመግለጫው ያለው ነገር የለም።
_____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።
Twitter : https://bit.ly/3uQBnvj
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Telegram : https://bit.ly/3JX93LY
Website : https://bit.ly/3JOUavm
YouTube : https://bit.ly/37rIyBa
547 views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:13:06 በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም ተመርቆ በ2014 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ሥራ የጀመረው የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ በመጀመሪያው ምዕራፍ ለ4 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጾ ነበር። ይሁንና ስራ የጀመሩትም ጥቂት ሰራተኞች በድንገት ስራ እንዲያቆሙ ተደርጎ ደሞዝ እየተከፈላቸው ተቀምጠዋል። ሙሉ ጽሑፉን እነሆ
https://bit.ly/3CKCzF4
#Ethiopia #Bahirdar
@AddisZeybe
527 views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:58:44
የላሊበላ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የሰዓት ዕላፊ ገደብን ጨምሮ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ

ነሃሴ 24፣ 2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ፤ ጎንደር) የላሊበላ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ ሁኔታን መነሻ በማድረግ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ወደ ከተማዋ መግባትም ሆነ መውጣት እንደማይቻል እና ማንኛውም ተሽከርካሪ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋቱ 12:00 ድረስ መንቀሳቀስ እንደማይችል አሳውቋል።

በተጨማሪም ከተፈቀደለት አካል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንዲሁም በመንግስት ዕውቅና ካለው የፀጥታ አካል ውጭ የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ ለብሶ መንቀሳቀስ በፍፁም እንደማይቻል ገልፆ ህዝቡ በሀሰተኛ ወሬ እና አሉባልታ ሳይደናገር አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ የፀጥታ ምክር ቤቱ መልዕክት አስተላልፏል።
@AddisZeybe
747 views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:57:29 በከተማዋ ያሉ አዳር የሚሰሩ ፋብሪካዎችና ድርጅቶች ድርጅቱ በሚሰጣቸው ህጋዊ መረጃና በፀጥታ መዋቅሩ የተረጋገጠ የይለፍ ፈቃድ ከያዘ ብቻ መንቀሳቀስ እንደሚቻል አንዲሁም መላው የከተማው ማህበረሰብ በአደረጃጀት አካባቢውን ቀንና ሌሊት ከሰርጎ ገቦች በንቃት መጠበቅ እንዳለበትም ተጠቁሟል።

የከተማው ባለሆቴሎች እና አልጋ አከራዮች ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ግለሰብ በድርጅታቸው ሲያጋጥማቸው ለህግ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ እና በከተማ አስተዳደሩ ያሉት የቤት አከራይዎች የሚያከራዩትን ግለሰብ ማንነት መታወቂያ በመጠየቅ ለይተው እንዲያከራዩ የተከራዩትንም መረጃ በፎርም በመሙላት ለከተማው ሰላምና ፀጥታ መምሪያ እንዲያሳውቁ የፀጥታ ምክር ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል።
@AddisZeybe
666 views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:57:19
የደብረ ብርሃን ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ ሁኔታዎችን አስመልክቶ አስገዳጅ ውሳኔዎችን አስተላለፈ

ነሃሴ 24፤ 2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ፤ ደብረ ብርሃን) የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ባለው ወቅታዊ የፀጥታ ስጋት ምክንያት በከተማዋ የሚተገበሩ አስገዳጅ ውሳኔዎችን አስተላለፈ።

በዚህም መሰረት በከተማው የሚገኙ ሁሉም አይነት ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ክልክል መሆኑ ተገልፆ ይህን ሲያደርግ የተገኘ ማንኛውም ተሽከርካሪ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድበትና በከተማው የሚገኙ መጠጥ ቤቶች፣ ምግብ ቤቶች እና ምሽት ጭፈራ ቤት እስከ ምሸት 2:00 ሰአት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል።

በከተማ አስተዳደሩ በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚኖር ተፈናቃዮች ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በኋላ ወደ መጠለያ ጣቢያውም ሆነ ወደ ከተማው መግባት ክልክል እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን በከተማው በሚገኙ የንግድ ቤቶች የምርት የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን እንዲሁም ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ሀይሎች ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የተከለከለ እንደሆነ ተገልጿል።

እንዲሁም ከመንግስት ዕውቅና ውጭ የሚደረጉ ማናቸውም አይነት ውይይቶችና ስብሰባ ማድረግ ፣ "የጠላትን ሀሳብና እንቅስቃሴ በመደገፍ አሉባልታና ወሬን ማሰራጨትና በህብረተሰቡ ላይ ሽብር መንዛት" በጥብቅ ተከልክሏል።
648 views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:33:56 በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በመኖሪያ ፍቃድ ምክንያት “ህገ ወጦች ናችሁ” በሚል እስር፣ እንግልትና የሰብአዊ መብት ጥሰት እየደረሰባቸው እንዳለ በተለይ ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል። እስሩ በተለይ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረ እንደሆነም አስረድተዋል። ስደተኞቹ ሱዳን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም “ዲፕሎማሲያችን የተበላሸ በመሆኑ ምንም ማድረግ አንችልም” የሚል ምላሽ እንደሚሰጣቸውም ጨምረው ተናግረዋል።
https://bit.ly/3RkCawX
#Ethiopia #AddisAbaba #Sudan
@AddisZeybe
134 views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:56:46
በሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የመንግስትም ሆነ የግል ታጣቂዎች የመንግስትን የፀጥታ ስምሪት መቀበል ግዴታ ሆነ

ነሃሴ 24/2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ፡ ባህር ዳር) የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ነዋሪዎች ስጋት ውስጥ እንዳይገቡ እና የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል የተለያዩ ገደቦችን ማስቀመጡን አስታወቀ።

በገደቦቹ መሰረትም በሰቆጣ ከተማ የሚገኙ የመንግስት እና የግል ታጣቂዎች መንግስት በሚያሰማራው የፀጥታ ስራ ላይ ተሳታፊ የመሆን ግዴታ እንዳለባቸው ተገልጿል። ከዚህም ባለፈም ተፈናቃዮች ከተሰጣቸው ካምፕ ውጪ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ፣ ማንኛውም እግረኛ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ መከልከሉ፣ ከፀጥታ አካላት ተሸከርካሪዎች ውጭ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ተገልጿል።

በተጨማሪም ከፀጥታ መዋቅሩ ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ባንክ ቤቶች፣ ሱቆች፣ ሆቴል እና መስል የመንግስትና የግል ድርጅቶችን መዝጋት በጥብቅ የተከለከለ ሆኗል። እነዚህን ጨምሮ ሌሎችም ገደቦችና ሀላፊነቶች የተቀመጡ ሲሆን ደንቡን በማያከበር ማንኛውም አካል የፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የከተማው ፀጥታ ምክር ቤት አስታውቋል።
@AddisZeybe
483 views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:57:40 የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና 3.5 ቢሊዮን ዶላር በጀት የተመደበለት የደረቅ ወደብ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ያካተተ “በኢትዮጵያ ግዙፍ የንግድና ኢንዱስትሪ ከተማ” የተባለለት ነው። ድሬዳዋ የኢንዱስትሪ መንደር፣ የባቡር፣ የየብስ እና የአየር ትራንስፖርት መሰረተ ልማት አጣምራ የያዘች በመሆኗ ለዚህ የንግድ ማዕከልነት ተመርጣለች። ሙሉ ጽሑፉን እነሆ
https://bit.ly/3e5QHhI
#Ethiopia #DireDawa
@AddisZeybe
504 viewsedited  11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:34:55 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በጎንደር ከተማ የመብራት አገልግሎትን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ አዳዲስ ምሰሶዎችን ቢዘረጋም በአጼ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ አንዳንድ ምሰሶዎችም ጠንካራ ከመሆናቸው የተነሳ እስካሁን ድረስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ሙሉ ጽሑፉን እነሆ
https://bit.ly/3czLWNa
#Ethiopia #Gonder
659 viewsedited  08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:38:58
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በፀጥታ ስጋት ግቢውን ለቀው በወጡ ተማሪዎች ጉዳይ ውሳኔ አስተላለፈ

ነሐሴ 23 ፤ 2014 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ: ደሴ) ትላንት እሁድ ነሐሴ 22 ቀን በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ባገረሸው የፀጥታ ስጋት ምክንያት የወልድያ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ግቢውን ለቀው መውጣታቸው የታወቀ ሲሆን ስለተማሪዎቹ መመለሻ ቀንና እየተካሄዱ ባሉ የትምህርት መርሃ ግብሮች ዙሪያ ዩኒቨርሲቲው ውሳኔ ማስተላለፉን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ለመደበኛ መርሃ ግብር ተማሪዎች የመመለሻ ቀን በቀጣይ አመት ጥሪ እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን ለክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች የተጀመረውን ትምህርትና ፈተና ለማጠናቀቅ መስከረም 3፣ 2015 ዓ.ም እንዲሆን ዩኒቨርሲቲው ውሳኔ አስተላልፏል።

በተፈጠረው የፀጥታ ስጋት በድንገት ከወልድያ ዩኒቨርሲቲ የወጡት ተማሪዎቹ የ150 ብር የትራንስፖርት ታሪፍ የተተመነለትን የ120 ኪሎ ሜትር መንገድ ለአንድ ሰው ከ2000 ብር በላይ በመክፈል ወደ ደሴ ከተማ ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ መግባታቸውን አዲስ ዘይቤ መረዳት ችሏል። ከተማው ላይ ካለው የስደተኛ ብዛት አንፃር ሆቴሎች በመጨናነቃቸው ምንም አይነት ማረፊያ ሳያገኙ ሌሊቱን እንዳሳለፉ ያነጋገርናቸው ተማሪዎች ገልጸዋል።

"ዩኒቨርሲቲው ወደግቢ እንድንመለስ ጥሪ ቢያደርግም አብዛኞቻችን ገንዘብ በመጨረሳችንና የትራንስፖርት መክፈል ስለማንችል የዩኒቨርሲቲው አውቶብሶች ደሴ ድረስ በመምጣት ቢመልሱን ወይንም ሌላ የትራንስፖርት አማራጭ የምናገኝበትን መንገድ ቢያመቻችልን ከተጨማሪ እንግልት እና ወጪ ይታደገናል" በማለት ተማሪዎቹ ስጋታቸውን አጋርተውናል።
@AddisZeybe
860 views15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ